tgoop.com/Noahtoaels_Idea/4418
Last Update:
እስቲ ዛሬ ደግሞ Feb 14 " Valentine's day" በመሆኑ ስለ በዓሉ እና ስላመጣጡ አንዳንድ ነገር ልበላችሁ🤌
💭
.
.ስንቶቻችን ይሆን የቫለንታይን ቀን(የፍቅረኞች ቀን ብለን የምናከብረው) የሚከበርበት ምክንያትና መነሻው የምናውቀው?
ወይስ ሰው ስለ አከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው?
ክርስቶስ ከመወለዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት
አረማዊ ሮማውያን የካቲት 14 ማታና የካቲት 15 "የተኩላ አዳኙ"ለሚሉት ሉፐርኩስ(Lupercus) ክብር በማለት በጣኦት አምልኮ ያከብሩት ነበር።ሮማውያን ይህ በዓል ሉፐርካልያ
(Lupercalia) ይሉታል።ንጉሥ ቆንጠንጢኖስ ክርስትና የሮማውያን ይፋዊ ሃይማኖት መሆኑ በማወጁ ማነኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተወስኑ ሮማውያን ሰዎች ግን በዓሉን ማክበር አልተዉም።ይህንን አረማዊ በዓል
ማለትም ሉፐርካልያ የሮማው ጳጳስ ገላስዮስ ክርስትያናዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር አደረጉ።ጳጳስ ገላስዮስ ለካቲት 15 ሲከበር የነበረው በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን በሚል አዲስ ስያሜ
የካቲት 14 እንዲከበር አደረጉ።
እንዴት ይህ አረማዊ በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የሚል ስያሜ ተሰጠው?
ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው። ቫላንታይን ጥንታዊው ታዋቂው ሉፐርኩስ ነው። ሉፐርኩስ በግሪካውያን ፓን(pan) ተብሎ ይጠራል። በጥንታውያን አይሁድ
ደግሞ ባል(Baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።ባል
በመጽሓፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 10-9 ላይ ታላቁ አዳኝ ተብሎ ለተገለጸው ኒምሮድ ሌላኛው መጠርያው ነው። ኒምሮድ የሮማውያን የተኩላ አዳኙ ሉፐርኩስ ነበር። በዚህ መሠረትም የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የአረማውያን ለኒምሮድ ክብር የሚያከብሩት የጣኦት አምልኮ ነው።
ቫለንታይን የሚል ቃል ቫለንቲኑስ(valentinus) ቫለንስ ከሚል የላቲን ቃል የመጣ ነው።
ቀጥተኛ ትርጉሙ ጠንካራ፣ሃይለኛ ታላቅ ማለት ነው።ዘፍጥረት10-9 ላይ እንደምናነበው " እርሱም በእግዚአብሔር ፊት አዳኝ ነበረ ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር
ፊት ሃያል አዳኝ እንደ ኒምሮድ ተባለ።" ኒምሮድ የሮማውያን ጀግና ሃይለኛ ሰው ቫለንታይን ነበር።
ሌላኛው የኒምሮድ ስም ሳንክቱስ(Sancutus) ወይ ሳንታ (santa) ነው ሳይንት(saint) የሚል የእግሊዝኛ ትርጉምአለው ማለትም ቅዱስ። የሮማውያን ሉፐርካልያ በመጨረሻ ቅዱስ
ቫለንታይን የሚል ስያሜያዘ ማለት ነው።
ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን በቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቀማሉ። በባቢሎናውያን ባል(bal) ልብ የሚል ፍቺ ነው ያለው።በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት
ለቫለንታይን ቀን(የፍቅረኛሞች ቀንየምንለው) መገለጫ እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን የጣኦት ጌታ ነበር። በሌላ መንገድም ኒምሮድ ወይም ቅዱስ ቫለንታይን ሳተርን ተብሎ
ይጠራል።ሳተርን የሮማ-ባቢሎን ከአባራሮዎቹ ለመሸሽ በምስጥራዊ ቦታ የሚደበቅ ጣኦት ነው።ሳተርን የሚል የላቲን ቃል ሴመቲክ(አይሁድ) ቋንቋ ከሚናገሩ ባቢሎናውያን የተገኝ ነው። መደበቅ፣ራስን መደበቅ የሚል ፍቺ አለው።
በጥንታዊ እምነትም ኒምሮድ(ሳተርን) ከአባራሮዎቹ በመሸሽ ወደ ጣልያን እንደተጓዘይነገራል።የአፐኒን ተራራ ስያሜው ወደ ኔምብሮድ ወይም ኒምሮድ ተቀየረ። ይህ ተራራ ኒምሮድ በጣልያን የተሸሸገበት ቦታ ነበር። ሮማም በዚ ተራራ ላይ እንደ
ተመሰረተች ይታወቃል።ሮም ፈርሳ እንደገና ከመሰራትዋ 753 ዓ/ዓ በፊት ሳቹርንያ (ሳተርን፡ኒምሮድ የተደበቀባት ቦታ) የሚል ስያሜ ነበራት። ኒምሮድ በዚህ ቦታ ተይዞበፈጸመው ወንጀል
ተገደለ።በንጉሥ ቆንጠንጦኖስ ጊዜም ክርስትያናዊ ሰማዕት የሚል የውሸት ክብር ተሰጥቶት በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መዘከር ጀመረ። ኒምሮድ፣ባል፣ቫለንታይን፣ታላቁ አዳኝ፣ፋውኑስና
ሉፐርክስ 31ኛ፣32ኛና 33ኛና ደረጃ (ዲግሪ) ላይ ያሉ ፍሪማሶኖሪዎች ከሚያመልኩት ባፎሜት(የሜንደዝ ፍየል) ጋር የሚስተካከል ነው።
እንግዲህ በሰላቢ እጆች (ኢሊሙናቲ) ሴራ ዘመናዊነት ተላብሶ ድብቅ ጣኦት የሚመለክበት የቅዱስ ቫለንታይን ቀን እኛ ደግሞ የፍቅረኛሞች ቀን በማለት እያከበርን ማለትም እያመለክንነው።
አንድ በአል የሚከበርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሊኖረው ግድ ነው። ሆኖም የምናከብረውን በአል የምናከብርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሳናውቅ ከሴረኞች ድብቅ አላማ ማስፈጸምያ ከመሆን መቆጠብ ይበጃል።
🫴ያዉ እድትገነዘቡ ስለፈለኩኝ ነዉ መቅረት ያለበት ነገር ነዉ ብዬ ስላሰብኩኝ!!!
BY ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
Share with your friend now:
tgoop.com/Noahtoaels_Idea/4418