Telegram Web
መልካም ልደት ለእኔ ህዳር ጽዮን

አአኵተከ ፡ እግዚኦ ፡ አምላኪየ ፡
ዘልፈ ፡ ዘወሀብከኒ ፡ ኃይለ ፡ ወጥበበ ፡
እስመ ፡ ናሁ ፡ ዘይሁብ ፡ እምረተ ፡ ለልቡባን ፡
ጥበበ ፡ ለጠቢባን ፡ እምብዕለ ፡ ፀጋሁ ።

"ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች የሰጠ ፤ የሚሰጥ ዛሬም ጥበብና ኃይልን. . . . . የሰጠኸኝ የአባቶቼ አምላክ አመሰግንሀለው ።"
( ት.ዳን 3÷ 21-24 )

"እገኒ ለከ እግዚኦ እስመ ግሩመ ተሰባሕከ መንክር ግብርከ ወነፍስየ ትጤይቆ ጥቀ......"
ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥርያለኹና አመሰግንሃለው

ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ታውቀዋለች
እኔ በስውር በተሰራኹ ጊዜ አካሌም ከምድር ታች
በተሰራ ጊዜ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም

#ያልተሰራ_አካሌን_ዐይኖችህ_አዩኝ
#የተፈጠሩ_ቀኖቼ_ኹሉ
#አንድ_እንኳን_ሳይኖር_በመጽሐፍህ_ተጻፉ

አቤቱ ዐሳቦችህ በእኔ ዘንድ
እንደ ምን እጅግ የከበሩ ናቸው
( መዝ 138፥14-17 )
~~~~~~~~
🍂
እንድንከባት፣ እንድናቅፋት፣ በዙሪያዋ ተሰብስበን እንድንመካባት፣ በብርታቶቿ ተማምነን ልባችንን እንድናሳርፍባት፣ ጽዮን አንባችንን፣ ጽዮን መታመኛችንን፣ ጽዮን መመኪያችንን የሰጠን አምላክ ይክበር ይመስገን!!!

🙏🏽......ለአመቱ በሰላም በጤና ያድርሰን ....🙏🏽

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

ህዳር ጽዮን ( 21 )
November 30

📸 💎LEGACY IMPRESSION ®
☎️+251984187946☎️
📸BOOK NOW📸
@Legacy Impression
🍂 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሰማዕት
ህዳር 25 በዓለ ዕረፍቱ

✝️ ቅዱስ መርቆሬዎስ የነበረበት ዘመን በሶስተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ንጉስ ዳክዮስ የሮም ገዥ ሆኖ የነገሰበት ዘመን እንደመሆኑ በዘመኑ የተከበረ የተባለ የውትድርናን ትምህርት ተምሮ ለንጉሱ አገልጋይ ሁኖ ነበር ።

✝️ አባቱ በአደን ላይ ሳለ ሊበሉት ከመጡ ገጸ ከለባት እግዚአብሔር ስላዳነውና እንዲያውም አገልጋዮች ስላደረጋቸው በዚህ ተአምር መነሻነት ቤተሰቡ ሁሉ በክርስትና ሐይማኖት አምነው ተጠምቀዋል ።

ከጥምቀት በኋላ
አባቱ ✝️ ኖኅ
እናቱ ✝️ ታቦት
ተብለው ተሰይመዋል

✝️ቅዱሱም ፕሉፓዴር ከሚባል ከቅድሞ ስሙ መርቆሬዎስ ተብሏል። ትርጓሜውም የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው።

🍂 ባርባርያን በሮም ላይ በጠላትነት በተነሱ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ የጦር አዛዥ ነበርና የእግዚአብሔር መልአክ በሰጠው ሰይፍ በመዋጋት ድልን ተቀዳጅቷል። የባርባርያንን ንጉሥም ገድሎታል።

🍂 ንጉስ ዳኬዎስ ግን “ ድልን የሰጡን ጣዖታቴ ናቸው። “ በማለት ለጣዖታቱ በዓል አደረገ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ይህንን ድርጊት በአደባባይ ተቃወመ በንጉሱም ፊት ትጥቁንና ልብሱን ማዕረጉንም አውልቆ ወረወረው።

🍂 በዚህ የተቆጣው ንጉሡም በወታደሮች አስይዞ መከራን ያደርሱበት ዘንድ ወደ ቂሳሪያ ( ቀጰዶቅያ ) ላከው ።በዚያም የሰማዕትነት ስቃይን ከተቀበለ በኋላ ፦

✝️ በኅዳር 25 ቀን አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ ።

✝️ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከዕረፍቱ በኋላ ጸሊም (ጥቁር) የሆነ ፈረሱ ለሰባት ዓመታት በየሀገሩ እየዞረ ስለ ክርስቶስ መስክሯል።

