tgoop.com/christsbelievers/4226
Last Update:
እግዚአብሔር ራሱን የአዳም አምላክ አድርጎ ያልገለጸው ለምንድን ነው? አብርሃም እንደ አዳም ኃጢአት እንደሠራ እናውቃለን። እግዚአብሔር ለምን የአቤል አምላክ ብሎ እራሱን አልጠራም?
ለምን እግዚአብሔር ይልቁንስ ራሱን የአብርሃም ፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ ብሎ ጠራው?
ጌታችን ኢየሱስ በሥጋ ከአብርሃም ዘር እንደተወለደ በአዲስ ኪዳን ለምን ቀረበ?
በእነዚህ ሦስት እና በሌሎች ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት የቱ ላይ ነው?
እንግዲህ እርሱ ከእነዚህ ሦስቱ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ከመግባቱ በተጨማሪ ፣ እነሱን እንደ ተወካይ አድርጎ ወስዷቸዋል።
❤️ እግዚአብሔር በአለም ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎችን እንዲወክሉ ይመርጣቸዋል።
አብርሃም ምን አይነት ሰው ነው? እሱ የእምነት ግዙፍ ነው። እሱ እንደዚህ አይነት አምላክ ብቻ ቢሆን ኖሮ እኛ በእምነት ግዙፍ ስላልሆንን በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንገባ ነበር።
እርሱ ግን የይስሐቅም አምላክ ነው። ይስሐቅ ምን ዓይነት ሰው ነው? እሱ በጣም ተራ ነው። በሚችለው ጊዜ ይበላል, እና እንደ እድል ሆኖ ይተኛል እሱ ደግ ሰው ወይም ክፉ ሰው አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔር የተራ ሰዎች ብቻ ሳይሆን የክፉ ሰዎችም አምላክ ነው።
የያዕቆብም አምላክ ነው። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያዕቆብ በብሉይ ኪዳን ከታዩት እጅግ የከፋ ሰዎች መካከል አንዱ ሆኖ ተሥሏልና።
ስለዚህም በነዚህ በሦስቱ አካላት እግዚአብሔር የአብርሃም የበላጭ አምላክ የይስሐቅ ተራ አምላክ የያዕቆብም አምላክ መሆኑን እየነገረን ነው።
እኔ እንደ አብርሃም ልዩ ነኝ እንበል ከዚያም እርሱ አምላኬ ነው። እኔ እንደ ይስሐቅ ተራ ነኝ እንበል ከዚያም እርሱ አምላኬ ነው። ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ እንደ ያዕቆብ ከወንድሜ ጋር በተጣላሁ ጊዜ ክፉ የሆንሁ ነኝ እግዚአብሔር ግን አምላኬ ነው።
✍ #ዋችማን_ኒ
BY Christsbelievers
Share with your friend now:
tgoop.com/christsbelievers/4226