AMENELECTRICALTECHNOLOGY Telegram 2399
#የፍሪጅ_ጋዝ_እንዴት_እንሞላለን?
#How_to_refilling_refrigerat_gas
=======
👉ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ #የአሜን_ኤሌክትሪካል_ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ለናንተ ይጠቅማል ብየ ያሰብኩትን ይዠላችሁ መጥቻለሁ እናንተም ልክ እኔ ጊዜ ሰጥቸ እንደምፅፍላችሁ ሁሉ እናንተም ለሌሎች ለማድረስ ጊዜ ሰታችሁ #ሼር ስለምታደርጉት ከልብ አመሰግናለሁ።
👉ዛሬ የምናየው የፍሪጅ ጋዝ አሞላል ቅደም ተከተሎችን ሲሆን ከዚህ በፊት ግን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ የተወሰኑ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እጀምራለሁ፦
1. ፍሪጅ መቸ/ለምንድን  ነው ጋዝ የሚሞላው?
2. ፍሪጅ ምን አይነት ጋዝ ነው የሚሞላው?
3. የተሞላ የፍሪጅ ጋዝ ያገልግሎት ማብቂያ(expired date) ምን ያህል ነው?
4. የፍሪጅ ጋዝ ለመሙላት የሚያስፈልጉ ምሳሪያዎች ምን ምን ናቸው።
👉አሁን የፍሪጅ ጋዝ አሞላል ቅደም ተከተል ከማየታችን በፊት እነዚን ጥያቄዎች በመመለስ እንጀምር።
#መልሶች
👉 1. ፍሪጅ ጋዝ የሚሞላው የፍሪጁ ጋዝ ማስተላላፊያ ቱቦ ላይ ጋዝ የሚወጣ ከሆን(leakage) ወይም ቱቦው ተዘግቶ የፍሪጅ ጋዝ እንደፈለገ የማያልፍ ከሆነ(blockage) ጥገና ስለሚፈልግ ከጠገንን በኋላ ደሞ ጋዙ ስለወጣ መሞላት ይኖርበታል።
👉 2. በዙ አይነት ጋዝ ቢኖርም ለፍሪጅ የተለመዱት 2 አይነት ጋዞች ሲሆኑ እነርሱ፦
R-134a (Tetrafluoroethane)
R-600a(Iso Butane) ናቸው። ነገር ግን እነዚን ጋዞች ስንሞላ የፍሪጁ ኮምፕረሰር ወይም ሌላ ክፍል ላይ አምራች ድርጅቱ የለጠፈውን የጋዝ አይነት አይተን መሆን ይኖርበታል።
👉 3. የፍሪጅ ጋዝ ከላይ በተገለፀው መልኩ ካልወጣ ያገልግሎት ዘመኑ አያልፍም። ስለዚህ ፍሪጅ ጥገና ካልተደረገለት በስተቀር ጋዝ መሙላት አስፈላጊ አይደለም ማለት ነው።
👉4. የፍሪጅ ጋዝ ለመሙላት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች/ዕቃዎች የሚከተሉት ናቸው።
ሁሉም ለብየዳ የሚያስፈልጉ መሰሪያዎች የሚያፈስ ወይም የተዘጋ ቱቦ ካለ ቆርጠን ስለምን በይድ ለብየዳ የሚያስፈልጉ መሳሪያውች እንደ የኮፐር መረጫ፣ ኦክስጅን ሲሊንደር፣ ቡቴን ጋዝ ሲሊንደር ፣ መበየጃ ፣ ሆዝ፣ ፓውደር፣ ሲልቨር ወዘተ ያስፈልጉናል።
የፍሪጅ ጋዝ(Refrigerant gas) ፍሪጁ እንዲሰራ የሚሞላ ጋዝ ሲሆን እንደ ፍሪጁ አይነት  R-134a ወይም R-600a ሊሆን ይችላል።
ማንፎልድ ጌጅ የፍሪጃችን ጋዝ ለመሙላትና የግፊት መጠኑን ለማወቅ የምንጠቀምበት መሳሪያ ነው።
ፊልትሮየኮንደንሰር ወደ ኢቫፖሬተር ጋዝ በሚዛዋወር ጊዜ ለማጣራት ይጠቅመናል።
ጋዝ መሙያ ቫልቭ(charging valve) ጋዝ ለመሙላትና የፍሪጁን የጋዝ መጠን ለማወቅ የማንፎልድ ጌጃችን ሰማያዊ ቀለም ያለውን ሆዝ ከኮምፕረሰር የጋዝ መሙያ ጫፍ (charging) ጋር ለማገናኘት ይጠቅመናል።
ናይትሮጅን ጋዝፍሪጃችን ለማፅዳት ይጠቅመናል።
ቫኪዩም ፓንፕ ማሽንጋዝ ከመሙላታችን በፊት ለማፅዳት የምንጠቀምበት ነው ከሌለ ግን በራሱ በፍሪጁ ሲስተም ማፅዳት ስለሚቻል ግዴታ አይደለም።
የተበላሸውን ክፍል(ኮንደንሰር ቱዩብ ፣ ኢቫፖሬተር ቱዩብ፣ ፊልትሮ ወዘተ ) የሚተካ ዕቃ
👉አሁን የሚያስፈልጉንን መሳሪያዎችና ዕቃዎች ካወቅን ወደ ጋዝ መሙላት ቅደም ተከተል እንሄዳለን።
1. በመጀመሪያ ከላይ የዘረዘርናቸውን መሳሪያዎች/ዕቃዎች ካዘጋጀን ባኋላ ፍሪጁ ጋዝ የሚያፈስበትን ወይም የተዘጋበትን ቦታ በጥንቃቄ ከፈለግን በኋላ ቆርጠን አውተን አስፈለጊውን የፓይፕ መጠንና እርዝመት እንበይዳለን።
2.  ጋዝ መሙያ ቫልቩን (charging valve) ከኮምፕረሰሩ የጋዝ መሙያ ጫፍ ጋር መበየድ።
3. የበየድናቸውን ቦታዎች ጋዝ እንደማያፈስ ማረጋገጥ።
4. ፍሪጁ ጋዝ በሚያፈስበት ጊዜ እና ስንበየድ አላስፈላጊ ጋዝ ስለሚገባ የፍሪጁን የውስጥ ክፍል በራስ አገዝ(self Vacum) ወይም ቫኪዩም ፓንፕ ማሽን(Vacum pump machine) ተጠቅመው ማፅዳት።
ሀ.  #በራስ_አገዝ(self Vacum) የማፅዳት ዘዴ
ከካፕላሪ ቱዩብ ትንሽ ክፍል ቆርጠን ከወሰድን በኋላ ፊልትሮውን በኮንደንሰር በኩል እንበሳለን።
ከዛ  ከካፕላሪ ቱዩብ የቆረጥነውን አንደኛውን ጫፍ  በተበሳው የፊልትሮ ቀዳዳ እንከተውና እንበይደዋለን። 
በይደን ከጨረስን በኋላ ምን ያህል ግፊት እንዳለው የማንፈልድ ጌጃችን ሰማያዊ ሆዝ ከኮፕረሰሩ ጋዝ መሙያ ቱዩፕ ጋር አገናኛለን።
ማንፈልድ ጌጃችን እስከ -20 ድረስ እስከሚያነብልን ከጠበቅነው በኋላ ፊልትሮ ላይ በይደነው የነበረውንና ጋዝ ሲወጣበት የነበረውን ካፒላሪ ትዩብ ጫፍ አየር እንዳይገባብን መበየድ።
ለ. #ቫኪዩም_ፓንፕ ማሽን(Vacum pump machine) ተጠቅሞ የማፅዳት ዘዴ
በዚህ ጊዜ ቫኪዩም ፓንፕ ማሽን ያስፈልገናል።
የማንፎልድ ጌጃችን ሰማያዊ ሆዝ(ዝቅተኛ ግፊት) ከኮፕረሰሩ ጋዝ መሙያ ቱዩፕ ጋር አገናኛለን።
የማንፎልድ ጌጃችን ኮመን(ቢጫ ሆዝ) ከቫኪዩም ፓንፕ ማሽን ጋር እናገናኛለን።
ከዛ ቫኪዩም ፓንፕ ማሽኑን ኤሌክትሪክ ሀይል እንሰጠው እና ማንፈልድ ጌጃችን እስከ -20 ሲደርስ ማንፎልድ ጌጃችን  እንዘጋው እና ጋዝ ወደ መሙላት እንሄዳለን።