✝️ በንጉሡ በዑልያኖስ ዘመን ክርስቲያኖች መከራና ስቃይ በበዛባቸው ጊዜ ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ በቅዱስ መርቆሬዎስ #ሥዕል ፊት ሲጸልዩ ሳለ
#አድነነ_ሥዕል_ከመ_ዘይብል_ኦሆ
/ #ስዕሉም_እንደሚታዘዝ_ዘንበል_አለ።/

🍂በስእሉ ላይ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሀዲውን ንጉስ ዑልያኖስን ሲገድለው ከጦሩም ጫፍ ትኩስ ደም ሲንጠባጠብ ታየ።
ባስልዮስና ጎርጎርዮስም ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር እጅግ ተደሰቱ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሐዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን ስላጠፋላቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ ።

🙏🏽የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን
ከመከራ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን 🙏🏽

👉🏻#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት እንደሣሉት


ዲያቅን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

@deacongetabalewamare
+ + አቤቱ ጌታዬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ + +
ከቤተ ያዕቆብ የወጣ የዘይት ዛፍ
ከዕሴይ ሥር የወጣ የሃይማኖት በትር፤
ከዳዊት ግንድ የበቀለችም አበባ ነኽ (ኢሳ ፲፩፥፩)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
በቅዱሳን አንደበት አንተ የሚጣፍጥ ስም ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
በእውነት ለሚጠሩኽ አንተ የሚጣፍጥ ዕሳቤ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
አንተ መንፈሰ ኮከባቸው ለደበዘዘባቸው መመኪያ የኾንኽ የአጥቢያ ኮከብ ነኽ (ዘኊ ፳፬፥፲፯፤ ራእ ፳፪፥፲፮)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቅዱሳን ገጽ ላይ ዘወትር የሚያበራ የጽድቅ ፀሓይ ነኽ (ሚል ፬፥፪)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከቊጣው የተነሣ የጨለማ አበጋዞች የደነገጡለት፤ ከማግሣቱም የተነሣ የምድር ተራሮች የተንቀጠቀጡለት ከይሁዳ ነገድ የተገኘ አሸናፊ አንበሳ ነኽ (ራእ ፭፥፭)

___
+ #አቤቱ_ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ
ከሕፃንነቴ ዠምረኽ ተስፋዬ አንተ ነኽ፤

+ በማሕፀንኽ አንተ ሰወርኸኝ በኹሉም ጊዜ አንተ ዕሳቤዬ ነኽ ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የመድኀኒቴ ቀንድ አንተ ነኽ

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የራሴ አክሊል አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለአፌ ጣፋጭ የኾንኽ የሕይወት እንጀራ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለጒረሮዬ
መልካም የኾንኽ የመድኀኒት ጽዋዕ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ያልተሸመነም ያልተፈተለም ልብስ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ዕጥፍ የኾንኽ ወርቅ የተገኘኽም ዕንቊ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
