Notice: file_put_contents(): Write of 8923 bytes failed with errno=28 No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 50

Warning: file_put_contents(): Only 8192 of 17115 bytes written, possibly out of free disk space in /var/www/tgoop/post.php on line 50
ባህረ ጥበባት@bahreTibebat P.855
BAHRETIBEBAT Telegram 855
የአቡነ ጽጌ ድንግል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ግብፃዊው አቡነ ሐራ ድንግል ብዙ ተአምራት የሚደረግበትንና በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ የሚያስቀምጥበትን አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳምን የመሠረቱት ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በ9ኛ መ/ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት ነግሣ አብያተ ክርስቲያናትን ለ40 ዓመታት ያህል ስታጠፋ ግብፃዊው አቡነ ሐራ ድንግል በአክሱምና በታላላቅ ገዳማት የነበሩትን ቅርሶችና ቅዱሳት መጻሕፍት ሰብስበው በአርብ ሐራ መድኃኔዓለም ገዳም ዋሻ ውስጥ አስቀምጠውት ነበር፡፡ በተከታታይም ከግብፅ ሀገር ከገዳመ አስቄጥስ አርባ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሀገራችን መጥተው ከአቡነ ሐራ ድንግል ጋር ተቀምጠው በጾም ጸሎት ተወስነው ብዙ ትሩፋትን ፈጽመዋል፡፡ አቡነ ሐራ ድንግል አንድ ቀን ‹‹ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ዋሻ ውስጥ ለውስጥ የምንፈለፍልበት መሣሪያ ፈልጉና አምጡ›› አሏቸው፡፡ አርባው ቅዱሳንም ወደ ሀገራቸው ግብፅ ተመልሰው ሄደው የዋሻ መፈልፈያ መሣሪያ አምጥተው ለጻድቁ ሰጧቸው፡፡ እርሳቸውም ቅዱሳኑ እየተራዷቸው ውስጥ ለውስጥ 4 ሰዓት የሚያስኬድ አስደናቂ ዋሻ ፈልፍለው በውስጡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ሠሩ፡፡ ከዚያም አቡነ ሐራ ድንግል ቅዱሳኑን ወንጌልን እየተዘዋወሩ ይሰብኩ ዘንድ አሰማሯቸውና እርሳቸው በዋሻው አጠገብ በታላቅ ተጋድሎ በጾም ጸሎት ኖሩ፡፡ ብዙ መናንያንም ወደ እርሳቸው እየመጡ ቡራኬአቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ አቡነ ሐራ ድንግል በእንዲህ ያለ የተጋድሎ ኑሮ ሲኖሩ አንድ ቀን ሠርገኞች ሙሽሮችን አጅበው ሲሄዱ ጻድቁ በሚጸልዩበት አርብ ሐራ በተባለው ገዳም ሲደርሱ ሁለቱ ሙሽሮች ከበቅሎ ላይ ተንከባለው ከዋሻው በር ላይ ወድቀው ሞቱ፡፡ የሙሽሮቹ አጃቢዎችም ከፍተኛ ሀዘን ደረሰባቸው፡፡ አቡነ ሐራ ድንግልም ይህን ሁኔታ አይተው በጸሎታቸው ኃይል የሞቱትን ሙሽሮች አስነሥተው ለሠርገኞቹ አስረከቧቸው፡፡ ሠርገኞቹም ደስታቸው ዕጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ከጻድቁ እግር ሥር ወድቀው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡

ከዚህም በኋላ የጻድቁ ዜና ይበልጥ በሁሉ ዘንድ ተሰማ፡፡ በላስታ የመራ ተክለ ሃይማኖት መንግሥት እንደተጀመረ ዋካ የሚባል ኃይለኛ ሽፍታ አቡነ ሐራ ድንግል ወዳሉበት ዋሻ መጥቶ ‹‹ይህን ዋሻ እፈልገዋለሁና ይልቀቁልኝ›› ብሎ ገና ቃሉ ከአፉ ሲወጣ መብረቅ በድንገት ከሰማይ ወርዶ ከነተከታዮቹ ገድሎ ፈጽሞ አጠፋቸው፡፡ ጻድቁም የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ አይተው አደነቁ፡፡ አስከሬኑንም በወቅቱ የጣለው ጎርፍ ወሰደው፡፡ ሽፍታውም በመንዝ አውራጃ የታወቀና ኃይለኛ ስለነበር በመቅሰፍት መሞቱን ሰዎች ሲሰሙ ተደሰቱ፡፡

