tgoop.com/Venisiya21/52
Last Update:
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
🌱🌱🌱 ችግኟ 🌱🌱🌱🌱
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ችግኝ ተተክሎ ዛፍ እንደሚሆን እንጂ ችግኝን እንዴት እንደሚንከባከቡት በውል የማያውቀው ሕጻን የተከላትን የዛፍ ችግኝ ለማየት ጠዋት ይወጣና ውኃ ካጠጣት በኋላ አጠገቡ ቁጭ ብሎ ሲያያት ውሎ ሲያያት ያመሻል።
እንዲህ የመጨነቁና የመጠበቡ ምስጢር ደግሞ አባቱ ይኽቺን ችግኝ ተክለህና አጽድቀህ ጠብቀኝ ብሎት ለሥራ ወደ ክፍለ ሃገር ስለሄደ ነበር። እናት የልጇን እንግዳ ነገር ስለለመደችው የት ዋልክ እያለች አታስጨንቀውም። ብቻ ጀምበሯ ማዘቅዘቅ ስትጀምር ልጇን ለእራትና ለመኝታ ትጠራዋለች ።
ይኸ እየሆነ ሳለ በእግዚአብሔር ቸርነት ችግኟ ጸደቀች፣ አባትም ከሄደበት አገር በሰላም ተመለሰና ለልጁ አደራ ሰጥቶት የሄደው የችግኟ ነገር ከምን እንደደረሰ ለማወቅ ሽቶ "ችግኝህ እንዴት ሆነች? የእኔ ጎበዝ? ሲል ጥያቄ አቀረበ።
ገና ከጅማሬው የችግኝን ጠባይ ያልተረዳው የዋሑ ሕጻን ፊቱ በደስታ እየፈካ አባቱ የሰጠውን ኃላፊነት በሚገባ እንደተወጣ ለማሳየት " ቆይ ላሳይህ" አለና ወደ ውጪ በረረ።
አባት ለነገሩ ትኩረት ሳይሰጠው ከባለቤቱ ጋር ወግ ይዞ እያለ ሕጻኑ በፍጥነት ተመልሶ " ይኸው አባዬ ችግኟ ጸድቃለች" አለ ችግኟን ነቅሎ አምጥቶ ለአባቱ እያሳየ። ያልታደለች ችግኝ።
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
ሁሌም ቢሆን አንድን ሥራ ለምን እንደምንሠራው ምክንያቱን፣ ለማን እንደምንሰራው ባለቤቱን ማወቅ ይኖርብናል። ይህ ደግሞ ስራችን በገዛ ራሳችን እንዳይበላሽና በሥራችን ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል። በተጨማሪም ሥራችንን እናከብረውና እንጠብቀው ዘንድ ያግዘናል።
ይኽ አጭር ታሪክን የሚጠቁመን ይህንኑ ነው በተለይም ችግኟን እንደነቀለው እንደዚህ አላዋቂ ህጻን ማተባችንን የቆረጥን (የበጠስን) ነጠላችንን የጣልን በአጠቃላይ የምንሠራው የጠፋብን ካለን ልብ በሉ ይለናል።
╭══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╮
@Venisiya21 @Venisiya21
╰══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╯
BY ቬኒሲያ
Share with your friend now:
tgoop.com/Venisiya21/52