የበዛ ምናን የተረፈም መክሊት አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ አዳምና ስለ ልጆቹ ስትል መከራን የተሸከምኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በሔዋንና በልጆቿ ስሕተት ምክንያት የመስቀልን ሕማማት የተሸከምኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ሰው ልጆች በደል ስትል የመስቀልን ችንካሮች የተቀበልኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ አንተ በኹሉም ላይ ጌታ ነኽ፤
ሥልጣንኽም በኹሉም ላይ ነው፤
ታላቅነትኽም ከኹሉም በላይ ነው፤
የኹሉም ጌታ ተባልኽ፤
በኹሉም ዘንድ ተጠራኽ፤

__
+ አንተ #ሊቀ_ካህናት ነኽ፤
+ አንተ ንጉሠ ነገሥት ነኽ፤
+ አንተ ታላቅ መምህር ነኽ፤
+ አንተ የእረኞች አለቃ ነኽ፤
+ አንተ የምትናገር በግ ነኽ፤ አንተ ፍሪዳ ላም ነኽ፤
+ አንተ የአንበሳ ልጅ አንበሳ ነኽ፤
+ አንተ የሕይወት ውሃ ምንጭ ነኽ፤
+ አንተ #የመድኀኒት_ቀንድ ነኽ፤
+ አንተ የጽድቅና የሕይወት መንገድ ነኽ፤
+ አንተ የጽድቅ ፀሓይ ነኽ፤
+ አንተ የብርሃን ኮከብ ነኽ፤
+ አንተ #የሕይወት_እንጀራ ነኽ፤
+ አንተ የመድኀኒት ጽዋ ነኽ፤
+ አንተ የሰው ልጅና የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ፤
___
ይኽነን ኹሉ ስለ እኛ ፍቅር ስትል ተጠራኽበት) በማለት አምላኩ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰገነው ምስጋና እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲነበብ፣ ሲተረጐም፣ ሲመሰጠር ይኖራል፡፡

ዮሐንስ በራዕዩ ላይ በኲረ ሙታን (ራእ ፩፥፭)፤
የምድር ነገሥታት ገዢ (ራእ ፩፥፭)፤
የታመነው ምስክር (ራእ ፩፥፭)፤
የይሁዳ አንበሳ (ራእ ፭፥፭)፤
የታረደው በግ (ራእ ፭፥፲፪)፤
የታመነና እውነተኛ (ራእ ፲፱፥፲፩)፤
የእግዚአብሔር ቃል (ራእ ፲፱፥፲፫)፤
ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)፤
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ (ራእ ፲፱፥፲፮)፤
አልፋና ኦሜጋ (ራእ ፳፪፥፲፫) ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)፤
የዳዊት ሥርና ዘር (ራእ ፳፪፥፲፮)፤
የሚያበራ የንጋት ኮከብ (ራእ ፳፪፥፲፮)
-------------------------------------------
/ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /

#ጌታችን_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ
ዘወትር እናመሰግንህ ዘንድ
ውሳጣዊ አዕምሯችንን ብሩህ አድርግልን ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /
@deacongetabalewamare
🍂 #ቅዱስ_አማኑኤል 🌹
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ

አቤቱ ቸርነትህ ፈጥና በላያችን ትደረግ
የፊትህም ብርሃን በሰውነታችን ይገለጽልን

🍂
የሚያድነን ይቅርታህ በቸርነትህ ይምጣ ይደረግልን
ደስ የሚያሰኘን ቸርነትህም ይገለጽ
አቤቱ ከከፉ ነገር ከስህተትም ጠብቀን
ተመለሱ እመለስላችኋለው ብለህ በረድኤት ተቀበለን

🍂
በእኛና በአንተ መካከል ያለውን ፍቅር አንድነትን ይቅርታህን አድርግልን ፤
የበደለውን ሰው በንስሐ ወደአንተ መመለስ ይቻልኻልና
ሥፍር ቁጥር በሌለው በቦታህ ሁሉ እንሰግድልሀልን

🍂
ጩኸን አሰምተን በለምንን ወደ አንተ በለመንን ጊዜ
አንተ ትሰማናለህና
የሰውነታችንንም ድካም ትሸከምልናለህ ፤ ታቀልልናለህ
ኃጢአታችንንም ትታገሠናለህ

አቤቱ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር
መሐሪ ይቅር ባይ ነህ ፤ 🙏🏽

+_+_+_+_+_+_+_+_+_

/ ሊጦን ዘረቡዕ /

…………………
መዓትህ የራቀ
…………………..
