tgoop.com/TonatorTheTewahedo/1182
Last Update:
@TonatorTheTewahedo
🕐 ታህሳስ 10/04/2013 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
👉 ዲያቆን
📖 1 ቆሮ. 9፥1 .....
👉 ንፍቅ ዲያቆን
📖 የሐዋ . 2፥20 .....
👉 ንፍቅ ካህን
📖 ግብረ ሐዋርያት 20÷16 ....
👉 ምስባክ
📖መዝ 138/139፥14
----------------
ወተወከፍከኒ ከመ አእምር እገኒ ለከ እግዚኦ እስመ ግሩመ ተሰባሕከ መንክር ግብርከ ወነፍስየ ትጤይቆ ጥቀ
ትርጉም
-------------
"ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።"
📖 ወንጌል
የማቴዎስ ወንጌል 6÷4
---------------------
አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል ፤ ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል ፤ አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል፤ አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ ፤ ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና ፤ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን ፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን ፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን ፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
📖 ቅዳሴ
ግሩም
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥💚@TonatorTheTewahedo💚✥
✥💛@TonatorTheTewahedo💛✥
✥❤@TonatorTheTewahedo❤✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
BY ቶኔቶር ዘ ተዋህዶ
Share with your friend now:
tgoop.com/TonatorTheTewahedo/1182