#ፋይዳ
ስለ " ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጥያቄ አለዎት ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰብ አባላቱ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች ይደርሱታል።
በዚህም የሚነሱ ጥያቄዎችን በቀጥታ እንዲመልሱ የሚመለከታቸው አካላትን ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምላሽ እሰጣለሁ በማለት ማረጋገጫ ልኳል።
ቤተሰቦቻችን በ "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ላይ ያላችሁን ጥያቄ ከዛሬ ጀምሮ ባሉ ሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በ @tikvahmagbot ላይ መላክ ትችላላችሁ።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine

ወጣት ዲፕሎማቶች ለምን የሉንም ?
ኢትዮጵያ በዓለም-አቀፍ መድረኮች የሚወክሏትን ወጣት ዲፕሎማቶች ለምን አጣች? አልፎ አልፎስ የምናያቸው ወጣቶች ቶሎ ከእይታችን የሚጠፉበት ምክንያት ምንድነው?
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ደምሰው ሽፈራው ወጣት ዲፕሎማቶችን እንዲሁም በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ሰዎችን በማነጋገር የተለያዩ ሐሳቦችን አንስቷል።
በዚህ ጹሑፍ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እንዲሁም በምትወከልባቸው ዓለማቀፍ ተቋማት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ወጣት ማየት ከባድ መሆኑ ተነስቷል።
በመንግስት በኩል በተለይም በዲፕሎማሲው ዘርፍ ከወጣቱ ጋር ተቀራርቦ መስራት እና ዕድሉን በማመቻቸት በኩል ፍላጎት አለመኖር እንደ ችግር የተጠቀሰ ሲሆን እድሉን መንግስት ሊፈጥር እንደሚገባም ምክረ-ኃሳብ ቀርቧል።
በተለይ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በኤምባሲዎች ውስጥ ወጣቶች እየሄዱ የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ የማመቻቸት ስልጣኑ እንዳለው ተጠቁሟል።
ሙሉ ጹሑፉን እንድታነቡት እንጋብዛለን https://www.concepthub.net/article/9

በሆሳዕና ከተማ እንጀራ ላይ ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለገበያ ሲያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ።
በሀድያ ዞን በሆሳዕና ከተማ እንጀራ ላይ ጄሶ፣ ሳጋቱራ እና ሌሎች ነገሮችን ቀላቅለው ለገበያ ሲያቀርቡ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ተከተል ዶባሞ እንጀራን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለገበያ ሲያቀርቡ የተገኙ 19 ቤቶች ሲታሸጉ 38 ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል።
ሀድያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከነዚህ ነጋዴዎች ደረቅ እንጀራ በ20 ብር ገዝተው ይጠቀሙ እንደነበር ገልጸዋል።
እንጀራ ላይ ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለማህበረሰቡ ሲያቀርቡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ወጣት ኤፍሬም መንግስቱ በሆሳዕና ከተማ ቦቢቾ ቀበሌ ለ7 ወራት ይህን ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግሮ በቀን ከ170 በላይ እንጀራ ለተጠቃሚ እያቀረበ መቆየቱን ገልጿል።
Source : HTV

የ7፣ 9 እና 12 ህጻናትን የደፈሩ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው 18፣ 17 እና 14 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።
የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ "አጫጭር የችሎት ዜና" በሚል በሦስት ህጻናት ላይ የደረሰ አስገድዶ መድፈር ወንጀልና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን መረጃ አቅርቧል።
🔴 የ12 ዓመት ህጻን በተደጋጋሚ የደፈረው ተከሳሽ
ተከሳሽ ሙሉነህ ኡጋሞ የ37 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የባለቤቱን እህት የሆነችውን የ12 ዓመት ህጻን ከሦስት ዓመት በላይ በቆየ ጊዜውስጥ ለማንም ከተናገርሽ እገልሻለሁ በማለት በማስፈራራት በተደጋጋሚ አስገድዶ እንደደፈራት የክስ መዝገቡ ያስረዳል።
ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ባለቤቱ በወሊድ ምክንያት ታማ ለ2 ወር ሪፌራል ሆስፒታል ከተኛችበት ከቀን 11/04/2013 ዓ.ም. ወንጀሉ እስከታወቀበት 27/05/2016 ዓ.ም. ድረስ መሆኑም ነው የተገለጸው።
የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት #በ14_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
🔴 የወለዳትን የ9 ዓመት ልጁን የደፈረ ወላጅ አባት
ተከሳሽ አዶኒያስ አቡታ 40 ዓመቱ ሲሆን የ9 ዓመት ህጻን ልጁን በቀን 07/07/2016 ዓ.ም.ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከቤተሰቦቹ ጋር ተከራይቶ በሚኖርበቴ ቤት ውስጥ አስገድዶ መድፈሩን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።
ተከሳሹ ድርጊቱን የተበዳይ እናት ቤተሰቧን ለማስተዳደር በከፈተችው የቁርሳ ቁርስ ቤት ውስጥ ለማደር በሄደችበት ዕለት የፈጸመ ሲሆን ተጎጂ ህጻን ተኝታ ካለችበት ቀስቅሶ አስገድዶ መድፈሩ ነው የተጠቀሰው።
የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት #በ17_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
🔴 የ7 ዓመት ህጻን ለአንድ ዓመት አስገድዶ የደፈረው የአከራይ ልጅ
31 ዓመቱ ከሳሽ ልደቱ አስፋ የ7 ዓመት ህጻን ከቀን 01/01/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ አመት ያህል የተለያ ማባበያዎችን በመስጠት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።
የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው በህጻናት ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት #በ18_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

