tgoop.com/Wahidcom/2812
Last Update:
በተመሳሳይ ወደ ሰዎች ስንመጣ የያዕቆብ ልጆች ስምዖን እና ሌዊ እኅታቸው ዲና በመደፈሯ ሰይፋቸውን ይዘው ወንዱንም ሁሉ ገደለው እና ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፦
ዘፍጥረት 34፥25-26 *"የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖን እና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ፥ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ። ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ"*።
ፈጣሪ ለያዕቆብ ልጆች፦ "የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፣ ከተማይቱን በእርስዋም ያለውን ሁሉ፣ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ" ብሏቸዋል፥ እነርሱም በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፣ ወንዱንና ሴቱን፣ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፣ በሬውንም በጉንም አህያውንም በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ፦
ዘዳግም 13፥15 *"የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ከተማይቱን፥ በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ"*።
ኢያሱ 6፥21 በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
ይህንን የሰይፍ መጽሐፍ ስናብራራ ሚሽነሪዎች፦ "ይህ እኮ በብሉይ ኪዳን እንጂ በአዲስ ኪዳን ስለ ሰይፍ አያወራም" በማለት ባይብሉን ቀጋና አልጋ ለማድረግ ይፈልጋሉ፥ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ፦ "ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ" ብሎ አዘዘዘ፦
ሉቃስ 22፥36 *"እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ"*።
ይህ ለመከላከል የተደረገ የጦር ስልት ሲሆን ከሐዋርያቱ አንዱ በመቸኮል ወደ ማጥቃት ገብቶ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘ እና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው፦
ማቴዎስ 26፥51 *"እነሆም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘ እና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው"*።
በሙሴ ሸሪዓህ የገደለ ይገደል የሚል ነውና ኢየሱስም፦ "ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ" አለው፦
ማቴዎስ 26፥52 ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።
"ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ" ማለት ሰይፍን አንስቶ በሰይፍ ያለ አግባብ የሚገድል እራሱ በሰይፍ ይገደላል ማለት ነው፦
ራእይ 13፥10 *"በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"*።
ልብ አድርግ ራእይ 1፥1-2 ላይ ራእዩ ከእግዚአብሔር ለኢየሱስ ከኢየሱስ ለመልአኩ ከመልአኩ ወደ ዮሐንስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይናገራል፥ ይህ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ላይ ያለ ቃል ነው። ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋልና አንብቡ! አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Share with your friend now:
tgoop.com/Wahidcom/2812