ምህረትህ የበዛ
…………………………………………..
አምላካችን ቅዱስ አማኑኤል ሆይ
…………………………………………………
እንደ በደላችን ሳይሆን እንደቸርነትህ

ማረን
ራራልን
ይቅርም በለን
🙏🏾
…………………………………..

#ሥዕለ_ቅዱስ_አማኑኤል
#ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት_እንደሣሉት
@seali_kesis_amare_kibret

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /
+ 251923075264

@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare
“ነቢይ ዘከመ እሳት ⇨ እሳታዊ ነቢይ”
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥

"ወተንስአ ኤልያስ ነቢይ ዘከመ እሳት ወቃሉኒ ከመ ነድ ያውኢ ⇨ እሳታዊው ነቢይ ኤልያስ ተነሣ ቃሉም እንደ እሳት ያቃጥል ነበር" 【ሲራ. ፵፰፥፩】

መነሻችን የሚሆነው ጥያቄ ነው?
☞ [መኑ ውእቱ] ዘዐርገ በነደ እሳት በሰረገላት ወበአፍራስ ዘእሳት ?
በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረስ ወደሰማይ የወጣ ማነው?
ይህን ጥያቄ የሚያነሳው ሲራክ ብለን የምንጠራው ኢያሱ ወልደ ሲራክ ወይም ኢያሱ ወልደ አልዓዛር በመጽሐፉ ፵፰ኛ ምዕራፍ ቁጥር ፱ ላይ ነው።

በመጽሐፈ ሲራክ መቅድም ሊቃውንቱ ይኽን ነግረውናል
ሲራክ፦ ፀሐፊ ማለት ነው፤ ፀሐፊው ኢያሱ ወልደ አልዓዛር ወልደ ሲራክ ይባላል።
፶፩ ምዕራፎች ፦ በአቀራረቡ ከሰሎሞን መጽሐፈ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይነት አለው።
ይዘት ፦ ለመንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወታችን ጥበብና ምክር የሚሰጥ ነው።

ሲራክ ስለእሳታዊ ነቢይ ይጠይቃል፤
ማነው? በእሳት ተጠቅልሎ የተወለደ ፣ በእግዚአብሔር ቃል ሦስት ጊዜ ከሰማይ እሳት ያወረደ ፣ በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ተጭኖ ወደሰማይ የነጎደ ማነው?
በዘይቤ መንፈሳዊ ትምህርትነትና ምክር በስፋት የያዘው ይኽ መጽሐፈ ሲራክ የእሳትን አስተማሪ ምሳሌነ አጉልቶ በብዙ መንገድ ይነግረናል ለአብነት
☞ ወርቅን ወርቅ ለመሆኑ የሚፈትኑት በእሳት እንደሆነው ሁሉ ጻድቅም ችግር በሚያመጣ መከራ ተፈትኖ የሚያልፍ ነው 【፪፥፭】
☞ የሚነድ’ እሳት የሚጠፋው በውኃ እንደሆነው ኃጢዓት የሚሰረየው በምጽዋት ነው 【፫፥፳፰】
☞ ከተናጋሪ ሰው ጋር መከራከር በእሳት ላይ እንጨት እንደመከመር ነው 【፰፥፫】