Forwarded from HaHuJobs (HahuJobs)
በስራ ፍለጋ ላይ ኖት? ወይስ ለመቅጠር አስበው ብቁ ባለሞያ ለማግኘት ተቸግረዋል?
እኛ ጋር መፍትሄ አይጠፋም HaHuJobsን አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
HaHuJobs ለሀገር ልጅ በሀገር ልጅ!
@hahujobs | @hahujobs_bot
እኛ ጋር መፍትሄ አይጠፋም HaHuJobsን አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
HaHuJobs ለሀገር ልጅ በሀገር ልጅ!
@hahujobs | @hahujobs_bot
ዘም ዘም ባንክ ሸሪዓን መሰረት ያደረገ "አንሳር" የተባለ የዲጅታል ፋይናንስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ።
ዘም ዘም ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውንና በሙሉ ሸሪዓን መሰረት ያደረገ "አንሳር" የተባለ የዲጅታል ፋይናንስ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ይህንን መተግበሪያ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ላይ አስመርቋል።
በዚህ ወቅት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ መሊካ በድሪ በሀገራችን ከተለመደው የፋይናንስ አሰጣጥ ተገልለው ለቆዮ በተለይም በአነስተኛ እና መካከለኛ የስራ ዘርፍ ለተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ለሴቶች መፍትሔ እንሚሆን ገልጸዋል።
"አንሳር የፋይናንስ ተቋማት ዋስትና ሳያስፈልጋቸው ብድር የማግኘት ብቻ ሳይሆን ብድር የሚሰጥበትን ጊዜ ይቀንሳል ነው የተባለው።
አንሳር ሸሪአን መሰረት ያደረገ የፋይናንስ መርሆዎችን እና የዲጂታል ፈጠራ ኃይልን በመጠቀም ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እና እድሎችን በፍትሃዊነት እና በእኩልነት የሚያቀርብ ይሆናል ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የተናገሩት።
በክፊያ የፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ የጎለበተው አንሳር መተግበሪያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያካተተ እና አማራጭ ዳታን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው ተብሏል።
የክፍያ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀያት አብዱልመሊክ መተግበሪያው በኢትዮጵያ ያለውን የወደፊት ፍትሐዊነት እና የፋይናንሺያል አካታችነትን ከማረጋገጡም በላይ ከባንክ አገልግሎት ተገልለው የቆዩ ማህበረሰቦችን በቀላሉ ማገልገል እንደሚቻል ማሳያም ጭምር እንደሆነ በምርቃቱ ወቅት አብራርተዋል።

