tgoop.com/Wahidcom/3850
Last Update:
አርካኑል ኢማን "ዐቀዲይ" عَقَدِيّ ወይም "ዐቃኢዲይ" عَقَائِدِيّ ናቸው፥ "ዐቀዲይ" عَقَدِيّ ወይም "ዐቃኢዲይ" عَقَائِدِيّ ማለት "ዶግማዊ"dogmatic" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ማለት "ከአሏህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن ማለት "እምነት" ማለት ሲሆን የኢማን ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ማለት ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ
"ነፍይ" نَفْي ማለት “ማፍረስ” ማለት ሲሆን ነፍይ “ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ ነው፥ “ኢስባት” إِثْبَات ማለት “ማጽደቅ” ማለት ሲሆን ኢስባት "ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه ነው፦
2፥256 “በጣዖት የሚክድ እና በአሏህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ገመድ በእርግጥ ያዘ”፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا
“ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ በጣዖት መካድ ሲሆን “ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه በአሏህ ማመን ነው፥ ከአርካኑል ኢማን አንዱ የሆነው የመጀመሪያው እና ዋናው "አመንቱ ቢላህ" آمَنْتُ بِاللَّه ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የሚለውን ጠንካራ የአሏህን ገመድ መያዝ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ይባላል፦
3፥103 የአሏህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا
"ያዙ" የሚለው ይሰመርበት! ይህ ገመድ ሰዎች ከጀሀነም እሳት ጉድጋድ አፋፍ ላይ እያሉ ተንጠንጥለው የሚድኑበት ገመድ ነው፦
3፥103 በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا
አርካኑል ኢሥላም "ዐቂዲያህ" عَقِيدِيَّة ወይም "ዐቃዒዲያህ" عَقَائِدِيَّة ናቸው፥ "ዐቂዲያህ" عَقِيدِيَّة ወይም "ዐቃዒዲያህ" عَقَائِدِيَّة ማለት "ዶግማውያን"dogmatism" ማለት ነው። ከአርካኑል ኢሥላም አንዱ የሆነው የመጀመሪያው እና ዋናው "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ነው፥ ሙሉ ሁለንተናውን ለአሏህ የሰጠ ሙሥሊም ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ያዘ፦
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አሏህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ያዘ፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ
እዚህ አንቀጽ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! ስለዚህ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ማለት "ሁለተኛ ወይም ንዑስ የዲን ቅርንጫፍ" ሳይሆን የመጀመሪያ እና ዐቢይ የዲን ቅርንጫፍ ነው፥ "ዐቂዳህ ምንድን ነው? ሲባል "እርሱ ሁለተኛ እና ንዑስ የዲን ቅርንጫፍ ነው" ብሎ ከመናገር በላይ የሚያሳፍር ነገር የለም። አምላካችን አሏህ ፈሣድን ከሚያስፋፉ ኢሕዋኑል ሙፍሢዱን ይጠብቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Share with your friend now:
tgoop.com/Wahidcom/3850