tgoop.com/adwav/10161
Last Update:
ዘንድሮም እንዳምና ካቻምናው የሸዋልኢድ በዓልን ለማክበር ወደ ሀረር ልንጓዝ ነው::
🗓️ ከመጋቢት 26-29 (april 04-07 )
የ 4 ቀናት ጉዞ/የ3 ቀናት አዳር
🔹ባሳለፍነው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት / UNESCO በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የሸዋልኢድ በዓልን ዘንድሮም ከጉዞ ቤተሰቦቻችን ጋር ለማክበር ቀኑ አልደርስ ብሎናል::
እናንተስ ከእኛ ጋር ለመሄድ ዝግጁ ናችሁ?
በዚህ የጉዞ መርሀ ግብር
🔸ከኢድ አልፈጥር በዓል 7 ቀናት በኋላ በሀረሪ ብሄረሰብ ተወላጆች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ተወዳጁ የሸዋልኢድ የአደባባይ በዓልን እንታደማለን።
በጀጎል ግንብ የሚከናወነው ይህ ልዩ ፌስቲቫል በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ታዳሚዎች እና እንግዶች አምረው ደምቀው በሚታዩበት ምሽት ይከበራል።
🔸እንዲሁም በጀጎል ግንብ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የሀረሪን ባህል እና ታሪክ የሚገልፁ ቅርሶች እንጎበኛለን::
🐎 ሌላው የዚህ ጉዞ አጓጊ ክፍል
በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኞቹ የዱር ፈረሶች ወደሚገኙበት ምስራቅ ሀረርጌ የኢትዮዽያ ክፍል በማምራት የቁንዱዶ ተራራ እና የቁንዱዶ የዱር ፈረሶችን እንጎበኛለን::
⛺️ የአንድ ቀን አዳራችንን ከባህር ጠለል በላይ 2,950 ሜ ከፍታ ላይ በማድረግ በቁንዱዶ ተራራ ላይ የማይረሳ ምሽት እናሳልፋለን::
🚂 ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የበርሃዋ ገነት ድሬድዋን ሳንጎበኝ በፍፁም አንመለስም::
ይህን አጓጊ ጉዞ ከእኛ ጋር ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ የስልክ አድራሻዎች በአፋጣኝ ይደውልልን:: ወይንም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላክልን:: @guzoadwahiking @guzoad
+251942545470, +251964423971
እጅግ ውስን ቦታዎች ብቻ ቀርተውናል::
#ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #harar #shewaleid #unescoworldheritage
BY Guzo Adwa updates
Share with your friend now:
tgoop.com/adwav/10161