tgoop.com/Wahidcom/3951
Last Update:
ዛሬ ላይ ዐበይት ክርስትና በሚባሉት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ"Eastern Orthodox" እና በጽባሕ ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" ለመላእክት፣ ለነቢያት፣ ለጻድቃን እና ለሰማዕታት "የአክሮት ስግደት" እየተባለ የሚሰገደው ስግደት ጸሎት፣ ልመና፣ ተማጽኖ ስላለበት የአምልኮ ስግደት ነው፥ ምክንያቱም ዱዓእ እራሱ ዒባዳህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "ዱዓእ ዒባዳህ ነው"። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ” إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ” .
"ዱዓእ" دُعَآء የሚለው ቃል “ደዓ” دَعَا ማለትም “ለመነ” “ጠራ” “ጸለየ” “ተማጸነ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልመና” “ጥሪ” “ጸሎት” “ተማጽንዖ” ማለት ነው፥ ከፈጠረን አምላክ ከአሏህ ውጪ "ድረሱልን እርዱን" የሚባሉት ፍጡራን ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም፣ አይሰሙም፣ አያዩም፦
7፥194 እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው ለእናንተ ይመልሱላችሁ። إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
46፥5 እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን ከአሏህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ
በትንሣኤ ቀን አሏህ ከእርሱ ሌላ በዱዓእ የሚያመልኳቸውንም ይሰበስብና እያወቀ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ መልሳቸውም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፦
34፥40 ሁሉንም በሚሰበስባቸው እና ከዚያም ለመላእክቶቹ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَـٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ
34፥41 መላእክቶቹም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ
መላእክት፣ ነቢያት፣ ጻድቃን እና ሰማዕታት በትንሣኤም ቀን ማጋራታቸውን ይክዳሉ፥ ከእነርሱ ስም በስተኃላ አምልኮውን የሚጋሩት ሸያጢን ናቸው።
ክርስቲያኖች ሆይ! "የአክሮት ስግደት" እያላችሁ የምሰግዱት ስግደት ጸሎት፣ ልመና፣ ተማጽኖ ስላለበት የአምልኮ ስግደት ነውና የአምልኮ ሐቅ ገንዘቡ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Share with your friend now:
tgoop.com/Wahidcom/3951