tgoop.com/KALTUBE/11383
Last Update:
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 43
ትጋት
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ (ሮሜ 12 : 11)
➢ ትጋት አንድን ተግባር ለማሳካት የሚያስፈልግ ብርቱ ጥረት ነው።
ትጋት አላማን ለማሳካት የሚኬድበት ርቀት ነው። ትጋት በፈተናና በተግዳሮቶች ውስጥ ሳይቀር ለአላማችን መሳካት የምናወጣውና የምንከፍለው ዋጋ ጭምር ነው።
➢ ትጋት የሚለው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃል በቃል ከ20 ጊዜ በላይ እንዲሁም በምሳሌ ከ5 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል።
➢ትጋት ተፈጥሯዊም መንፈሳዊም መርህ ነው። ይህን መርህ የሚከተል የትኛውም ሰው ከውጤት ይደርሳል።ትጋት ያለበት ነገር ለፍሬ ይበቃል። በተቃራኒው መታከት ደግሞ መነሳሳት ማጣትና ለስራ የወረደ አመለካከት እና ስንፍና ነው።
➢ ታካች መንገድ መጨረስ ይፈልጋል ነገር ግን መንገድ መጀመር አይፈልግም። ሳይሰራ እንዲሳካለት የሚፈልግ፣ሳይጸልይ እንዲመለስ ለት የሚፈልግ፣ህብረት ሳያደርግ ማደግ የሚፈልግ ነው። በአጠቃላይ ምንም ሳይዘራ ማጨድ የሚያምረው አይነት ሰው ነው።ትጉ ሰው ደግሞ በተቃራኒው።
ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፤ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።ምሳ 12 : 27
➢ታካች ሰው ሊያድን ጫካ ሄዶ መጀመርያ ላይ የወረወረው ቀስት ሳይሳካ ቢቀር ወይም ሊያድን የፈለገው የዱር እንስሳ እጁ ላይ አልገባ ቢል ምን ሊያደርግ እንደሚችል አስቡት። ወይ ተስፋ ቆርጦ ቀስቱን ወርውሮ ጥሎ አደኑን ይተዋል። ወይም ሌላ የታካች ሰው ውሳኔ ወስኖ ወደመጣበት ይመለሳል።
➢እናስተውል።ትጋት አላማን ለማከናወን የሚያስፈልግ መነሻ ካፒታል (CAPITAL) ነው። ምክንያቱም ትጋት በራሱ ሃብት ነው።
➢ያለ ትጋት ህልም ህልም ብቻ ሆኖ ይቀራል፣ ያለ ትጋት ራዕይ እውን አይሆንም፣ ያለ ትጋት በክርስትና ህይወት ማበብ አይቻልም፣ ያለ ትጋት እግዚአብሔር የሰጠንን እድልና ጊዜ በአግባቡ መጠቀም አንችልም። ያለ ትጋት በዚህ ምድር ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን አይቻልም።
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች። ምሳ 10:4
➢ እንደ አማኝ ማህበረሰብ በመንፈሳዊም፣ በማህበራዊ ህይወት በስራም ትጉዎች እና ታታሪዎች ሆነን ተፅዕኖ መፍጠር አለብን።
➢ቁጭ ብሎ በመቀመጥ የሚወርድ መና የለም።እግዚአብሔር በትጋት ውስጥ የሚባርክ አምላክ ነው።ስንፍና ተገዢ ያደርጋል፣ትጋት ግን ገዢ ያደርጋል።
የትጉ እጅ ትገዛለች፤ የታካች እጅ ግን ትገብራለች። ምሳ 12:27
ክፍል 44 ይቀጥላል
✍መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
BY #KALTUBE
Share with your friend now:
tgoop.com/KALTUBE/11383