tgoop.com/KALTUBE/11382
Last Update:
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 41
እንደ እባብ ብልሆች
“እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ማቴ 10:16
➢መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ90% በላይ እባብ በክፋቱ እና ሰይጣንን በመወከል የተጠቀሰ ሲሆን በዚህ ክፍል ግን ጥበብን ወክሎ ተጠቅሷል። እባብ ከጥንት ማህበረሰብ አንስቶ እስካሁን ድረስ በአዎንታዊ ጎኑ የኃይል፣የጥበብ፣ የአስፈሪነት እና የምስጢራዊነት ተምሳሌት ተደርጎ በተለያዩ ባህሎች ውስጥ ይታመናል።
➢ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ምክር የመከረው ለደቀመዛሙርቱ ሲሆን ለወንጌል ተልዕኮና በአጠቃላይ የህይወት ምልልስ ውስጥ ሁለት አይነት ባህርያትን ተላብሰው ይኖሩ ዘንድ ነው።
አንድ እንደ እርግብ የዋሆች
ሁለት እንደ እባብ ብልሆች እንዲሆኑ።
➢የዋህ የሚለው ቃል ክፋት አለማሰብን harmless ወይንም ንፁህ መሆንን ያመለክታል። በእንግሊዝኛው ትርጉም
Behold, I send you forth as sheep in the midst of wolves: be ye therefore wise as serpents, and harmless as doves. Matthew 10:16
የዋህነት ሞኝነት እና ጅልነት አይደለም። ይህም አንዱ ክርስትያናዊ ጨዋነትና መገለጫ ነው።የዋህነት አለማስተዋል ማለት አይደለም።
➢እባብ "ብልህ" ፍጥረት ነው።በሌላ በኩል ደግሞ ርግብ ንፁህና በብሉይ ኪዳን ዘመን ለመስዋዕትነት ንፁህ ተብለው ከተመረጡ አዕፋት መካከል አንዱ ነበር። "ዘሌ14 22).
እንደ እርግብ የዋህ መሆን የልብን ንፅህና ፤ እንደ እባብ ብልህ መሆን ባለ አዕምሮ መሆንን ያሳያል።
➢እባብ አለም ላይ ካሉ ተሳቢ እንሰሳት መካከል በቁጥር እጅግ ትልቁ ነው። ወደ 3,789 የሚጠጉ የተለያዩ ዝርያዎች እንዳሉም ይነገራል። እባብ ከተወሰኑ ሜትሮች ቀድሞ ሊያጠቁት የመጡትን በምላሱ በማሽተት እራሱን ከአደጋ ይከላከላል።እባብ ጆሮ የለውም፣ነገር ግን በምላሱ በየሰከንዱ የአከባቢውን ሁኔታ ያጤናል። እባብ ሽፋሽፍት የለውም ስለዚህ አይኑ አይርገበገብም፤ አንድ ነገር ላይ ካፈጠጠ አፈጠጠ ነው። ይህም ደግም ትኩረቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።
እባብ ተደብቆ ሲለሚራባ የማይገኝበት የአለም ክፍል የለም ማለት ይቻላል። ውሃ ውስጥ፣ በበረሀ፣በጫካ ውስጥ፣አለት ውስጥ፣አፈር ውስጥ መኖር ይችላል።እባብ ስጋ በል( carnivores) ከሚባሉት የእንስሳት ምድብ የሚመደብ ነው።
እባብ አብዛኛውን ጊዜ የሚመገበው በምላሱ መርዝ ነድፎ በመግደል ነው። ምላሱ ለማሽተትም፣ መርዝ ለመርጨትም ያገለግላል። እባብ ምንም እንኳን ረጅም ሰውነት ቢኖረውም ተጠቅልሎ እራሱን ከተለያዩ ተፈጥራዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ይከላከላል። እባብ የተወሰኑ የሰውነት አካሎቹ ቢጎዱም ድጋሚ ሰውነት የመዝራት አቅም ስላለው እንደገና መኖር ይጀምራል።እባብ ድምፅ አልባ የሆነ እና እጀግ በፀጥታ የተሞላ ተሳቢ እንስሳ ነው።እባብ ከሰውነቱ ሁለት እጥፍ የሆኑ አዕፋትን እና እንስሳትን ሳያኝክ መዋጥ ይችላል።
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕ 1:5
✍ መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
ክፍል 42 ይቀጥላል
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
BY #KALTUBE
Share with your friend now:
tgoop.com/KALTUBE/11382