tgoop.com/abumuazhusenedris/8315
Last Update:
የጥበበኞች ተሞክሮ(ምክር) ለባለ ትዳሮች
=
ከ አፈ_ታሪክ የተወሰደ ተሞክሮ
አንዲት ሴት ለጥበበኛው ሽማግሌ ባሌ ከፋብኝ ፀባዩን ልችለው አልቻልኩም ምን ትመክሩኛለሁ? በማለት ጠየቀየች
ሽማግሌውም የአንበሳ ፀጉር ከነ ሕይዎቱ እያለ ከ ግንባሩ ላይ ነጭተሽ አምጭልኝና የባልሽ ፀባይ እንድስተካከል መድ ኃኒት በፀጉሩ እሰራልሻለሁ አሏት።
ሴትዮዋም ይሄ ለኔ ቀላሌ ነው ብላ ስጋ ነገር በመያዝ ወደ ቤቷ ስር ወደሚገኘው ጫካ በመሄድ ላንበሳው ስጋ መወርወር ጀመረች።
አንበሳውም ገና በርቀት ጥላለት ስትሄድ ሴትዮዋን ማስተዋል ጀመረ ባለውለታውም አደረጋትና ለመዳት
እሷም ቀስ እያለች ወደ አንበሳው እየቀረበች ስጋ መስጠት ጀመረች እሱም ለመዳት ሁሌም ስጋ ይዛለት ስትመጣ ጅራቱን በመቁላት ደስታውን ይገልፅላት ጀመረ
እሷም የአንበሳውን መላመድ ስትረዳ ቀረብችውና ስጋውን በእጇ ሰጠችው እሱም ፀጥ አለ
ከዚያም እያሻሸች ፀጉሩን በምላጭ ቆረጠችውና ወዲያውኑ በደስታ ተውጣ ወደ ሽማግሌው በመሄድ ይሄው የታዘዝኩትን ይዤ መጣሁ መድኃኒቱን ስሩልኝ አለቻቸው
የሚገርመው የሽማግሌው መልስ ነው
"ከዚያ ከከፋ አንበሳ ግንባር ላይ በሕይዎት እያለ አባብለሽ ፀጉር መቁረጥ ከቻልሽ ያንች ባል ካንበሳው ስለ ማይከፋ ባልሽን አባብለሽ መያዝ ነው መድኃኒቱ"አሏት።
www.tgoop.com/abumuazhusenedris
BY አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ)
Share with your friend now:
tgoop.com/abumuazhusenedris/8315