tgoop.com/Wahidcom/2916
Last Update:
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *አስናምን እናመልካለን፥ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ «ይህቺ *”ቅርጻ ቅርጽ”* ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَا هَـٰذِهِ التَّمَاثِيلُ الَّتِي أَنتُمْ لَهَا عَاكِفُونَ
“ቲምሳል” تِمْثَال ማለት “ምስል” “ቅርጽ” ማለት ነው፥ የቲምሳል ብዙ ቁጥር ደግሞ “ተማሲል” تَمَاثِيل ሲሆን “ምስሎች” “ቅርጻ ቅርጽ” ማለት ነው። የአምልኮ ይዘት ያላቸው ማንኛውም ምስል ሆነ ስዕል ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 156
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ምስሎች ወይም ስዕሎች ያለበት ቤት አይገቡም”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ تَمَاثِيلُ أَوْ تَصَاوِيرُ
ስለ ሱራህ በመስኩ ምሁራን ዘንድ ያለው እይታ በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. ለምንም ነገር ሱራህ መጠቀም ሐራም ነው፣
2ኛ. በእጅ የተሠራ እንጂ ልክ እንደ መስታዎት እራሳችንን የሚያሳዩ በካሜራ እና በፊልም የሚታዩ ነገሮች ችግር የላቸውም፣
3ኛ. ለፓስፓርት፣ ለመታወቂያ እና ለሰርተፍኬት ብቻ መጠቀም ይቻላል፣
4ኛ. ለአምልኮ አንጠቀም እንጂ ስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ በራሱ ሥነ-ጥበብ”art” ነው” የሚሉ ናቸው። ለምሳሌ “ፊደል” የሚለው ቃል “ፈደለ” ማለትም “ቀረፀ” ወይም “ጻፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቅርፅ” ወይም “ጽሑፍ” ማለት ነው፥ ፊደል የቃላት ቅርፅ ናቸው። “ሐርፍ” حَرْف የሚለው ቃል እራሱ “ሐረፈ” حَرَفَ ማለትም “ጻፈ” ወይም “ቀረፀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቅርፅ” ወይም “ጽሑፍ” በሚል ይመጣል፥ ቃል በጽሑፍ ወይም በቅርፅ ማስቀመጥን ያመለክታል። አራተኛውን እይታ ለማስደገፍ፦ “ሡለይማን በቤተ-መንግሥቱ ምስሎች አድርጓል፥ እነዚህ ምስሎች ስዕሎች ነበሩ” ይላሉ፦
34፥13 *ከምኩራቦች፣ “ከምስሎችም”፣ እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል*፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 34፥13
ወሱዲይ ከወድሐክን፣ ዐጢይል ዐውፊይ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ *”ምስሎች ማለት ስዕሎች ናቸው”*። فقال عطية العوفي ، والضحاك والسدي : التماثيل : الصور
“ዒሣ የወፍ ቅርፅ እንዲሠራ መፈቀዱ በራሱ “ቅርፅ መቅረፅ በራሱ ችግር የለውም” የሚል አቋም አላቸው። በሱራህ እሳቤ ዙሪያ “አንጡራ መረጃ አላገኘንም” ካላችሁ በአካባቢያችሁ ወደሚገኙት ምሁራን እና ሊሒቃን ጎራ ብላችሁ ጠይቁ! አሏሁ አዕለም።
✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Share with your friend now:
tgoop.com/Wahidcom/2916