tgoop.com/Solualenebiiy/10303
Create:
Last Update:
Last Update:
«ለዚህች ሌት (የሻዕባን አጋማሽ) ትሩፋት አላት ፣ ልዩ የሆነ ምህረትና ልዩ የሆነ የዱዓ ተቀባይነት ይገኝባታል » ኢብኑ ሀጀር አል ሀይተሚ
«የሻዕባን አጋማሽ ሌት ለርሷ ብልጫ አላት ፣ ከሰለፎች በዚህች ሌት የሚሰግዱ ነበሩ ፣ ሌቷን ህያው ለማድረግ በመስጂድ መሳባሰብ ግን አዲስ መጤ ተግባር ነው » ኢብኑ ተይሚያህ
«በዚህች ሌት አንድ ሙእሚን አላህን ለማውሳት እና (ለወንጀል ማህርታን ፣ ለነውር ሲትርን ፣ ለጭንቀት ፈረጃን) ለማግኘት ለዱዓእ እራሱን ነፃ ማድረጉ ተገቢ ነው ። ይህን ተግባሩም በተውባ ሊያስቀድም ይገባል ፣ በዚህች ሌት አላህ አላህ ወደርሱ ለሚመለሱ ፀፀትን ይቀበላል » ኢብኑ ረጀብ አል ሀንበሊ
የተጨነቁ ነፍሶች የተሰበሩ ልቦች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ የአላህ ባሮች ሁሉ የቀልባቸውን መሻት የሚያገኙትባት ሌት አላህ ያድርግልን 🤲
✨@Solualenebiiy || ★Islamic Post★
BY Islamic Post✨🕋
Share with your friend now:
tgoop.com/Solualenebiiy/10303