5. ጋዘ መሙላት
👉ጋዝ ለመሙላት የማንፎልድ ጌጃችን ኮመን(ቢጫ ሆዝ) ከጋዙ ሲሊንደር ጋር አገናኝተን ፍሪጁን የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያገኝ እናደርጋለን።
👉 የጋዙን ሲሊንደርና ማንፎልድ ጌጃችን ከፍተን ከ30-40 ሴኮንድ  ከሞላን በኋላ ማንፎልድ ጌጃችን ዘግተን ለ10 ደቂቃ ያህል ኮምፕረሰሩ እየሰራ እንጠብቃለን። ከ10 ደቂቃ ባኋላ  እንደገና ከ30-40 ሴኮንድ ያህል ማንፎልድ ጌጃችን ከፍተን ከሞላን በኋላ አሁንም መልሰን ለ10 ደቂቃ ገደማ ዘግተነው እንቆያለን።
👉ይህን ሂደት #ኮምፕረሰራችን እስኪሞቅና ኢቫፖሬተራችን እስኪቀዘቅዝ ድረስ(ማንፎልድ ጌጃችን 60psi እስከሚደርስ ድረስ) እንደጋግመዋለን።
👉 አሁን በትክክል ጋዝ መልተን ስራችንን ስላጠናቀቅን አረፍ ይበሉና ይን ፖስት ለግለሰቦችና ለተለያዩ ጉርፖች #ሼር በማድረግ ሌሎችንም ተጠቃሚ ያደርጉ❗️
#እናመሰግናለን❗️
👉#በግል_ወይም_በቡድን_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_በሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል❗️
👇👇👇👇👇
0911585854
0118644716
" #ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
🔹🔸🔹 #ለወዳጅዎም_ያጋሩ!🔸🔹
🔹🔸🔹🔹 #እናመሰግናለን!🔹🔸
👍412😢1🎉1

tgoop.com/amenelectricaltechnology/2399
Create:
Last Update:

BY Amen Institute of Technology Official®

Share with your friend now:
tgoop.com/amenelectricaltechnology/2399

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp. Your posting frequency depends on the topic of your channel. If you have a news channel, it’s OK to publish new content every day (or even every hour). For other industries, stick with 2-3 large posts a week. Other crimes that the SUCK Channel incited under Ng’s watch included using corrosive chemicals to make explosives and causing grievous bodily harm with intent. The court also found Ng responsible for calling on people to assist protesters who clashed violently with police at several universities in November 2019. So far, more than a dozen different members have contributed to the group, posting voice notes of themselves screaming, yelling, groaning, and wailing in various pitches and rhythms. Healing through screaming therapy
from us

Telegram Amen Institute of Technology Official®
FROM American