tgoop.com/KALTUBE/11370
Last Update:
⭐ =እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን=⭐
ከሺህ አመታት በፊት ቀድሞ በነቢያት በትንቢት በተነገረው መሰረት ጌታችን ሰው ሆኖ ከድንግል ያለወንድ በመንፈስ ቅዱስ ተፀነሰ፣ በመንፈስቅዱስ የሃጢአት ውርስ ተካፋይ እንዳይሆን ተከልሎ ተወለደ፣ሲወለድም በሰማይ ሰራዊት ታጀበ፣በዙርያው የሰማይ ብርሃን በራ፤ በመወለዱም ንጉስ ሄሮድስ ተቆጣ። እረኞችም ክብሩን አዩ።ሰብአሰገል ዕጣን፣ከርቤና ወርቅ አመጡለት ሰገዱለትም።
ዕጣኑ ክህነቱን፣ከርቤው ደግሞ የኢየሱስን ሞት ፣ወርቁ ደግሞ የኢየሱስን ንግስና የሚያሳይ ምስጢር ነበር።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተወለደ ??⛤
1ኛ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ለማሳየት ነው።
2ኛ እኛን ዳግም ለመውለድ ነው።
3ኛ የአለምን ሃጢአት ለማስወገድ ነው።✞
4ኛ እራሱን ስለእኛ የሃጢያት መስዋዕት ለማድረግ ነው።
5ኛ ፍፁም ሰው ሆኖ ህግን ለመፈፀም ነው።
6ኛ እኛን የእግዚአብሔር ፅድቅ ለማድረግ ነው።
7ኛ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ለመሆን ነው።✞
8ኛ ለአለም ሁሉ ስጦታ ለመሆን ነው።
9ኛ ነፍሱን ለብዙዎች አሳልፎ ሊሰጥ ነው።
10ኛ የመንግስተ ሰማይ ብቸኛ መንገድ መሆኑን ለማስረዳት።
11ኛ የእግዚአብሔር አብ ፈቃድ በምድር ለመፈፀም ነው።
12ኛ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት ያገኝ ዘንድ ነው።
⛤ታድያ እርሶ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው ድነዋልን?
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።የዮሐ 3 : 16
አዎ አምናለሁ የምንል ከሆነ.....
በክርስቶስ አምናለሁ ብሎ የሚል ሰው እምነቱ ትክክለኛ መሆን አለመሆኑ የሚረጋገጠው በእግዚአብሔር ቃል ነው።
በክርስቶስ ማመን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በእግዚአብሔር ቃል መረዳት ያስፈልጋል።
ብዙ ሰዎች ኢየሱስን የሚያምኑት በብቸኝነት ሳይሆን -በደባልነት- ነው።
ይህ ማለት አዳኝ፣አማላጅ ብለው የሚያምኗቸው ብዙዎች አሉ።ኢየሱስን ማመን ማለት ግን ምን ማለት ነው?
1ኛ -ኢየሱስን ማመን ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ =ብቸኛ= አዳኝ እንደሆነ ማመን ነው።
-ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። የዮሐ 14 : 6
-መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋ 4 : 12
2ኛ -ኢየሱስን ማመን ማለት የዘላለም ህይወት የሚሰጠው እሱ ብቻ እንደሆነ መቀበል ነው።
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤የዮሐ 1 : 12
3ኛ-ኢየሱስን ማመን ማለት በኢየሱስ አማላጅነት ማመን ማለት ነው።
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ሮሜ 8 :34
4ኛ- ኢየሱስን ማመን ማለት ደህንነት በፀጋ እንጂ በስራ እንደማይገኝ ማመን ነው።
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና። ኤፌ 2 : 5
5ኛ-ኢየሱስን ማመን ማለት ኢየሱስ ለሃጢያታችን እንደሞተልን ከሞትም እንደተነሳልን ማመን ነው።
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሮሜ 10 : 9
6ኛ-ኢየሱስን ማመን ማለት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ማመን ማለት ነው። ዮሐ 3:16
ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ አምኛለሁ የሚል ሁሉ ከላይ የተጠቀሱትን መፅሃፍ ቅዱሳዊ እምነት ካልተከተለ ጤናማ የሚያድን እምነት እየተከተለ አይደለም። ክርስቶስን የምናምነው ቃሉ እመኑት ባለው መንገድ እንጂ እኛ በፈለግነው መንገድ አይደለም።
ኢየሱስ ክርስቶስ የክርስትና ህይወት ተጨማሪ ሳይሆን ብቸኛ የእምነታችን መሰረት ነው።ኢየሱስ የክርስትና ህይወት ጀማሪና ፈፃሚ ነው።
ክርስቶስን አምናለው የሚል ሁሉ እምነቱ የሚፈተነው በቃሉ ነው።በቃሉ አስተምህሮ ኢየሱስ ተጨማሪ ተመላኪ አይደለም። በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሰው አምልኮተ መላእክትን አይከተልም፤ወደ ሞቱ ፃድቃን ለምልጃ አይፀልይም።ሌሎች ሰው ሰራሽ እና ተረት ተረት አይከተልም።
በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምን ደህንነት በፀጋ እንጂ በስራ እንዳልሆነ ያምናል። ኢየሱስን አምናለሁ የሚል ፅድቃችን ክርስቶስ እንጂ የኛ መልካም ስራዎች ውጤት እንዳልሆነ ያምናል።
እናም በነዚህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መስፈርቶች አንድ ሰው በክርስቶስ ማመን አለማመኑንና የእምነቱን ጤናማ መሆን አለመሆኑ ይረጋገጣል።
በድጋሚ መልካም የጌታ ልደት በአል ይሁንላችሁ! ይሁንልን!
✦ መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
BY #KALTUBE
Share with your friend now:
tgoop.com/KALTUBE/11370