tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group/1489
Last Update:
ማስታወሻ ‼
መልዕክተኛችን( ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ) እንዲህ ይላሉ
- ﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﻗﺎﻝ : ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪ
ﷺ : «ﻻ ﺗﻘﺪﻣﻮﺍ ﺭﻣﻀﺎﻥ ﺑﺼﻮﻡ ﻳﻮﻡٍ ﻭﻻ ﻳﻮﻣﻴﻦ،
ﺇﻻ ﺭﺟﻞٌ ﻛﺎﻥ ﻳﺼﻮﻡ ﺻﻮﻣًﺎ ﻓﻠﻴﺼُﻤْﻪ » . ﻣﺘﻔﻖٌ
ﻋﻠﻴﻪ
"ረመዷንን ሁለት ወይም አንድ ቀን በመፆም አትቅደሙት፤ከዛ በፊት ፆም ያስለመደ ሰው ካልሆነ በስተቀር፤ (ያስለመደ)ከሆነ ግን ይፁም።"
ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው ረመዷን ሁለት ወይም አንድ ቀን ሲቀረው መፆም የተከለከለ መሆኑን ነው።ነገር ግን የተከለከለው ያለምንም ምክንያት ከመሬት ተነስቶ ( ለምሳሌ የረመዷን መቀበያ እያሉ) መፆም እንጂ እዚው ሐዲስ ላይ እንደተብራራው ከዛ በፊት ያስለመድነው ሸሪዓዊ ምክንያት ያለው ፆም ከሆነ ግን ሁለትም ይሁን አንድ ቀን ሲቀረው መፆም የተፈቀደ መሆኑን ነው።ሸሪዓዊ ምክንያት ሲባል ለምሳሌ ረመዷን ማክሰኞ የሚገባ ቢሆን ሰኞና ሐሙስ ያስለመደ ሰው ረመዷን አንድ ቀን ሲቀረው መፆም አይቻልም ተብሏልና ሰኞን ቀን አትፁም አንለውም ምክንያቱም ሐዲሱ ላይ ከዛ በፊት ፆም ያስለመደ ሰው ካለ ግን ይፁም ተብሏልና።
አስተውሉ‼
ማስተላለፍ የፈለኩት መልዕክት ካለፈው ረመዷን ቀዷ ኖሮብን በተለያዩ ምክንያቶች ሳንፆም የቀረን ወንድሞችና እህቶች ካለን የሐዲሱ ክልከላ እኛን አይመለከተንምና ረመዷን አንድ ቀን ብቻ ቢቀረው እንኳን ያለብንን ቀዷ መክፈል ይቻላል ብቻ ሳይሆን ግዴታችን ነው።ምክንያቱም ሐዲሱ ላይ መልዕክተኛው ( ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ) ከዛ በፊት ፆም ያስለመደ ሰው ካለ ግን ይፁም ብለው ፍቃድ ሰጥተዋልና።ያስለመድነው ሱና ፆም ካለ እንድንፆም ከተፈቀደለን ዋጂብ የሆነን ፆም ( ያለብንን ቀዷ) መፆም ደሞ ይበልጥ የተፈቀደና ከዛም አልፎ ግዴታ ይሆንብናል።ስለዚህ ቀዷ ያለብን ወንድምና እህቶች ሐዲሱን በስህተት ተረድተን ወይም ያለ አግባብ የተረዱት ሰዎችን ንግግር ሰምተን ጊዜውን ማስመለጥ የለብንምና ያለብንን ቀዷ ካልጨረስን የተቀሩትን ጥቂት ቀናት ተጠቅመን ቀዷችንን እንፁም።
አሏህ ለመልካሙ ሁሉ ይግጠመን ‼
BY የቡታጅራ አህለሱና ቂራኣትና ዳዕዋ ቻናል
Share with your friend now:
tgoop.com/butajira_Qirat_daewa_group/1489