በአንድ ወቅትም የመንዙ ገዥ ልጁ ሞቶበት በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሳለ ምእመናን ለገዥው ‹‹በግዛትህ ውስጥ የሚገኙት ጻድቁ አቡነ ሐራ ድንግል የልጅህን አስክሬን ብትወስድላቸው ከሙታን ለይተው ያስነሡልሃል›› ብለው መከሩት፡፡ እርሱም የልጁን አስክሬን አሸክሞ አምጥቶ ከአቡነ ሐራ ድንግል ፊት ጣለውና ‹‹ክቡር አባቴ ሆይ! በተሰጠዎት ሀብተ ጸጋ ልጄን ያድኑልኝ›› ብሎ በግንባሩ ወድቆ ለመናቸው፡፡ ጻድቁም ወደ እግዚአብሔር ጸልየው የሞተውን የገዥውን ልጅ አስነሡለት፡፡ ገዥውና ሕዝቡም ሁሉ በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነገርን የሚያደርግ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ጻድቁንም እጅግ አከበሯቸው፡፡ የሀገሩ ገዥና ምእመናንም ልብስና ገንዘብ እያመጡ ጻድቁ ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች እንዲሆን ሰጧቸው፡፡ ጻድቁም ለተማሪዎቻቸውና ለጦም አዳሪዎች አከፋፍለውታል፡፡አቡነ ሐራ ድንግል ለመንዝ ሕዝብ የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል በሚገባ አስተምረዋል፡፡ በተአምራታቸውም ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል፡፡ ሙታንን አስነሥተዋል፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በ220 ዓመታቸው ጥቅምት 27 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
አቡነ ሐራ ድንግል ከማረፋቸው በፊት በጸሎት ላይ ሳሉ ጌታችን ተገልጦ ብዙ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ዐፅማቸውንም አንድ ቅዱስ መነኩሴ በክብር ገንዞ በዋሻው ውስጥ አስቀምጦታል፡፡ ከግብፅ መጥተው እሳቸውን ሲያገለግሉ የነበሩት አርባው ቅዱሳንም ብዙ ካስተማሩና የትሩፋት ሥራ ሲሠሩ ከኖሩ በኋለ ዐርፈው በዚያው የጻድቁ ዐፅም ባረፈበት ዋሻ በክብር ተቀምጠዋል፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለአቡነ ሐራ ድንግል ከሰጣቸው አስደናቂ ቃልኪዳኖች አንዱ ‹‹…እስከ ዕለተ ምጽዓት ድረስ እኔን አምነው የሚነሡ ቅዱሳን የማረፊያቸው ቦታ ክቡር ዐፅምህ ባለቤት ቦታ ይሁንልህ›› የሚለው ነው፡፡ በዚህም ቃልኪዳን መሠረት እነሆ ከልዩ ልዩ ሥፍራ ነገር ግን ከየት እንደመጣ የማይታወቅ በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ ከአርብ ሐራ መድኃኔዓለም ገዳም ዋሻ ውስጥ ያስቀምጣል፡፡ ነጩ ንስር የቅዱሳንን ዐፅም ሲያመጣ በመጀመሪያ ከዋሻው ውስጥ የሚወጣው ጢስ መዓዛው ከከበረ ሽቱ ይበልጣል፡፡ የዕጣኑም ጢስ ከዋሻው ሲወጣ ይታያል፡፡ ቀጥሎም አስፈሪ የሆነ የነጎድጓድ ድምጽ ይሰማል፡፡ ወዲያው ነጭ ንስር ከዋሻው በር ላይ ባለው ዛፍ ላይ ሲያርፍ ይታያል፡፡ ወዲያው ዝናብ በሌለበት በፀሐይ ወቅትም ቢሆን የዋሻው በር በቀስተ ደመና ተከቦ ይታያል፡፡ ይህ በሚደረግበት ጊዜ እረኞችና ምሥጢሩ የሚገለጥላቸው ሰዎች ከዋሻው ራቅ ብለው ተአምራቱን ያያሉ፡፡ በማግሥቱ በዋሻው ሥር ያሉ እረኞችና ምእመናን ወደ ዋሻው ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ ከወትሮው የተለየ ትኩስ የቅዱሳን ዐፅም በሰሌን ተጠቅሎ መቁጠሪያና መቋሚያ ይዞ ይገኛል፡፡ በዚህ ዋሻ ውስጥ የሚታዩትን እጅግ አስገራሚ የሆኑትን ተአምራት በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ በቦታው ላይ አዲስ የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እየተሠራ ይገኛል፡፡

