tgoop.com/SubulAsalam2/2878
Create:
Last Update:
Last Update:
ሁሉም በጭንቀት በተዋጠበት አስፈሪ ቀን ፍጥረት ሁሉ አንድ ሳይቀር ሁሉም ነቢያትን አንድ በአንድ ምልጃ ይጠይቃሉ። ነቢያት ምክንያታቸውን እየጠቀሱ «ነፍሴን! ነፍሴን!» ይላሉ።…
:
ከዚያም የመርየም ልጅ ዒሳ ﷺ «ሙሐመድ ዘንድ ሂዱ!» ይላሉ።
ሰዎች ሰዪዲ ሙሐመድ ﷺ ዘንድ ይሄዳሉ።
«ሙሐመድ ሆይ አንቱ የአላህ መልክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነዎት። አላህ ያለፈውንም ሆነ የሚመጣውን ኃጢኣት ምሮልኋል። ጌታዎ ዘንድ አማልዱን። ያለንበትን ጭንቀት አይመለከቱምን?» ይላሉ።
:
ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ከዐርሽ ስር እመጣና ለጌታዬ የሰገድኩ ስሆን እወድቃለሁ። ከዚያም አላህ ለማንም ያልከፈተውን የምስጋና እና የውዳሴ ዓይነት ይከፍትልኛል።»…
እንዲህም እባላለሁ: ‐
«ሙሐመድ ሆይ!
ራስህን አንሳ። ጠይቅ ይሰጥሃል። አማልድ ትሰማለህ!»
ከሰገድኩበት እነሳና «ኡመቴን! ኡመቴን!» እላለሁ።
ቡኻሪ ዘግበውታል
:
ያ ረቢ ሸፈዐውን!
🌹. http://www.tgoop.com/Muslim_negn
🌻. http://www.tgoop.com/Muslim_negn
BY || ሱቡል አል-ሰላም ||
Share with your friend now:
tgoop.com/SubulAsalam2/2878