tgoop.com/KALTUBE/11373
Last Update:
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 36
የዲያብሎስን ሽንገላ መቃወም
የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ኤፌ 6:11
ዲያብሎስ የሚለው ቃል የመጣው ከግሪክ ዲያቦሎስ ከሚለው ቃል ሲሆን፣ ፍችውም “ስም አጥፊ” ወይም አታላይ 'ሐሰተኛ ከሳሽ' ማለት ነው። (The Tempter and slanderer)
> 'ሰይጣን' ማለት ደግሞ 'ጠላት'ባላንጣ የሚል የዕብራይስጥ ትርጉም አለው። እንደሚታወቀው የመጀመሪያው የሐሰት ክስ እና ከፍተኛ የሆነ የማጭበርበር ተግባር የጀመረው በኤደን ገነት ውስጥ ነበር።
➢ዲያብሎስ እጅግ ኃያል ፣ብርቱና ልዕለ ኃያል ፍጡር አይደለም።ምክንያቱም በሰማይ ሊያካሂድ ያሰበውን መፈንቅለ ዙፋን ተከትሎ በደረሰበት ከባድ የመለኮት ቁጣና ቅጣት አመድ ተደርጎ እንደተወረወረ ቃሉ ይናገራል። (ሕዝ 28:23-19)
➢ላለፉት ሺህ አመታት ሰይጣን ብዙዎችን ወደራሱ መንግስት በማፍለስ የተሳካለት ምክንያት በማታለል ወይም በማጭበርበር ነው። ዲያብሎስ ማንንም ከሀሳብ በፊት አይዋጋም ።ማለትም ቀድም ሀሳብ ሳይረጭ ወይም ሳይወረውር ማንንም ለማጥቃት አይወጣም።
➢አታላይ ሀሳብ የዲያብሎስ ትልቁ ስልቱ ነው። ዲያብሎስ ለሺህ አመታት የተቀመሙ እና አዋጭነታቸው የተረጋገጡ የተንኮል ሀሳቦችን እየፈበረከ ዛሬም ድረስ ወደ ሰዎች አዕምሮ ይወረውራል። አብዛኛው የማታለያ ዘዴው ተመሳሳይ የሆነ ነገር ግን የተሻሻለ (Upgraded )ነው።
➢ሐዋርያው ጳውሎስ ለአፌሶን ቅዱሳን በፃፈው መልዕክቱ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ በማለት ያሳስባል።
➢ያኔ ኤደን ገነት ውስጥ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠሩ ባልና ሚስት መካከል ገብቶ ግራ ያጋባቸው በጉልበቱ ሳይሆን በተንኮሉ ነበር።
ዲያብሎስ ሄዋንን ለማሳት የተጠቀመበት ስልት :--
1ኛ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን?”አላት።(ዘፍ 3:1)
ይህ ንግግሩ introduction ወይም የመግቢያ ንግግር ነው። ሰይጣን ደህና አደራችሁ ?ሰላም ዋላችሁ ማለት ስለማይችል ቀጥታ ወደገደለው ለመግባት የሚያንደረድ ረውን በጥያቄ ጀመረ።
2ኛ ቀጠለ....እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤ አላት። ዘፍ 3:2
ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ነበር:--
'እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤
ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” ዘፍ 1:16-17
ይህ ስልት እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘዛቸውን ትዕዛዝ ቢጥሱም ምንም እንደማይሆኑ የሚያሳምን ነበር። ሞት ያለመታዘዝ ውጤት መሆኑን ዲያብሎስ እያወቀ ነገር ግን ባትታዘዙም ችግር የለውም በሚል የንግግር ቅላፄ አሳመናት።
ሄዋንም ፈሪሀ እግዚአብሔር ከውስጧ ወጣና የመብላት ፍላጎቷ ጨመረ በመጨረሻም ቀንጥሳ በላች ባሏዋንም አበላችው። ተልዕኮው ተጠናቀቀ!!
3ኛ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ዘፍ 3:5
ይህ የተንኮል ንግግሩ እግዚአብሔርን እንዲጠራጠሩ የሚያደርግና አትብሉ ያለን አይናችን እንዳይከፈት ፈልጎ ነው እንዴ ብለው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንዲጠራጠሩ ነበር።
➢እንደ አዲስኪዳን ህዝቦች ዲያብሎስን የምንቃወመው በትረ ስልጣኑን ለመንጠቅ አይደለም።ኢየሱስ አስቀድሞ ነጥቆታል። አሁን ሰይጣን የታጠቀው ተንኮል ነው።
ተንኮልን ደግም የምናሸንፈው በኢየሱስ አዕምሮ ነው።አንድን ተንኮል ከነቃችሁበት አይሰራባችሁም።የሚሰራው ከተሸወዳችሁ ብቻ ነው።ላለመሸወድ ደግሞ አዕምሯችን በቃሉ ብስል ሊሆን ይገባል።
➢ በቃሉ ያልበሰለና ቃሉን እንደ ልብስ ያለበሰ አማኝ በቀላሉ ይታለላል። በቃሉ የማይፈርስ የሰይጣን ተንኮል የለም። ስለሆነም የቃሉን መንፈስ፣የቃሉን እውቀት ፣የቃሉን ኃይል፣የቃሉን ጥበብና የቃሉን መንገድ በመከተል የዲያብሎስን ሽንገላ በቀላሉ ማክሸፍና ማሸነፍ እንችላለን።
✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
ክፍል 37 ይቀጥላል
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
BY #KALTUBE
Share with your friend now:
tgoop.com/KALTUBE/11373