tgoop.com/Wahidcom/3953
Last Update:
እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ነው። የእስር ቤት ዘበኛው ለጳውሎስ እና ለሲላስ ሰግዷል፦
የሐዋርያት ሥራ 16፥29 መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስ እና ከሲላስ ፊት ተደፋ። αἰτήσας δὲ φῶτα εἰσεπήδησεν καὶ ἔντρομος γενόμενος προσέπεσεν τῷ Παύλῳ καὶ Σιλᾷ,
የአክብሮት ስግደት ባይኖር ኖሮ በፊታቸው ሲሰግድ ዝም ይሉት ነበር? ራእይ የፊላድልፍያ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው ሰው እንደሚሰገድለት ይናገራል፦
ራእይ 3፥9 እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት "ይሰግዱ" ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ። ἰδοὺ ποιήσω αὐτοὺς ἵνα ἥξουσιν καὶ προσκυνήσουσιν ἐνώπιον τῶν ποδῶν σου, καὶ γνῶσιν ὅτι ἐγὼ ἠγάπησά σε.
እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω በ King James Version ላይ "worship" ብሎታል፥ "ዎርሺፕ" የሚለው ቃል "ዋጋ"worth" እና "ነት"ship" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ዋጋነት"worthy-ship"፣ "ማክበር" እና "አክብሮት" ማለት ነው። ዮሐንስ ለመልአኩ ሁለት ጊዜ ሰገደለት፦
ራእይ 19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። καὶ ἔπεσα ἔμπροσθεν τῶν ποδῶν αὐτοῦ προσκυνῆσαι αὐτῷ.
ራእይ 22፥8 በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። ἔπεσα προσκυνῆσαι ἔμπροσθεν τῶν ποδῶν τοῦ ἀγγέλου
ሁለት ጊዜ ሰግዶለት ሁለት ጊዜ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፥ ለአምላክ ስገድ" ብሎ አስጠንቅቆታል፥ እንደ ጴጥሮስ ለትህትና ይሆን? አይመስለኝም፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥25 ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት። ጴጥሮስ ግን፦ “ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ፥” ብሎ አስነሣው።
ምናልባት በንያው የአምልኮ ስግደት ሰግዶ ይሆን? አናውቅም። አብርሃም እና ሎጥ ለመላእክት ሰግደዋል፦
ዘፍጥረት 18፥2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ።
ዘፍጥረት 19፥1 ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ።
መላእክት ወደ ሰዎች ሲመጡ እና ሰዎች እርስ በእርስ ሲገናኙ መስገድ የአክብሮት ስግደት ነው፥ ነገር ግን መላእክት እና ሰዎች የችሎታ፣ የዕውቀት፣ የማየት እና የመስማት ውስንነት ስላለባቸው በአካል ሳይገናኙ በገይብ ለእነርሱ መስገድ የአምልኮ ስግደት ነው። በተጨማሪ በላይ በሰማይ ያሉትን የመላእክትን ምስል ሆነ በታች በምድር የሰዎችን ምስል ሠርቶ መስገድ ሆነ ማምለክ የተከለከለ ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም።
ለመላእክት ሆነ ለሰዎች "የአክብሮት ስግደት" እያላችሁ የአምልኮ ስግደት የምትሰግዱ እንዲሁ የተቀረጸ ምስል ለሆኑት ለመስቀል እና ለስዕል የጸጋ ስግደት የምትሰግዱ ቶሎ ብላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ እንደትመለሱ ጥሪያችን ነው። አሏህን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፦
41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Share with your friend now:
tgoop.com/Wahidcom/3953