tgoop.com/Seidsocial/4089
Last Update:
በህይወቴ አንድንም ብሔር ተሳድቤ አንቋሽሼ አላውቅም። የአንድ ብሔር ሆነ ህዝብም ጥላቻ የለብኝም። በየብሔሩ ያሉ የደም ፖለቲካ ነጋዴዎችንና ጥቅመኞችን ግን እተቻለሁ አወግዛለሁ።
ግና የሁሉም ጠላት ተደርጌ ነው የምሳለው!
በኦሮሞ ህዝብ ስም ተደራጅተው ያሉ ገዳይ አስገዳይ ሌባና ዘራፊዎችን ስተች አንተ የኦሮሞ ጠላት ቀንተህ ነው ጥላቻ ስላለብህ ነው በቃ የማልባለው የለም!
በአማራ ብሔር ስም ያሉትን ጨካኝ ብሔርተኞችና የሌላውን ህዝብ በሀይማኖትና በዘሩ የሚጠሉ ፅንፈኞችን ሳወግዝ " አንተ የኦነግ ተላላኪ የአማራ ጠላት ባንዳ" በቃ የማይደርሰኝ ስድብ የለም !
የትግራይ ወራሪ ሀይሎችን ሳወግዝም እንደዚያው !
ከግንባር እየደወሉ ሁሉ ያስፈራሩኝ ነበር! ስልኬን ከየት እንዳገኙት ሁሉ ይገርመኝ ነበር።
የሆነው ሆኖ እኔ የማንም ህዝብ ጥላቻ የለብኝም። የግፈኞች ሁሉ ጥላቻ ነው ያለብኝ! ለተገፊዎች ደግሞ እስከመጨረሻው ድምፅ ለመሆን ለመሞገት የተቻለኝን አደርጋለሁ። ጥላቻ ሰባኪዎችን እቃወማለሁ!!
በዚህ ፔጅ ላይም ሀሳቤን ትዝብቴን ሳንሸራሸር አንተ የእከሌ ጠላት የሚለኝን አንድም ሰው አላስቀርም ! ሀሳቤን ባልተመረዘ እይታና ጥላቻ የማይረዱኝ ጋር ብቻ እቀጥላለሁኝ 100 ሰው ቢሆኑ እንኳ እነርሱ ለኔ ብዙ ናቸው!!!!
እንኳ የሀገሬ መሻኢኾች በጨካኞች እየተገደሉና የፍልስጤማውያንም ደም እንቅልፍ ይነሳኛል!!
👉 www.tgoop.com/Seidsocial
BY Seid Social

Share with your friend now:
tgoop.com/Seidsocial/4089