tgoop.com/Orthopiato/1410
Create:
Last Update:
Last Update:
ዜማውን ለማግኘት ከላይ ያለውን forward በመንካት ቻናላችን ይቀላቀሉን
ታብሷል እንባዬ ሸሽቷል መከራዬ
ማርያም ማርያም እያልኩ
ኧረ ስንቱን አለፍኩ፪
።።።።።።።አዝ
እኔስ መስሎኝ ነበር ማይገፍ ቀኑ
ነብሴን ያስጨነቃት ያዘን ወላፈኑ
ማልቀስ ብቻ ሆኖ ዘወትር ስራዬ
አናግርሻለው ሆኜ ለብቻዬ
ድንግል ደረሽልኝ ህልሜን ፈታሽልኝ
አልኩኝ ቀና ቀና ያም ቀን አለፈና
።።።።።።።አዝ
መቆሸሼን አይቶ ከሳሼ ቢከሰኝ
እመአምላክ ግን ምልጃሽ አዲስ አደረገኝ
ነጩን አለበሽኝ ወርቃማውን መፍታ
እንዴት ዘነጋለው ያንችንስ ውለታ፪
።።።።።።አዝ
በቀኙ ባትቆሚ ፀሎቴን ባትሰሚ
አይሰምርም ጉዞዬ ፅልመት ነው ተስፍዬ
።።።።።።አዝ
እንደናት አባብለሽ አሳድገሽኛል
ኑሮዬ ሲጨልም ብርሃን ሆነሽኛል
የተማመንኩበት ሲሸሸኝ ወዳጄ
አንቺ ግን አገኘሽ በጓዳ በደጄ ፪
።።።።።አዝ
አፈራች በለሴ ተደሰተች ነብሴ
ለምን ላቀርቅርህ አሁን ልዘምርህ
።።።።።።አዝ
ትላንት ያዩኝ ሁሉ ዛሬ ይገረማሉ
እንዴት በእግሩ ቆመ እየተባባ
ለሰው የማይቻል ለልጅሽ ተችሏል
እንዳያልፉት የለም ለልጅሽ ተችሏል፪
።።።።።።አዝ
ከቤቴ ማጠፊ ችግሬን ምትቀርፊ
እንዳንቺ ማን አለ ጭንቀቴን የጣለ
ታብሷል እንባዬ...፪
BY የኖህ መርከብ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ቻናል
Share with your friend now:
tgoop.com/Orthopiato/1410