tgoop.com/NY_YC/1169
Create:
Last Update:
Last Update:
የሰካራም ኑዛዜ
የሰከረ ሁሉ የተንገዳገደ የሳተ አቅሉን
በአዝማሪ ታግዞ ይገልጻል ስሜቱን
በደመቀው ምሽት ሰዎች በበዙበት
ሆድ የባሰው ሆኖ ብቅል አወጣበት
ከበዛው ጫጫታ ከሚሰማው ጩኸት
''ተቀበል!''
...የሚል ድምጽ ይሰማል በድንገት
ተቀበል!
ዘወትር ማለዳ ከቤትሽ ከትሜ
ጠጁን በብርሌ እንዳሻኝ ገትሜ
ስገባ ከቤቴ ከደሳሳው ጎጆ
ሚስቴ ታነባለች ውቢት የኔ ቆንጆ
ስታነባ ሳያት...
ስታነባ ሳያት አንጀቴን ብትበላኝ
ከዛሬ በኋላ ላልጠጣ ወሰንኩኝ
እናም ...
ለሀሳቤ ስምረት ስሚኝ አንዴ ለአፍታ
ኑዛዜዬን እንኪ ጠጁን አርገሽ ገታ
ከዛሬ በኋላ ዘወትር ባልመጣም
አንዳንዴ...
አንዳንዴ ታውሶኝ ግን ማሰቤ አይቀርም
ስለዚህ...
ስለዚህ አንቺ ሰው የምጠጣበትን ያንን ውብ ብርሌ
እኔ ሳልኖር ስቀር እያየሽ አስታውሺኝ
ምንም ብዘገይም ከእለታት አንድ ቀን 'መጣለሁ አካሌ
እያለ ነገራት የውስጡን መብሰልሰል
ጠጁ እና ቀጂዋ
ከበዛ ሕመሙ ያድኑት ይመስል!
ምትኬ ዐስራት
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
BY NY DESIGN
Share with your friend now:
tgoop.com/NY_YC/1169