tgoop.com/KALTUBE/11384
Last Update:
በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 44
የእግዚአብሔር ሰላም
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ሰላሜን እሰጣችኋለ ሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም።ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
ዮሐ 14:27
➢ሰላም(peace) በዕብራይስጥ Shalom- ትርጉሙም ሁለንተናዊ ጤንነት፣ ደስታ፣ ክንውን፣ሰላም መሆን ማለት ነው፡፡
➢እግዚአብሔር የልጆቹ ሰላም መሆን አጥብቆ የሚፈልግ አምላክ ነው።ጌታ እንዲህ አለ
➢የዓለም መንግስታት በየአመቱ ብዙ ቢሊየን ዶላር በጅተው ውጫዊ እና ቀጠናዊ ሰላም ለማስፈን ይሰራሉ። በ2024-2025 በዩናይትድ ኔሽን (UN) በፈረንጆቹ ወደ 6ቢሊየን ዶላር በኢትዮጵያ ብር 744,000,000,000 ብር ወጪ ተድርጓል።
➢የዓለም ስርአት እንዱን ገድሎ ለሌላው ሰላም መስጠት፣አንዱን አስሮ ለሌላው ነፃነትን መስጠት ነው።ሰላምን ለማስፈን ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ ስራዎች ይሰራሉ። ሀገራት እራሳቸውን ከአሸባሪዎች ለመከላከል ህዝቦች በሰላም እንዲኖሩ ወታደራዊ ሀይሎች ይደራጃሉ። ሀገራት ዓለምአቀፍ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ የጋራ ወታደርና ገንዘብ ያዋጣሉ። አለም ላይ ሰላም ለማስፈን የሞት ትንቅንቅ ይደርጋል።
ይህ ሁሉ ሰላም ለማግኘት ነው።
➢ዓለም የምትሰጠው ሰላም አለ። ነገር ግን ዓለም የምትሰጠው ሰላም ጊዜያዊና ሰው ሰራሽ ነው።ለዛ ነው ጌታ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም ያለው።
የዓለም ሰላም አስተማማኝ አይደለም።
➢በዚህ ሁሉ ግን ጌታ የሚሰጠን ሰላም አስተማማኝ፣ውስጣዊ እና በመንፈስ ቅዱስ አብሮነት የታጀበ ሰላም ነው።የሚያስጨንቁን ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ጌታ ቅርብ ነው።
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ፊል 4:6-7
➢ውጫችን ታውኮ ውስጣችንን በሰላም የሚሞላ የሰላም አምላክ ከልጆቹ ጋር ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሰላም መርበብ ነው።
ሰላሙ ከመታሰብ ያለፈና የላቀ ነው። የጌታ ሰላም አዕምሮ ሊገምተው አይችልም። ከነውጥ ያረጋጋል፣በሁከት ውስጥ ልዩ እረፍት ይሰጣል።
➢ ይህ ሰላም መለኮታዊ ሰላም ነው። ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ታስረው እንዴት ሊያመልኩ ቻሉ? በጣም ጠንካራ ሰዎች ስለሆኑ ወይስ የመንፈስ ቅዱስ ሰላም ከእነሱ ጋር ስለነበር? ጴጥሮስ በነጋታው ሊገደል ቀጠሮ ተይዞ እንዴት ለጥ ብሎ ሊተኛ ቻለ?
ምስጢሩ የክርስቶስ ሰላም ነው።
➢የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁን ፣ህይወታችሁን በሰላሙ ይሙላ!
ክፍል 45 ይቀጥላል
✍መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
BY #KALTUBE
Share with your friend now:
tgoop.com/KALTUBE/11384