በአካባቢው ያለው የገጠሩ ምእመን በስዕለት ለዚህ ቅዱስ ቦታ የሚያስገባው መብዓ እና ከከተማ ለሚሄደው ተሳላሚ የሚሰጠው እምነት ለየት ያለ ነው፡፡
የአቡነ ሐራ ድንግል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ የሚያስቀምጥበትን አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳምን በተመለከተ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ አንድ የራሱ አተያይ አለው፡፡ ይኸውም፡- እንደ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ካሉ አስደናቂ ገዳማት ውስጥ አዲስ የሚቀበር ትኩስ አስክሬን ከተቀበረበት ቦታ እየተሰወረ የት እንደሚሄድ አይታወቅም፡፡ ምናልባትም ወደ አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም በየጊዜው በተአምራት የሚመጣው ትኩስ አስክሬን እንደነገላውዴዎስ ካሉት ሌሎች ገዳማት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ጎንደር ውስጥ ከወሮታ ወደ እስቴ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የቅዱስ ገላውዲዮስ ቤተ ክርስቲያን በንብ ይጠበቃል፡፡ ምግብ በልቶ ወደዚህ ቤተ ክርስቲያን መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ በድፍረት በልቶ የሚገባም ካለ ጠባቂው የንብ መንጋ መጥቶ ይወረዋል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ለየት ያለ አስገራሚ ተአምር ይፈጸማል፣ይኸውም በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የካህናት፣ የወንዶችና የሴቶች መካነ መቃብር የተለያየ ሲሆን የሚቀበረው አስክሬን ከሳምንት በኋላ የት እንደሚሄድ ሳይታወቅ አስክሬኑ ይሰወራል፡፡ በመቃብሩም በሳምንቱ ሌላ የሞተ ሰው ይቀበርበታል፡፡ አዲስ የሚቀበረውም አስክሬን ከሣምንት በኋላ ይሰወራል፡፡

(ምንጭ፡- ድርሳነ መድኃኔዓለም፣ ሕመማተ መስቀል፣ ገድለ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ፣ ገድለ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት፣ ሐመር 6ኛ ዓመት ቁ.4 1990 ዓ.ም ከገድላት አንደበት)
✞ ✞ ✞

tgoop.com/bahreTibebat/855
Create:
Last Update:

BY ባህረ ጥበባት

Share with your friend now:
tgoop.com/bahreTibebat/855

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The court said the defendant had also incited people to commit public nuisance, with messages calling on them to take part in rallies and demonstrations including at Hong Kong International Airport, to block roads and to paralyse the public transportation system. Various forms of protest promoted on the messaging platform included general strikes, lunchtime protests and silent sit-ins. Click “Save” ; Ng Man-ho, a 27-year-old computer technician, was convicted last month of seven counts of incitement charges after he made use of the 100,000-member Chinese-language channel that he runs and manages to post "seditious messages," which had been shut down since August 2020. Step-by-step tutorial on desktop: best-secure-messaging-apps-shutterstock-1892950018.jpg
from us

Telegram ባህረ ጥበባት
FROM American