tgoop.com/abdu_rheman_aman/3770
Last Update:
የፅናት ተምሳሌት [ኢማሙ አህመድ]
= = = = = =
ከዕለታት በአንዱ ቀን "ኑጉስ አል-ሙዕተሲም" ኢማሙ አህመድ ወደታሰሩበት እስርቤት ሄደና: እንዴት አደርክ አህመድ? ‹አላቸው› ኢማሙ አህመድም: አል-ሐምዱ ሊላህ "ሰላም አድሬያለሁ" ግን በጣም የሚደንቅ ህልም አይቻለሁ፣ ቁርኣን ሙቶ አጥቤ ገንዤ(ከፍኜ) ሶላተል-ጀናዛን ሰግጄበት ስቀብረው አየሁት ‹አሉት›
(ንጉስ አል-ሙዕተሲም ቁርኣን መኽሉቅ/ፉጡር ነው የሚል ዕምነት ስላለው፣ ኢማሙ አህመድ ነገረ-አሽሙር እየተጠቀሙ ነው።)
ሙዕተሲም ቁጣ በሞላው አንደበት ወየውልህ ያ-አህመድ! ቁርኣን ይሞታልዴ? ወይስ በኔላይ እያሾፍክ ነው? ‹አላቸው› ኢማሙ አህመድም ይሄ (ህልም'ኮ) የናተው ንግግር ነው። ቁርኣን ፉጡር ነው ትላላቹህ፣ ፉጡር ሁላ ደግሞ ሟች ነው ‹አሉት።› ሙዕተሲም ዘወር አለና ኢብኑ አቢ'ዱኣድን ተመለከተው፣
(ኢብኑ አቢ ዱኣድ ማለት: ቁርኣንን ፉጡር ነው ከሚሉ ሰዎች መካከል ግንባር-ቀደም ተጠቃሽ ነው።)
ኢብኑ አቢ'ዱኣድም: ንጉስ ሆይ! ይሄ ሰውዬ "ኢማሙ አህመድ" መገረፍ አለበት፣ ከአለንጋ ውጭ ምንም ነገር አያሰተካክለውም። ‹አለው› ንጉስ አል-ሙዕተሲምም ወደ ኢማሙ አህመድ ጠጋ አለና አህመድ ሆይ! ነፍስህን አትግደል፣ ቁርኣን መኽሉቅ ነው ብለህ እመንልኝ፣ ‹አላቸው› ኢማሙ አህመድም ቁርኣን መኽሉቅ ነው እልልህ ዘንዳ ከቁርኣን ወይም ከሐዲስ መረጃ ስጠኝ ? ‹አሉት›
ሙዕትሲም: በንዴት (ለአለንጋ ገራፊው) እጅህን አሏህ ይቁረጠውና በደንብ አድርገህ ግረፈው! ‹አለው› ገራፊውም የመጀመሪያውን ብትር በኢማሙ አህመድ "ጀርባ" ላይ ሲያሳርፍባቸው፣ ኢማሙ አህመድም " بسم الله " ቢስሚላህ/በአሏህ ስም ‹አሉ› ሁለተኛውን ብትር ሲያሳርፍባቸው፣
" لا حول ولا قوة الا بالله. "
"ችሎታና ብቃት የለም፣ በአሏህ ቢሆን'ጂ" ‹አሉ› ሶስተኛውን ብትር ሲያሳርፍባቸው፣
القرآن كلام الله غير مخلوق
"ቁርኣን የአሏህ ንግግር ነው፣ ፉጡርም አይደለም!። ‹አሉ› የመጨረሻውን ብትር ሲያሳርፍባቸው ፣
فقال: لن يصيبنا إلا ما كتب الله لنا !
" ምንም ነገር አያገኘንም አሏህ የፃፈልን ቢሆንጂ። ‹አሉ›
ከዛም ኢብኑ አቢ'ዱኣድ ወደ ኢማሙ አህመድ ቀረብ አለና፣ አህመድ ሆይ! ከኑጉሱ ቅጣት የሚያድንህን አንዲትን ቃል (ቁርኣን መኽሉቅ ነው) የሚለውን በጆሮዬ ሹክ በለኝ? ‹አሏቸው› ኢማሙ አህመድም: ይልቅ እኔ ሳልሆን አንተ ከአሏህ ቅጣት የሚጠብቅህን (ቁርኣን መኽሉቅ አይደለም) የሚለውን ንግግር በጆሮዬ ሹክ በለኝ? ‹አሉት› ኢብኑ አቢ'ዱኣድም በንዴት ለገራፊው በደንብ አድርገህ ግረፈው!። ‹አለው› ገራፊውም ኢማሙ አህመድ እራሳቸውን ስተው እስከሚወድቁ ድረስ ገረፋቸው!።
📚سير أعلام النبلاء، للذهبي.
✍አብደረህማን አማን: መስከረም 6/2015)
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
BY نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

Share with your friend now:
tgoop.com/abdu_rheman_aman/3770