tgoop.com/bilal_jema/8942
Last Update:
ዐርባ የሶለዋት ጥቅሞች
===============
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«ዐርባ ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] ጥቅሞች: ‐
❶ የአላህን ትእዛዝ መፈፀም።
❷ አላህም በነቢዩ [ﷺ] ላይ ሶለዋት ስለሚያደርግ ከአላህ ድርጊት ጋር መሳሰል። በእርግጥ የእኛና የአላህ ሶለዋት የተለያየ ነው። [የአላህ ሶለዋት እዝነት ሲሆን ከኛ ሲሆን ደግሞ ዱዓ ነው።]
❸ ከመላኢካዎች ጋር መመሳሰል።
❹ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያደረገ ሰው አላህ ዐስር ሶለዋት ያደርግበታል።
❺ ሰውየውን አላህ በዐስር ደረጃዎች ከፍ ያደርገዋል።
❻ ዐስር ሐሰና (የበጎ ሥራ ምንዳ) ይፃፍለታል።
❼ ዐስር ኃጢኣት ይሰረዝለታል።
❽ የዱዓን ተቀባይነት ያስገኛል።
❾ የሙስጦፋን [ﷺ] ምልጃ ያገኛል።
❿ ወንጀልን ለማሰረይ ምክንያት ይሆናል።
⑪ ሰውየውን አላህ ከጭንቀት ይገላግለዋል።
⑫ በቂያማ ቀን ሰውየው ከነቢዩ [ﷺ] ቅርብ ይሆናል።
⑬ ድኻ ለሆነ ሰው ሶለዋት የሶደቃን ቦታ ይሸፍናል።
⑭ አስቸጋሪ ጉዳይን ያገራል።
⑮ የአላህና የመላኢካዎችን ሶለዋት ያስገኛል።
⑯ ሰውየውን ከወንጀል ያፀዳዋል። ንፅህናን ያላብሰዋል።
⑰ ሰውየው ከመሞቱ በፊት በጀነት እንዲበሰር ያደርጋል።
⑱ ከቂያማ ቀን ድንጋጤ ይጠብቃል።
⑲ ሰውየው የረሳውን ነገር እንዲያስታውስ ያደርገዋል።
⑳ ለሰላምታው የነቢዩን [ﷺ] ምላሽ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
21. ስብሰባን ያሳምራል። ሶለዋት የተደረገበት ስብሰባ በቂያም ቀን ቁጭት አይከተለውም።
22. ድህነትን ያስወግዳል።
23. ስስትን ያስወግዳል።
24. አፍንጫው ይታሽ (ውርደት ይንካው) ብለው ነቢዩ [ﷺ] ካደረጉት ርግማን ይድናል።
25. ወደ ጀነት መንገድ ያስገባል። ሶለዋት የተወ ሰው ደግሞ ከጀነት መንገድ ይርቃል።
26. ከስብሰባ ክርፋት ያድናል። ምክንያቱም አላህና መልክተኛው [ﷺ] የማይወሱበት ስብሰባ ሁሉ የከረፋና የገማ ነው።
27. ኹጥባንም ሆነ ሌላን ንግግር ያሳምራል።
28. ሰውየው በሲራጥ ላይ የሚኖረውን ብርሃን ያበዛለታል።
29. ሰውየውን ከጭካኔ ያፀዳዋል።
30. ሶለዋት የሚያደርግ ሰው በምድርም ሆነ በሰማይ መልካም ስም እንዲኖረውና እየተወደሰ እንዲኖር ያደርገዋል።
31. ሶለዋት የሚያበዛ ሰው የተባረከ ይሆናል። ስራውና እድሜውም በረካ ይሆንለታል።
32. የአላህን እዝነት ያገኛል።
33. ሰውየው ለአላህ መልክተኛ ﷺ ያለው ፍቅር ዘውታሪ እንዲሆን ያደርጋል።
34. ዘውታሪ የሆነ የአላህ መልክተኛን [ﷺ] ውዴታ ያገኛል።
35. ቀና መንገድ መመራትን (ሂዳያ) ያገኛል። ቀልቡም ህያው ይሆንለታል።
36. የሰውየው ስም በነቢዩ [ﷺ] ፊት እንዲጠራ ያደርጋል።
37. በሲራጥ ላይ የሰውየው እግር እንዲፀና ያደርጋል።
38. ሰውየው የነቢዩን [ﷺ] ሐቅ በከፊል እንዲወጣ ያግዘዋል።
39. ሶለዋት አላህን መዝከርና ማመስገንን ያካተተ በመሆኑ ሰውየው ከአመስጋኞችና ከዛኪሮች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
40. ሶለዋት ዱዓም ነው። ምክንያቱም በሶለዋቱ ሰውየው አላህ በሚወዳቸው እና በመረጣቸው ነቢይ ላይ ውዳሴውን እንዲያደርግ መለመን ማለት ነው። በዚያውም ሰውየው ጉዳዩ እንዲፈፀምለትና ጭንቀቱ እንዲወገድለትም እየተማፀነ ነው።
--------------------------
📚 «ጀላኡል‐አፍሃም ፊ ፈድሊስ‐ሶላቲ ወስ‐ሰላሚ ዐላ ኸይሪል‐አናም ﷺ»
አህባቦቼ በዱኣ እና በዚክረ ሶላት ዓለ ነብይ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንበርታ
ፋጢመቱ✍️✍️✍️
@MEDINATUBE
BY ቢላሉል ሀበሽይ ጀመአ
Share with your friend now:
tgoop.com/bilal_jema/8942