የ5 ዓመት ህፃን ልጅ የደፈሩ 2 ግለሰቦች ፍርድ ቤቱ በ19 ዓመት እስራት ቀጥቷቸዋል።
በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል።
ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን ተበዳይ የሆነችው የ5 ዓመት ህፃን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት ነው ጥቃቱ የተፈጸመባት።
ጥቃቱን ያደረሱት አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ የዳቦ መጋገሪያ ቤቱ ሰራተኞች ናቸው።
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞቹ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
🔴 3 ዓመት ከ 6 ወር ህጻን መድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
በዚያው ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድቤት #በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
💬 በህጻናት ላይ የሚደርሱ አሰቃቂ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ እየሰማን ነው። ሁኔታው አሁን በምንሰማው ልክ ነው? ወይስ ሁሉም አከባቢ ለህዝብ ያልተገለጠ ብዙ ጥቃት አለ? በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማትስ ምን እየሰሩ ይሆን?ሀሳባችሁን አካፍሉን!
@tikvahethmagazine
በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል።
ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን ተበዳይ የሆነችው የ5 ዓመት ህፃን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት ነው ጥቃቱ የተፈጸመባት።
ጥቃቱን ያደረሱት አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ የዳቦ መጋገሪያ ቤቱ ሰራተኞች ናቸው።
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞቹ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
🔴 3 ዓመት ከ 6 ወር ህጻን መድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
በዚያው ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድቤት #በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from HaHuJobs (HahuJobs)
በስራ ፍለጋ ላይ ኖት? ወይስ ለመቅጠር አስበው ብቁ ባለሞያ ለማግኘት ተቸግረዋል?
እኛ ጋር መፍትሄ አይጠፋም HaHuJobsን አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
HaHuJobs ለሀገር ልጅ በሀገር ልጅ!
@hahujobs | @hahujobs_bot
እኛ ጋር መፍትሄ አይጠፋም HaHuJobsን አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
HaHuJobs ለሀገር ልጅ በሀገር ልጅ!
@hahujobs | @hahujobs_bot
የኢትዮጵያዊያን ኤንዶስኮፒክ እና ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ማህበር ተመስርቷል።
የኢትዮጵያዊያን ኤንዶስኮፒክ እና ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ማህበር (SEELS) በዛሬው ዕለት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ መመስረቱን ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያሳያል።
ማህበሩን የመሰረቱት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ውሰጥ የሚሰሩ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች በጋራ ተሰባስበው እንደሆነ በምስረታው ወቅት ተገልጿል።
በምስታው ላይ የተገኙት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት የሆኑት ዶክተር አንተነህ ምትኩ ማኅበሩ በኢትዮጵያ ለሚደረጉ የቀዶ ጥገና ሕክምናዎች በጎ ተጽእኖ ከፍ ያለ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ለማኅበሩ መመስረት አንበሳውን ድርሻ ከተጫወቱት መካከል ዶክተር ሱራፌል ሙላቱ በበኩቻቸው የቀዶ ጥገና ሐኪሞች በጋራ መሰባሰብ በመጠነኛ ቀዶ ጥገናና በመሳሪያ በመታገዝ የሚደረግን ቀዶ ጥገናን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንደሚያሳድገው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኤንዶስኮፒክ እና ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ማህበር (SEELS) መመስረት አገልግሎቱን ለሚፈልጉ፣ የዚህ ሙያ ባለሙያ መሆን ለሚፈልጉ ሐኪሞች፣ ለኢትዮጵያ የሕክምና እድገት አዲስ በር የከፈተ እና ተስፋ ሰጪ መሆኑም ተገልጿል።
✍ Dr. Zelalem Chimdesa/#TikvahFamily🩵

በልጅነታችን በጨዋታ መልክ የተቀረጹ ትርክቶችና ምሳሌዎች አሁን ባለን የኑሮ ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖራቸው እሙን ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌንሳ እንዳለ በተለይ "እንቆቅልሽ" በተሰኘው የህጻናት ጨዋታ "ሀገር ስጡኝ" የሚለው የጨዋታው ክፍል እንዴት አስተሳሰባችንን እንደቀረጸው ትዳስሳለች።
የጹሑፉ ርዕስ “Hager Situgn”: The Unseen Vaccination of Desire for Others Over Our Own ይሰኛል።
ሙሉ ጹሑፉን እንድታነቡት እንጋብዛችኋለን 👉 https://www.concepthub.net/article/6

TIKVAH-MAGAZINE
ስምንተኛውና የመጨረሻው የይዞታ ማረጋገጫ ሥራ በ337 ቀጠናዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ኤጀንሲው የመጨረሻ ያለውንና 8ኛውን የመሬት ይዞታ የማረጋገጥና የእወጃ መርሐግብር ሊጀመር መሆኑን ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር የሆኑት አቶ ግፋወሰን ደሲሳ በሰጡት…
#እንድታውቁት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ኤጀንሲው የመጨረሻ ያለውንና 8ኛውን የመሬት ይዞታ የማረጋገጥና የእወጃ መርሐግብር በ6 ክፍለ ከተሞች ከታህሳስ 10/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወሳል።
ለመሆኑ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄ በሚቀርብበት ወቅት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ምንድን ናቸው?
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
- ማንነትን የሚገልጽ የታደሰ መታዎቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣
- ፓስፖርት ወይም ፋይዳ መታወቂያ፣
- ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣
- ይዞታው በሊዝ የተገኘ ከሆነ የሊዝ ውል፣
- የፍርድ ቤት ውሳኔ ካለ፣
- ህጋዊ የውል ሰነዶች፦ የውክልና፤ የስጦታ፣ የውርስ፤ የሽያጭ ውል ካሉ መቅረብ ይኖርባቸዋል።

