tgoop.com/NehnuTube/806
Create:
Last Update:
Last Update:
ደስታ ማግኘት ቀላል ነው!
1, እውነትህን ኑር :- እውነትህን ተጋፈጥ አታስመስል ከራስህ አትደበቅ ምንም ቢሆን ልብህ እውነቱን ያውቃል ከላይ ከላይ ላስመስል ልሸውደው ብትልም አይቀበልህም ስለዚህ ደስታህን ይነፍግሀል መደሰት ከፈለክህ የእውነትህን ኑር እውነቱ ከባድ ቢሆንም ተጋፍጠህ ስታሸንፈው የምታገኘውን ደስታ እና እርካታ ማንም አይሰጥህም!
2 , በፍቅር ኑር :- ከሰዎች ጋር ከልብ በሆነ እውነተኛ ፍቅር ኑር ምንም ሳትጠብቅ ፍቅር ስጥ ለሰዎች ሰላም መስጠት የምትችል ሁን ብርቱ ሁን ከልብህ ተቀበላቸው ለመጠንከራቸው ለመሳቃቸው ለማሸነፋቸው ለሰላማቸው ምክንያት ሁን ፍቅር በመስጠትህ ብቻ ህይወቱን የምታተርፍለት አንድ ሰው መኖሩን እወቅ ፤ ሞቅ ያለ ፈገግታህን በማየት ከህይወቱ ጨለማ የሚወጣ የሆነ ሰው አለ ስለዚህ በሄድክበት ሁሉ ፍቅርን የምትሰጥ እና ፈገግታህ ተስፋን የሚፈነጥቅ መሆኑን እወቅ ያኔ ደስታ ሳትጠራው ራሱ ፈልጎህ ይከተልሀል ካንተ ርቆ መሄድ አይችልም!
"እነዚህን ካደረግህ ደስታ ራሱ ካንተ ጋር መሆን ያስደስተዋል "
BY Nehnu Tube ◈ ነህኑ ቲዩብ_||ኢስላማዊ ጥበብ||
Share with your friend now:
tgoop.com/NehnuTube/806