Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
🟢🟡🔴
ጥር 7 | #በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ፨
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፥ በአካል፥ በግብር ሦስትነት፣ በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው። በዚህ ጊዜ ተገኙ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም። መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና።
ሩኅሩኀን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን። የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም። የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል።
በዚህች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው።
፩. ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው
፪. ቅዳሴ ቤታቸው ነው።
#_ሕንጻ_ሰናዖር
በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ በነበረ ግዛት ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃን ሠሩ። በክፋትም ሥላሴን ሊወጉ ተነሡ።
ርኅሩኀን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም። የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና። ይልቁኑ "ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቀው" አሉ እንጂ።
ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቋንቋዎች ተፈጠሩ። እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ። ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት። ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል።
#_ቅዳሴ_ቤት
አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮጵያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጎንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታ ተጠናቃለች።
በተሠራች በ16 ዓመቷ፣ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል። ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በዓፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው።
🍀 #ቅዱስ_ሶል_ጴጥሮስ ዕረፍቱ ነው፨
የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት፣ ከ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት አንዱ፣ የኒቂያ ጉባኤ ሊቀመንበር ከነበሩና አርዮስን ካወገዙ አንዱ የሆነ፣ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ያጠመቀ ሊቅ ነው።

tgoop.com/christian930/5615
Create:
Last Update:

BY አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
Share with your friend now:
tgoop.com/christian930/5615