SLE_QELBACHN1 Telegram 164
📌ሰይጣንን እና ወንጀሎቻችንን ለማሸነፍ የሚረዱን አምስት ምልከታዎች!

①ኛ―አትዘውትር!

ማለትም ወንጀልን ልማድህ አታድርግ።በየዕለቱ የምታደርገው ነገር አይሁን።
   •• አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ
እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡

አወ! የሕይዎትህን መሰረት ኢስቲቃማ አድርግ።ስህተት መስራትን ደሞ ከመንገድ(እንደመውጣት አድርግ) ልክ እንደተበላሸ መኪና። መኪናህ ሲበላሽ ትቆማለህ፣ ትጠግነዋለህ ከዛም መንገድህን ትቀጥላለህ።

ስለዚህ ወንጀል ስትሠራ ተመልሰህ ወደ ነበርክበት መንገድ ተመለስ። ምክኒያቱም አንድ ሰው ከመንገድ ወጥቶ እየሄደ ጉዞውን ከቀጠለ በመጨረሻ ወዴት እንደሚደርስ አያውቅምና።

ለዚህም ነው አብደሏህ ኢብኑ ዓባስ እንዳሉት፦
"لا صغيرة مع الإصرار"
«(ወንጀል ላይ) ከመዘውተር ጋር ትንሽ የሚባል ወንጀል የለም።» ይላሉ።

ማለትም…አንድ ሰው ትንሽም ወንጀል ቢሆን እዛ ላይ ከዘወተረ ትንሹ ወንጀል እንኳን ትልቅ ይሆናል ማለታቸው ነው።

②ኛ ወንጀልን በይፋ አታድርገው!

አደራህን የሰይጣን ድርጅት ውስጥ ሰራተኛ ከመሆን ተጠንቀቅ።ሰይጣን ሰዎችን ለመበከልና ለማጥመም እራሱን ዳዒ ያደረገ፤ ብዙ ሰዎችንም በድርጅቱ ውስጥ ቀጥሮ ወደ ወንጀል በመጣራት ወይም በግልፅ ወንጀልን በመፈፀም ላይ ተጣሪ አድረጓቸዋል።

ለዛም ሲባል ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- «የኔ ኡመት ሁላቸውም ይቅር ይባላሉ።(ወንጀልን)በ ግልጽ የሰሩትን ሲቀር!» ስለዚህ ወንጀልህን በግልፅ ከመፈፀም ተጠንቀቅ።

ወንጀልን በይፋ የሚሠሩ ሰዎች የሰይጣን አጋር ናቸው። ምክንያቱም ሌሎችንም ወደ ወንጀል ስለሚጋብዙ።

③ኛ ወንጀልን አታብዛ!

ሰይጣን ወንጀልን እንዳትተወው ቢያሸንፍህ እንኳ፤በተቻለህ መጠን ለመቀነስ ሞክር።
ከ ወንጀል መላቀቅ የማትችል ከሆነ ቢያንስ የምትሰራውን ወንጀልን ለመቀነስ ሞክር።

④ኛ― ተውበት እና ኢስቲጝፋር አድርግ!

ወንጀል ላይ ከወደቅክ ቶሎ ብለህ በተውባ እና በ ኢስቱግፋር አጥፋው።የሥራ መዝገቦቻችን እንደ ነጭ ሰሌዳ ነው። ወንጀሎቻቸን ደግሞ በላዩ ላይ በጥቁር ቀለም እንደተፃፉ ፁሁፍ ናቸው።ስለዚህ በሥራ መዝገብህ ላይ በ ወንጀል ጥቁር ቀለም ስትጽፍ እና በኃጢአት ስትበክል ወዲያውኑ በተውበት እና በኢስቲጝፋር አጥፋው። በየጊዜው ወንጀል ስትሠራ ወዳው ተውበትን ማድረግ ተለማመድ።

⑤ኛ― መጥፎውን በመልካም ተካ!

ወንጀልን መተው አለመቻልህ፣በተደጋጋሚ ወንጀል ላይ መውደቅህ ተስፋ እንዳያስቆርጥህ። አንተም በተደጋጋሚ መልካምን ስራ ስራበት። ምክንያቱም መልካም ስራዎች መጥፎ ስራዎችን ያጠፋሉና!

ስለዚህ ወንጀል በሰራህ ቁጥር ከሱ ብኃላ መልካም ስራዎችን አስከትል።ለሰዎች መልካምን መዋል፣ ቁርአን መቅራት፣ዚክር ማድረግ፣ ሰደቃ መስጠት፣የሱና ሶላቶችን መስገድ…መሰል ዒባዳዎችን ፈፅም።

📑ከሸይኽ ሃመደል-ዓቲቅ የቴሌ ግራም ቻናል ተወስዶ ከትንሽ ቃላት ቅያሬ ጋር ወደ አማርኛ የተመለሰ―
=www.tgoop.com/Sle_qelbachn1

tgoop.com/Sle_qelbachn1/164
Create:
Last Update:

BY ስለ ቀልባችን

Share with your friend now:
tgoop.com/Sle_qelbachn1/164

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Some Telegram Channels content management tips To view your bio, click the Menu icon and select “View channel info.” So far, more than a dozen different members have contributed to the group, posting voice notes of themselves screaming, yelling, groaning, and wailing in various pitches and rhythms. Hui said the time period and nature of some offences “overlapped” and thus their prison terms could be served concurrently. The judge ordered Ng to be jailed for a total of six years and six months. For crypto enthusiasts, there was the “gm” app, a self-described “meme app” which only allowed users to greet each other with “gm,” or “good morning,” a common acronym thrown around on Crypto Twitter and Discord. But the gm app was shut down back in September after a hacker reportedly gained access to user data.
from us

Telegram ስለ ቀልባችን
FROM American