☞ መልከ መልካምና ደምግባት ያላት ሴት ፍቅር የሚነድ’ እሳት ነው 【፱፥፰】
☞ በነጻ ፈቃድ እንዲመርጥ ለሰው እግዚአብሔር ያቀረበው የጽድቅና የኃጢዓት መንገድ እንደ እሳትና ውኃ ነው 【፲፭፥፲፮】
☞ ሰው በልቡ ሐሳብ መፈተኑ ሸክላ በእሳት እንደሚፈተነው ነው 【፳፯፥፭】
☞ የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣው እሳት ነው 【፳፰፥፳፪】…

እሳት በጠባዩ ይቡስ (ደረቅ) ፣ ውዑይ (የሚያቃጥል) እና ብሩህ (የሚበራ) ነው። በፍጥረትነቱም ከዐራቱ አሥራው ፍጥረታትና ባሕርያት አንዱ ሆኖ በሁሉ የሚገኝ በይብስቱ ከነፋስ በውዕየቱ ከመሬት በብርሃኑ ከውሃ የሚስማማ ፍጥረት ነው።

ሲራክ ምዕራፉን የሚጀምረው የነቢዩን ማንነት እንዲህ ሲል ነግሮን ነው! "ወተንስአ ኤልያስ ነቢይ ዘከመ እሳት ወቃሉኒ ከመ ነድ ያውኢ ⇨ እሳታዊው ነቢይ ኤልያስ ተነሣ ቃሉም እንደ እሳት ያቃጥል ነበር" 【ሲራ. ፵፰፥፩】

አልያስ ማለት ቀናዒ
መደንግጸ አብዳን፡ ሕገ መነኮሳት ሠራዒ
ኤልያስ ማለት ድንግል
ብእሴ ሰላም ፡ መምህረ እስራኤል
ኤልያስ ማለት ቅብዓ ፍሥሐ
ለቤተክርስቲያን ፡ አንቀጸ ጽርሐ
ኤልያስ ማለት ካህነ ኦሪት
ምዑዘ ምግባር ፡ መዝገበ ሃይማኖት
ኤልያስ ማለት ጸዋሚ
ለእግዚአብሔር ቊልኤሁ ፡ ዝጉሐዊ ተሐራሚ

ኤልያስ ማለት…

ኤልያስ ቴስብያዊ ፣ ኤልያስ ቀርሜሎሳዊ ፣ ኤልያስ ታቦራዊ ፣ ኤልያስ ዘሰራጵታ፣ ኤልያስ ነቢየ ፋፃ … በኩረ ሐዋርያት ፣ ቢጸ ነቢያት ፣ ነቢየ ክርስቶስ ፣ ነቢየ ልዑል ባለብዙ ግብር ባለብዙ ስም …

የዚኽ እሳታዊ ነቢይ ስሙ እንዲህ የበዛው ሥራው ስለበዛ ነው "በአምጣነ ዕፁ ለእሳት የዐቢ ነዱ ⇨ በእንጨቱ ብዛት የእሳቱ ነዲዱ ይበዛል" እንዲል【ሲራ. ፳፰፥፲】

ወሬዛ በኃይሉ አረጋዊ በመዋዕሉ ተብሎ የተገለጠ ጸሐፌ ትዕዛዝ ቅዱስ ኤልያስ ጥር ፮ በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ተጭኖ ወደሰማይ ያረገበት ቀን ፣ ታኅሳስ ፩ በአክአብ ፊት በኃይል ለዘለፋ የተገለጠበት(የናቡቴ ዕረፍት) ፣ «ነሐሴ ፳፬ ቀን ደግሞ ልደቱ» ነው፤ በእነዚኽ ቀናት ልንዘክረውና ልናከብረው ይገባል!

እንኳን እሳት ያወረደውን ቀርቶ የወረደውን እሳት ማክበር ተገቢ ነው ፤ አበው እንዴት መያዝ እንደሚገባው ሲነግሩን «እሳትን በገል ውሃን በቅል» ብለዋል።
ሙሴ አንደበቱ ትብ የሆነው እሳት በልቶ ፣ መጻጉዕ እጁ የተኮማተረው እሳት ጸፍቶ መሆኑን እናውቃለን።

ሊቁ እንዲህ ተቀኝቷል
"መጻጉዕ ሕፃን ኢያእመረ ነፍሰ ዓዲ
አኮኑ ፈነወ እዴሁ መንገለ እሳት ነዳዲ

【 መጻጉዕ ሕጻን ነው ነፍስ ማወቅ መች ጀመረ ?
