tgoop.com/SubulAsalam2/2849
Last Update:
🕌━═══════👍👌════════━🕌
🚫#አንገብጋቢ_መልእክት_ሶላትን_ለማይሰግድ🚫
☞ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ፡-
#ሶላት ለማይሰግድ ሰው ሴት ልጅን መዳር ሀራም ነው።
ኒካው ብልሹ የሆነ የኒካህ አይነት ነው ፡፡ ይህ ኒካህ እሷን ሀላል አያደርግለትም፡፡ ምክኒያቱም ሶላት የማይሰግድ ሰው ካፊር (ካሃዲ) ስለሆነ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል " በሰውየው እና በክህደት መካከል ያለው ሶላትን መተው (አለመስገድ) ብቻ ነው ፡፡
ምንጭ፡- መናሩል ኢስላም (127/1)
☞ #ኢብኑ_ዑሰይሚን_እንዲህ_አሉ፡-
- ሚስትህ እንድትሰግድ መክረሀት የማትሰግድ ከሆነ እሷ ካፊር (ካሃዲ) ናት፡፡ ከኢስላም የወጣች ነች፡፡ ለአንተም አብራህ ልትኖር አይፈቀድልህም፡፡ ይልቁንስ እሷን ልትለያያት ይገባል (ዋጂብ) ግዴታ ነው፡፡ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በቁርአን እንዲህ ይላል። የካሃዲያን ሴቶችን ቃል ኪዳን አትያዙ። (ምዕራፍ፡ ሙምተሂናህ) ምንጭ፡- መናሩል ኢስላም (135/1)
☞#ኢብኑ_ዑሰይሚን_እንዲህ_አሉ፡-
- ከቤተሰቡ አባል አንድ ሶላት የማይሰግድን ግለሰብ ያወቀ ሰው ዝም አይበል፡፡ ሶላት እንዲሰግድ ይዘዘው። አልሰግድም ካለ ይምታው። ይህ ሁሉ መፍትሄ ካላመጣ ለበላይ ለሚመለከተው የህግ አካል ያስተላልፍ፡፡ ሶላትን የተወ ሰው ካፊር (ካሃዲ)ነው፡፡ በጀሃነም እሳት ውስጥም ለዘላለም ዘውታሪ ነው፡፡ ሲሞት አስክሬኑ ላይ አይሰገድበትም። ከሙስሊሞች መቃብር ቦታም አይቀበርም።።። ምንጭ፡- መናሩል ኢስላም (123/1)
ወቅቱን ጠብቀው ከሚሰግዱት አላህ ያድርገን👏👏
BY || ሱቡል አል-ሰላም ||
Share with your friend now:
tgoop.com/SubulAsalam2/2849