tgoop.com/RvcClub/1275
Last Update:
16/02/2017
ቅዳሜ ምሽቱ ላይ ፀሃይ ቤቷ ከከተመች፤ ጨረቃ ከደመቀች ወዲህ በባለ እንጨት ምሰሶዋ ቤታችን (RVC) ሁላችንም ተገናኘን ።
ዛሬ ከረጅም የትምህርት ረፍት ጊዜ በኋላ ሁለተኛው የአካል ውይይታችን ስለሆነ ሁሉም ሃሳቡን ወዲህ ለማለት ጓጉቷል ።
በተለይ የዛሬው ውይይት ሁላችንም የምናስበው እና አከራካሪ የሆነው "ደስታ ምንድነው?" የሚለው ርዕስ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ውይይቱን አጓጊ አድርጎታል።
ልክ ከምሽቱ 1:20 ውይይቱ ርዕሱን በመረጠው ሰው ንግግር ተጀመረ (ርዕሱ ስለተመረጠለት ደስ እንዳለው ለማወቅ ፈገግ እንዳለ ጀምሮ ፈገግ እንዳለ መጨረሱ ምስክር ነው)።
ድሮስ ከዛ ሁሉ ሃሳብ የሱ በላጭ ሆኖ በዛሬው የመክፈቻ ፕሮግራም መመረጡ እንኳን ፈገግ ሌላስ ቢያስደርገው?)
ደስታ ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ እድል የተሰጣቸው ሰዎች መልሶች ባላሰብኩት መንገድ ጥያቄዎን እንዳሰላስለው አደረገኝ።
"ደስታ ውስጣዊ ስሜት ነው።"( አንዷ የሳይኮሎጂ ተማሪ )…
"ደስታ እና ሃሴት መባልና መከፈል አለበት !"(ሌላ የሳዬኮሎጂ ተማሪ)…
"ደስታ ለእኛ አንጂ እኛ ለደስታ አልተፈጠርምም" (ስሙን ካልየዛዝኩት ዲፓርትመት )
እውን ግን ደስታ ምነድነው?
ለእኔ የውስጥ መረጋጋት፤ የውስጥ ሰላም መሆን የሚሉ መልሶችን አዕምሮዬ ላይ መልሼ ቀና ስል በሃሳብ የሰጠመ ፊት በመወዛገብ የተጨማደደ ፊት ስልካቸው ላይ ያተኩሩ ሰዎች (ልክ እንደኔ ) በማስክ ተሸፍነው የሚያወሩ ቤተሰቦችን ተመለከትኩኝ፤
ሃሳቤን ሰብሰብ አድርጌ ወደ ውይይቱ መለስ ስል ውይይቱ
ከደስታ ምንድነው ጥያቄ እልፍ ብሎ ስለ ዘለቄታዊ እርካታና ጊዜያዌ ደስታ ተሸጋግሯል።
"እርካታ ባርነት ውስጥ የምናገኘው ደስታ ነው" (የጋዜጠኝነት ተማሪ )…
አንድ ጊዜ ሲመቸን ሲስማማን ደስታ ነው ሁሌ ስናደርገው ግን ከፍተኛ ደስታ ከተሰማን እርካታ ነው ።
የሚል ነፀብራቅ ያለው ሃሳብ ተቀበልኩኝ።
ስንት ጊዜ ረክቻለሁ ወይም ተደስቻለሁ ብያለሁ? አንድም ቀን መቼ ረካሁኝ እንዳልኩ፤ መቼ ተደሰትኩ እንዳልኩ ግን አስተውዬ አላውቅም ነበር ፤ሌላ የማሰቢያ ርዐስ አትርፌ ስመለስ ቤታችን ሞልቶ ጥቂት ያልተያዙ ወንበሮች ብቻ ነበሩ የቀሩት ውይ ስናምር እናት ደግሳ ሁሉም ልጅ ሲሰበሰብላት አይነት ስሜት አለው።
ሰዓቱ እየገፋ ከሁለት አለፍ እያለ ነው የቀሩት ጥቂት ባዶ ወንበሮች ሞልተዋል በዛው ልክ ብዙ እንቅልፍ የተጫጫናቸው ፊቶች ከፈግታቸው እየከሰሙ መጥተዋል። ይህን እያስተዋሉ የመጡት አስተናባሪዎችም ውይይቱን ማጠቃለል ጀምረዋል....(አጣደፉት)
ለቀጣዩ የውይይት ሃሳብ መርጠን ብሄራዊ መዝሙራችንን ከልብ በመነጨ ስሜት ዘምረን በወዳጅነት ደንብ ለሳምንቷ ቅዳሜ ተቀጣጥረን ተሰነባበትን።
የሳምንት ሰው ይበለን!!
📝 በማክዳ ጸጋዬ (3ተኛ አመት የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ተማሪ)
ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
BY የምክንያታዊ ባለራዕዎች ስብስብ (RVC)
Share with your friend now:
tgoop.com/RvcClub/1275