tgoop.com/Wahidcom/2777
Last Update:
መካህ እና መዲናህ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
9፥28 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَـٰذَا
“መካህ” مَـكَّـة ወይም “በካህ” بَكَّة አምላካችን አሏህ የማለበት እና ጸጥተኛ አገር ነው፦
90፥1 *”በዚህ አገር እምላለሁ”*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ
95፥3 *”በዚህ በጸጥተኛው አገርም እምላለሁ”*፡፡ وَهَـٰذَا الْبَلَدِ الْأَمِينِ
ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በዚህ አገር ውስጥ ይገኛል፥ ይህም የአሏህ ቤት "በይቱል ሐረም" بَيْت الْحَرَام ማለትም "የተቀደሰው ቤት" ወይም "የተከበረው ቤት" ይባላል፦
3፥96 *"ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው"*፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ
5፥97 *"ከዕባን የተከበረውን ቤት፣ ክልክል የኾነውንም ወር፣ መስዋዕቱን እና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ"*፡፡ جَعَلَ اللَّهُ الْكَعْبَةَ الْبَيْتَ الْحَرَامَ قِيَامًا لِّلنَّاسِ وَالشَّهْرَ الْحَرَامَ وَالْهَدْيَ وَالْقَلَائِدَ
የዚህን ቤት መሠረት የጣለው ኢብራሂም ነው፥ ይህ ቤት ያለበትን አገር የቀደሰውም እርሱ ነው። ልክ ነቢያችን"ﷺ" መዲናን ለመሥጂድ እንደቀደሱት ኢብራሂም መካህን ለመሥጂዱል ሐረም ቀድሶታል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው"*። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ
"ሐረምቱ" حَرَّمْتُ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ሐረመ" حَرَّمَ ማለት "ቀደሰ" ወይም "አከበረ" ማለት ነው፥ ይህ መካህ የሚገኘው መሥጂድ እራሱ "መሥጂዱል ሐረም” مَسْجِد الْحَرَام ማለትም “የተቀደሰው መሥጂድ” ወይም "የተከበረው መሥጂድ" ይባላል፦
9፥28 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَـٰذَا
"ነጀሥ" نَجَس የሚለው ቃል "ነጂሠ" نَجِسَ ማለትም "ረከሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ርኩስ" ማለት ነው፥ መካህ እና መዲና የተቀደሱ ሥፍራዎች ስለሆኑ በሺርክ የተነጃጀሡ ሙሽሪኮች ወደ እዛ እንዳይቀርቡ አምላካችን አሏህ፦ "የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ" በማለት ነግሮናል። ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ" በሐዲስ ላይ ከእነዚህ ስፍራዎች ክርስቲያን እና አይሁድ እንዲወጡ አዘዋል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 69
ዑመር ኢብኑ ኸጧብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ብኖር ኢንሻሏህ አይሁድ እና ክርስቲያንን ከዐረቢያ ባሕረ-ገብ አስወጣለው"*። عَنْ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " لَئِنْ عِشْتُ إِنْ شَاءَ اللَّهُ لأُخْرِجَنَّ الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى مِنْ جَزِيرَةِ الْعَرَبِ "
"ጀዚራህ" جَزِيرَة ማለት "ባሕረ-ገብ" ማለት ሲሆን ይህም የዐረቢያ ባሕረ-ገብ በነቢያችን"ﷺ" ጊዜ እና በቀደምት ሠለፎች ጊዜ 180,000 km2 የሆነውን መካህን እና መዲህናን የሚያመለክት ብቻ ነው። ሚሽነሪዎች ግን በዘመናችን ያሉትን 3,237,500 km2 የያዘውን የዐረቢያ "ባሕረ-ገብ"Peninsula" ባህሬንን፣ ጆርዳንን፣ ኩዌትን፣ ኦማንን፣ ኳታርን፣ የመንን፣ ሠዑዲይን፣ ኢማራትን በማመልከት ከዐረቢያ ምድር አህሉል ኪታብ እንዲወጡ እንደታዘዘ ይናገራሉ፥ ቅሉ ግን "ጀዚራቱል ዐረብ" جَزِيرَة الْعَرَب የተባለው "አል-ሒጃዝ" ٱلْحِجَاز ነው። "ሒጃዝ" حِجَاز የሚለው ቃል "ሐጀዘ" حَجَزَ ማለትም "ለየ" "ከለለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተለየ" "የተከለለ" ማለት ነው፥ መካህ እና መዲናህ የተቀደሱ ሥፍራዎች በመሆን ተለይተዋል፤ ተከልለዋል። ከላይ ያለውን ሐዲስ የተረከልን ዑመር ኢብኑ ኸጧብ እራሱ አይሁድ እና ክርስቲያን ከአል-ሒጃዝ ምድር አስወጥቷል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 57, ሐዲስ 60
ዑመር ኢብኑ ኸጧብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ዑመር ኢብኑ ኸጧብ አይሁድ እና ክርስቲያን ከአል-ሒጃዝ ምድር አስወጣ"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما أَنَّ عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ، أَجْلَى الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى مِنْ أَرْضِ الْحِجَازِ
BY ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Share with your friend now:
tgoop.com/Wahidcom/2777