tgoop.com/christian930/5621
Last Update:
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም።
===================
ለነቢዩ ኢሳይያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ኤርምያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ሕዝቅኤል የተገለጸለት
እንዲሁም ለሁሉም ነቢያቶች የተገለጸላቸው ይለያያል።
ነገር ግን አንዱ ነቢይ ሁሉንም እኔ ብቻ ነው የማውቅ ብሎ ሌላውን ነቢይ ሲነቅፍ ሲተች አልታየም።
ለምሳሌ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ስሙንም አማኑኤል እንደምትለው ለነቢዩ ኢሳይያስ ተገልጾለት።ተናገረ።
ለነቢዩ ኤርምያስ ደግሞ በሠላሳ ብር እንደሚሸጥና ክርስቶስ እንሚባልም ተገልጾለት ተናገረ።
ነቢዩ ሚክያስም ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደሚወለድ ተገልጾለት ተናገረ።
ሁሉም እግዚአብሔር የገለጸላቸውን ተናገሩ።
እግዚአብሔር እኮ ሁሉንም ለነቢዩ ኢሳይያስ ገልጾለት ሁሉንም መናገር ይችል ነበር የሁሉም ክብር ይገለጽ ዘንድ እንጂ።
እናም ነቢዩ ኢሳይያስ ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ ነቢዩ ሚክያስ የተናገረውን ውሸት ነው ክርስቶስ በቤተልሔም አይወለድም አላለም።
ስለዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና
ሁሉን አውቃለሁ ብሎ ምሥጢሩን ሁሉ ሳይመረምር ዝም ብሎ ከሚናገር ሰው በዚህ ዘመን መራቅ ብልህነት ነው።
ማቴዎስ 11፥6 ላይ እንደተጻፈው።ጌታ
ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።
ሲል ተናገረ።እውነት በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት የማይሰናከል ምንኛ ብጹዕ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን አሳልፎ ለፍርድ የሚመጣው እኮ ቀድሞ መጥቶ ተወልዶ ተጠምቆ ተርቦ ተጠምቶ ንስሓ ግቡ ብሎ የታመሙትን ፈውሶ ለምጻሞችን አንጽቶ ወንጌልን አስተምሮ ተሰቅሎ ሙቶ ተነስቶ አርጎ ይህንን ሁሉ አድርጎ ቃሉን በናቁት እና ባቃለሉት ላይ ነው የሚፈርደው።ይህንን ሁሉ ባያደርግ ኑሮ ለፍርድ ባልመጣም ነበር።
ታድያ ዛሬስ በዚህ አመጸኛ ትውልድ ላይ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን የተሠጠው ንጉስ ቴዎድሮስስ ቀድሞ ሳያስተምር የሚገሰጸውን ሳይገስጽ ሳያስጠነቅቅ እንዴት ይመጣል?
የሚፈርደው እኮ በዚህ መልእክቴ እንዲህ አላልኩህም ነበር?ለምን ቃሉን ሰምተህ ንስሓ አልገባህም ብሎ እኮ ነው?
እናም ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን መልእክትን አጣጥሎ ልክ አዲስ እምነት እንደሆነ አድርጎ ህዝቡን ማሰናከል እጅግ ከባድ ፍርድ ውስጥ መግባት ነውና።
ሁሉም ሰው ሁሉን እንደማያውቅ ተረድተን መልእክቱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አምነን እስከ መጨረሻው ድረስ መጽናት ከመታደልም በላይ መታደል ነው።
የእግዚአብሔር እውነት ሁሌም አያዳላም።
ዲያቆን ቄስ ጳጳስ መነኩሴ መምህር ብሎ አያዳላም ካጠፋ አጠፋ ነው ንስሓ እንዲገባ ይገስጻል።ያማ ካልሆነ ምኑን እውነት ሆነ ታድያ?
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና በማንኛውም ሰው መሰናከል ከእውነት ፈቀቅ ማለት እውነትን አለማወቅ ነውና እስከ ሞት ድረስ የታመንን እንሁን
እውነት አርነት ያወጣናል እና።
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም። አራት ነጥብ።
17/5/2017
BY አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
Share with your friend now:
tgoop.com/christian930/5621