tgoop.com/andromedainfo/7449
Create:
Last Update:
Last Update:
ደራሲዎች በማህበራዊ መስተጋብር ደካማ ናቸው። አንደኛ ስራቸው ጥልቅ አትኩሮታቸውን ይፈልጋል። ሁሌም ያሉበትን አለም ረስተው በምናብ ይመንናሉ። ደራሲዎች መናኝ ናቸው። ቢያገቡም ቢወልዱም ከሰው ቢቀላቀሉም ብቻቸውን ናቸው። የሰው ሃሳብ አይጥማቸው፤ የነሱ ሃሳብ ለሰው አይጥም።
ኤሚሊ ዲክንሰን የተባለች አውራ የአሜሪካዊ ገጣሚ ከቤቷ ወጥታ አታውቅም፤ ሰዎች ከፈለጓት በሩቁ ሆና ታነጋግራቸዋለች።
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ባሕታዊ ነበር። ከሰው መቀላቀል ያስተማረችው የመጀመሪያ ሚስቱ ሃና ናት።
ዳኛቸው ወርቁ ከቤተሰቡ በቀር ከሌላው ተነጥሎ ለብቻው ዘግቶ የሚኖር ደራሲ ነበር።
መንግስቱ ለማ በደካማ የማህበራዊ ሕይወታቸው የተነሳ ትዳራቸው ፈርሷል። መንግስቱ እቁብ፣ እድር የተባለ ነገር የላቸውም።
ደግሞ ደራሲዎች ብቻ አይደሉም። ሰአሊዎች ፣ ፈላስፋዎች ፣ ሳይንቲስቶች ጭምር።
ለምሳሌ ማይክልአንጀሎ የሲስቲን ቻፕል ጣራ በስእል ሲያስውብ ለአራት አመት ሙሉ ተዘግቶበት ከሰው ዘር ጋር ሳይገናኝ እንደከረመ አንብቤያለሁ።
አይዛክ ኒውተን እና ኒኮላ ቴስላ ከሴት ዘር ጋር ሳይገናኙ ሙሉ ዘመናቸውን በድንግልና ኖረዋል። ኒኮላ ቴስላ የነበረችው ብቸኛ ጓደኛ አንዲት ድመት ነበረች።
(ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው book for all)
ድጋፋችዉን የማዉቀዉ like 👍 ስታደርጉ ነዉ
BY አንድሮሜዳ (Sirnhatty)
Share with your friend now:
tgoop.com/andromedainfo/7449