tgoop.com/MuradTadesse/40486
Last Update:
አንድ መታወቅ ያለበትና ግልፅ መሆን ያለበት ነገር ያለ ይመስለኛል።
ይህ እፎይ (ሰለሞን ሽፈራው) የተባለ ግለሰብ ፈጣሪያችንን አላህን፣ እምነታችን ኢስላምን፣ ነቢያችንን ሙሐመድን ﷺ፣ መመሪያችንን ቁርኣንና ሐዲሥን… መሳደቡና ማንቋሸሹ፣ መቅጠፉና ለጥላቻ ሰበካው በሚጠቅመው መልኩ እያጣመመ ግጭት መጥመቁ ቃል ከሚገልፀው በላይ ቢያስከፋንም፤ ስሜታችንን ተቆጣጥረን ለፍርድ ይቅረብ እያልን ነው።
ያለነው ህግ ባለበት ሃገር እስከሆነ ድረስ በስሜታዊነት የደቦ ፍርድ ይወሰድበት አላልንም። ጠዋት ማታ እየጮኽን ያለነው ህግ ይከበር ነው። የፍትሕ ስርዓቱም ፍትሕ እየጠየቀ ያለ ሚሊዮን ህዝብ በአስቸኳይ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል። «የዘገየ ፍትሕ እንደታጣ ይቆጠራል!» እንደሚባለው ፍትሕ ሲዘገይ ህዝብ በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ያለው ታማኝነት ይቀንሳል፣ ይህን የሚያስተውሉ የጥላቻ ሰባኪዎችም የልብ ልብ ይሰማቸዋል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳለን፤ ግለሰቡን ራሳቸው እርምጃ ወስደውበት እኩይ የፖለቲካ አላማ ለማስፈፀም እንዳይጠቀሙበት የሚመለከተው የመንግስት አካል ጥብቅ ክትትል ሊያደርግና በአስቸኳይ በህግ ከለላ ስር ሊያውለው ይገባል። አንዳንድ አካላት በብዙ መልኩ ግጭት በመቀስቀስ ሃገረ መንግስቱን እስከመናድ ሙከራ ድረስ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስለሚያሴሩ፤ በብዙ መልኩ እስካሁን ሙከራቸው የከሸፈባቸው አካላት ከጀርባቸው ህዝብን ለማሰለፍ በዚህ ስስ ብልት በሆነው የኃይማኖት ጉዳይ ቁማር እንዳይጫዎቱ ጥብቅ ሥራ ሊሠራ ይገባል።
መንግስት በዚህ ረገድ ከሁሉም አካላት ጋር ተባብሮና ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ፤ ግለሰቡን ለእኩይ አላማቸው መስዋዕት ሳያደርጉት በቁጥጥር ስር አውሎ ባጠፋው ጥፋት ብቻ ተገቢውን እርምት እንዲያገኝ ማድረግ አለበት። አሊያ እነዚህ ሰዎች በመሰል ሴራቸው የሚታወቁ አረመኔዎች ስለሆኑ ራሳቸው ገድ'ለው «ገደ'ሉትና አስገ'ደሉት!» ብለው ሌላ ግጭት እንዳይቀሰቅሱ ያስፈራል። ሰዎቹ አላማችንን ያሳካል ብለው ካመኑ፤ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን በብዙ አጋጣሚዎች ታዝበናል።
አሁንም ልድገመው አቋሜን፤ ግለሰቡ በህግ ከለላ ስር ይዋል። በህግ ከለላ ስር እንዲውል ግሰለቡ ያለበትን በመጠቆም የፍትሕ ስርዓቱን ሂደት ለሚያግዝ ማንኛውም አካል 400,000 ብር ሽልማት እንሰጣለን። ይህን የሚያደርግ አካል፦
1) ከእውነት ወግኗል፣
2) የፍትሕ ስርዓቱን አግዟል፣
3) ህጉ በወንጀሉ ልክ ስለሚቀጣው ገደብ እንዳይታለፍበትና በራሱ ሰዎች ጭምር ህይዎቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ታድጓል።
አመሰግናለሁ‼
ሙራድ ታደሰ
ሐሙስ መጋቢት 4 /2017
Cc:
===
Ethiopian Federal Police
Addis Ababa Police
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
#እፎይ_ለህግ_ይቅረብ
#የጥላቻ_ሰበካ_ይቁም
#የኃይማኖት_ግጭት_ጠማቂዎች_ለፍርድ_ይቅረቡ
||
www.tgoop.com/MuradTadesse
BY Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/MuradTadesse/40486