tgoop.com/Yahyanuhe/3865
Last Update:
መምህር ፈንታሁን ዋቄ በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ከነበሩ ተጽእኗቸው የጎላ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። በጥቅሉ ስሜታዊነት ቢያጠቃውም በማኅበሩና በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ግን ኹነኛ ስትራቴጂስት ነበር። በዘጠናዎቹ በነበረው የተሐድሶ ትግል ውስጥ ማኅበሩ ያሳትማቸው ከነበሩ ጸረ ተሐድሷዊ ጹሁፎች ጀርባ ነበር። ቤተ ክርስቲያኗ ከ50 አመት በፊት ወደነበረው የፖለቲካው የበላይነት መመለስ አለባት ብሎ በጽኑ ከሚሞግቱ ሰዎች መካከል ነበር።
በተለይም ባለፉት ስድስት አመታት ይህንን አቋሙን ሀገር ቤት እያለም ከተሰደደም በኃላ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ቤተ ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በነበራት አደገኛ ኮንፍሮንቴሽን ሳቢያ ይህንን ለመፍጠር የሚያስችለው ግራውንድ ሁሉ በመንግስት እንደተዘጋ ሲረዳ በስተመጨረሻም አሁን ላይ እየተካሄደ ያለውን የትጥቅ ትግል መደገፍ ላይ አተኮረ። በተለያዩ የትግሉ ሚዲያዎች በመቅረብ ሀሳቡን ማካፈል፣ ስልጠናዎችን መስጠት፣ አካሔዶችን መጠቆም "ቋሚ አገልግሎቱ" ሆነ። በህግ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊትም ከሀገር መሰደድ ችሏል። ይህ ሰው አሁን ላይ ነውረኛ ተግባር እየፈጸመ ለሚገኘው "እፎይ" ለተሰኘው ግለሰብ ይፋዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል። ግለሰቡን መደገፍ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ እስልምናን በመስደብ ሳይቀር ከሰሞኑ በተለያዩ የትግል ሚዲያዎች ሀሳቡን ሰጥቷል (ኢንሻአላህ ቀጣይ አቀርባቸዋለሁ)
"መንግስት በጸሎት ሳይሆን በመሳርያ አፈሙዝ ነው የሚወርደውና ታጥቀህ ተዋጋ" ብሎ በይፋ የሚናገረው መምህር ፈንታሁን ዋቄ አንድ እስልምናን በጸያፍ ቃላት በመስደብ ኹከት እንዲፈጠር የሚተጋን ግለሰብ በምን አግባብ ሊደግፈው ይችላል? የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። ተሞክሮ ከከሸፈው የቀድሞ ፕሮጀክት ውስጥ ሌላኛው ክፍል ላለመሆኑ ግን ምንም እርግጠኛ መሆን አይቻልም።
ቪዲዮው፦
https://vm.tiktok.com/ZMBArhptF/
BY የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
Share with your friend now:
tgoop.com/Yahyanuhe/3865