በምን ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ ጹሑፍ ማቅረብ ይፈልጋሉ?
"ሐሳብ አለኝ" የዲጂታል መጽሔት 2ኛ ዕትም የጹሑፍ ማሰባሰብ ሥራ ተጀምሯል።
ለወጣት ጋዜጠኞች፤ በተለያየ የሙያ መስክ ተሰማርተው በሞያቸው ባዳበሩት ክህሎትና እውቀት ለማኅበረሰብ ለውጥ አስተዋጽኦ ማበርከት ለሚፈልጉ ጸሐፊያን አሁን እድሉ ተመቻችቷል።
በምትኖሩበት አከባቢ እንዲሁም ባላችሁበት የዲጂታል ሥነ-ምዳር ብዙ የምትታዘቡት ጉዳይ አለ በየትኛው ላይ ጥናት አድርጋችሁ መጽሐፍ ትፈልጋላችሁ?
ወጣት ጋዜጠኛ፤ የመብት ተሟጋች፤ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ለማኅበረሰብ ንቃተ ህሊና ለምትተጉ ሁሉ መድረኩ ለእናንተም ጭምር ክፍት ነው።
በምርምርና ጥናት ላይ ያላችሁ ወጣት መምህራን፤ ተማሪዎች እንዲሁም ባለሞያዎች ሥራዎቻችሁን የምታቀርቡበት መድረክ ተመቻችቷል።
አሁን ጹሑፍ በማሰባሰብ ሂደት ላይ የምንገኝ ሲሆን በሐሳብ አለኝ የዲጂታል መጽሔት እንዲሁም በ Concepthub.net ላይ ጹሑፋችሁን በመላክ ማሳተም ትችላላችሁ።
🕒 በእስከ ታህሳስ 25 ድረስ የጹሑፉን ዋና ሐሳብ (Abstract) ይላኩ!
👥 በቡድን የሚሳተፉ ይበረታታሉ!
📱 ጹሑፉን ለማስገባት እንዲሁም መረጃ ለመጠየቅ @concepthubeth_bot ይጠቀሙ።
@tikvahethmagazine @Concepthubeth
"ሐሳብ አለኝ" የዲጂታል መጽሔት 2ኛ ዕትም የጹሑፍ ማሰባሰብ ሥራ ተጀምሯል።
ለወጣት ጋዜጠኞች፤ በተለያየ የሙያ መስክ ተሰማርተው በሞያቸው ባዳበሩት ክህሎትና እውቀት ለማኅበረሰብ ለውጥ አስተዋጽኦ ማበርከት ለሚፈልጉ ጸሐፊያን አሁን እድሉ ተመቻችቷል።
በምትኖሩበት አከባቢ እንዲሁም ባላችሁበት የዲጂታል ሥነ-ምዳር ብዙ የምትታዘቡት ጉዳይ አለ በየትኛው ላይ ጥናት አድርጋችሁ መጽሐፍ ትፈልጋላችሁ?
ወጣት ጋዜጠኛ፤ የመብት ተሟጋች፤ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ለማኅበረሰብ ንቃተ ህሊና ለምትተጉ ሁሉ መድረኩ ለእናንተም ጭምር ክፍት ነው።
በምርምርና ጥናት ላይ ያላችሁ ወጣት መምህራን፤ ተማሪዎች እንዲሁም ባለሞያዎች ሥራዎቻችሁን የምታቀርቡበት መድረክ ተመቻችቷል።
አሁን ጹሑፍ በማሰባሰብ ሂደት ላይ የምንገኝ ሲሆን በሐሳብ አለኝ የዲጂታል መጽሔት እንዲሁም በ Concepthub.net ላይ ጹሑፋችሁን በመላክ ማሳተም ትችላላችሁ።
👥 በቡድን የሚሳተፉ ይበረታታሉ!
@tikvahethmagazine @Concepthubeth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Earthquake : ዛሬ ምሽትም 4:17 ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
💬 በእናንተስ አከባቢ ? አከባቢውን፤ መጠኑንና ሁኔታውን እየጠቀሳችሁ ይጻፉልን!
@tikvahethmagazine
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM