tgoop.com/Solualenebiiy/10233
Last Update:
#ከጌታዬ_እዝነት_ተስፋ_አትቁረጡ 💛
ኡለሞች ቁርኣን ላይ ለሙዕሚኖች በጣም ተስፋን ይሰጣል ብለው የሚያስቀምጡት አያህ የአላህን ገፉርነት በግልፅ ያመለክታል።
۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ [ሱረቱል ዙመር :53] 💛
እንዴት ያለ ውብ አያህ እንደሆነ እኮ ቢስሚላህ 💛... አላህ እዚህ ጋር እያናገረ ያለው በነፍሶቻቸው ላይ ድንበር ያለፉ፤ ሐጢያት ውስጥ የተዘፈቁ ባሮቹን ነው። እንደዛም ሆኖ "ያ አዩሐል ሙዝኒቡን" ማለት እየቻለ "ያ ኢባዲ: ባሮቼ ሆይ!" አለ! ... በቃ እኮ ቀጣይ ምን እንደሚል ሳናነብ እንኳን የውስጥ ሰላማችንን እናገኛለን። "ባሮቼ ሆይ! የሰራሁት ወንጀል ብዙ ነው ጌታዬ አይምረኝም ብላቹ ተስፋ አትቁረጡ! እኔ ሐጢያትን በሙሉ እምራለሁ! ምክንያቱም እኔ አል ገፉር ነኝ! እኔ አል ረሒም ነኝ።" ይለናል ጌታችን 💛
ኢብኑል ቀዩም ራህመቱላህ አለይህ "ለምንድነው ሁል ጊዜ አልገፉርና አልረሒም በሚለው ጥምረት ላይ አል ገፉር ከአልረሒም ቀድሞ የሚመጣው?" ብለው ይጠይቁና እራሳቸው ይመልሳሉ። ምክንያቱም ይላሉ:
"لأن المغفرة سلامة والرحمة غنيمة"
"መግፊራ ሰላም ነው(ከጭንቅ ነፃ ያደርጋል፤ እረፍት ይሰጣል)፤ ራህማ ደግሞ ተጨማሪ ጉርሻ ነው። ተጨማሪ ደስታ ነው።" ይላሉ! አንድ ሰው መጀመሪያ የአላህን ምህረት አግኝቶ ሰላሙን ከመለስ በኃላ ነው የእዝነቱን(የራህማውን) ፍሬ የሚያጣጥመው። ❤️🩹
ስለዚህ እኛ እንዴት የአላህን ምህረት እናግኝ ስንል እርሱ ሐዲሰል ቁድስ ላይ ያስቀመጣቸውን መንገዶች መከተል ነው!
•አንደኛ: "يابن آدم ، إنك ما دعوتني" በማለት የገለፀው! ሐጢያቶቻችን ምንም ያህል ቢገዝፉ እሱንና እሱን ብቻ መጥራት!
•ሁለተኛ: አላህን መጠየቅ!
ورجوتني غفرت لك على ما كان منك ولا أبالي
"ከእኔ ዘንድ እስከጠየቅህ ድረስ ለሰራኸው ድርጊት ይቅር እልሃለሁ! አልቀየምም።" ይላል 🥹
•ሶስተኛው: አላህ ላይ አለማጋራት
"يا ابن آدم ، إنك لو أتيتني بقراب الأرض خطايا ، ثم لقيتني لا تشرك بي شيئا ، لأتيتك بقرابها مغفرة"
"የአደም ልጅ ሆይ! የመሬቱን ያህል የሚተልቅ ኃጢያቶች ጋር ወደኔ ብትመጣና ከዚያም ለእኔ አንድ ሸሪክ ሳተበጅልኝ ፊቴ ከቀረብክ ከወንጀልህ የሚተልቅ ይቅርታ አጎናፅፍሃለሁ።" ይላል ሱብሓነላህ ጌታዬ 💛
አላህ ይህንን ሁሉ እድሎችን አመቻችቶልን የእሱን ምሕረት አለማግኘት ግን ከባድ ኪሳራ ነው። አላህ መሓሪ ጌታ ቢሆንም ምህረት የማያደርግላቸው ሰዎችም አሉ! ረሱለላህ ﷺ በአንድ ሐዲሳቸው ላይ: "አላህ ሁሉንም ሰው ይምራል፤ ማታ የሰራውን እና ጌታው የሸሸገለትን ጠዋት ላይ 'ሙጃሃራ' ከሚያደርግ ሰው በስተቀር።" አሉ ሰሐቦችም "ሙጃሃራ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ፤ ሸፊዒም: "አላህ የሸፈነለትን ወንጀል ያለምንም ሀፍረት ግልፅ የሚያወጣ ሰው አሉ።" አላህ ይህንን አይነቱን ሰው አይምርም አሉ! አላህ ይጠብቀን!
የሁሉም ችግር መፍትሔ ደግሞ ኢስቲግፋር ማብዛት ነው! የጌታችንን መግፊራ በተደጋጋሚ መጠየቅ! ረሱሊ ﷺ በአንድ ሀዲሳቸው ላይ ኢስቲግፋር የሚያበዛ ሰው የሚኖረውን ትሩፋት በዚህ መልክ ገልፀውታል:
"አንድ በቋሚነት ኢስቲግፋር የሚል ሰው በተደጋጋሚ ለሰራው ስራ አላህን ምህረት የሚጠይቅ ሰው ከገባበት ድህነትና መከራ አላህ ያላቅቀዋል፤ ሐዘኖቹም ይገረሰሳሉ። በምትኩ ሐብትና ደስታን ያጎናፅፈዋል! ባላሰበው በኩልና ሁኔታዎች አላህ ሪዝቁን ያፈስበታል፤ መንፈሳዊ ፅናትንም ይለግሰዋል።" ይላሉ! 💛... የአላህን ምህረት መከጀል የእርሱን ምህረት ከማስገኘት ያለፈ አያሌ በረከቶች አሉት! አላህ ያስረዳና
اللهم اغفر لي ذنبي كله دقه وجله وأوله وآخره وعلانيته وسره
#የረጀብ_ሐሳቦች 💛
✨@Solualenebiiy || ★Islamic Post★
BY Islamic Post✨🕋
Share with your friend now:
tgoop.com/Solualenebiiy/10233