ቢበስልማ ኖሮ ወደሚነደው እሳት እጁን ባልጨመረ 】

ኤልያስ ማለት በእብራይስጡ (ኤል אֵל) እና (ያስ/ ያህ יָהּ)ከሚሉ ሁለት የፈጣሪያችን ስሞች የተገኘ ጥምረት ሆኖ "እግዚአብሔር ጌታዬ ነው" የሚለውን ፍቺ ይሠጣል። በቅዱሱ መጽሐፍም ከታላቁ ነቢይ ውጪ ሌሎች ሁለት እስራኤላውያን በዚህ የከበረ ታላቅ ስም ተጠርተዋል።

በግሪኩ ደግሞ ኤሊያ ἐλαία (አላህያህ) ማለት ወይራ ማለት ነው። ይህን ያዞ ጌታችን የወይራ ዛፍ በበዛበት ተራራ በደብረ ዘይት ሲጸልይበት የነበረውን ዋሻ የኤልዮን ዋሻ እያለ ይጠራዋል

“ወመዐልትሰ ይሜህር በምኵራብ ወሌሊተ ይወፅእ ወይበይት ውስተ ደብር ዘስሙ ኤሌዎን ⇛ዕለት ዕለትም በመቅደስ (በምኩራብ) ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን [ኤሌዎን በሚባል] ደብረ ዘይት ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር ” 【ሉቃስ ፳፩፥፴፯】

መጽሐፍም ኤልያስ ማለት ወይራ ማለት ነው የሚለውን ልሳነ ጽርእ ይዞ የወይራን ተክል ፍሬና ዘይትን ኤልያስ እያለ ይገልጣል (The tree , the fruit or the oil ☞ ዕፀ ዘይት ፣ ፍሬ ዘይት ፣ ቅብዐ ዘይት)

【ኩፋ ፲፯፥፲】 "ወነሥአቶ እሙ ወሐራዊ ወገደፈቶ ታሕተ አሐቲ ኤልያስ ወሖረት ወነበረት አንጻሮ መጠነ አሐቲ ምንጻፍ እስመ ትቤ ኢይርአይ ሞት ለሕጻንየ ወነቢራ በከየት ⇨እናቱ አነሳችውና ሔዳ በአንዲት የወይራ/ዘይት እንጨት ሥር አኖረችው የልጁን ሞት አላይም ብላለችና በዚያ ተቀምጣ አለቀሰች" (13፥31)

【ሔኖ ፫፥፳፬】 "ወአሕቲ መስፈርተ ኤልያስ ትገብር ዐሠርተ ምክያደ ዘይት ⇨አንዲቱም መስፈሪያ ዘይት አስር የዘይት አውድማንበትመላለች "

የእኛ ሊቃውንት ስሙን በዘይቤና በምሥጢር እያራቀቁ «ዕፀ ዘይት ማኅቶት በቅድመ እግዚአብሔር ፣ ሥዩም ላዕለ ምድር ወሥሉጥ ላዕለ ሰማይ ወላዕለ ማይ » በማለት ገልጠውልናል። በ«መልኩ» መነሻ ላይም
ሰላም ለትርጓሜ ስምከ ዘተብህለ ዘይተ
… በጸውኦ ስምከ ኤልሳዕ ዮርዳኖስ አዕተተ" ይላል

የቅዱስ ዮሐንስ ራእይ ቃልም ለእርሱ መነገሩን በምሥጢር አስማምተው ይተረጉማሉ።

"ዕፀ ዘይት ወመኃትው በቅድመ እግዚአብሔር "【ራዕ ፲፩፥፬】
አቡቀለምሲስ በዚህ የራእዩ ክፍል በአምላካቸው ፊት ወይራና መቅረዝ እያለ አክብሮ የጠራው ሔኖክና ኤልያስን ነው።
✧ ወክልኤ ዕፀ ዘይት እለ ቅድመ እግዚአብሔር
(በእግዚአብሔር ፊት ያሉ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የሚሆኑ ሁለቱ የወይራ ዛፎች) መባላቸው
☞ ሄኖክ ማለት ተሐድሶ(አዲስ መሆን) ማለት ነው።
ተሐድሶ በዘይት ነውና
☞ ኤልያስም ማለት ከላይ እንዳየነው ዘይት ማለት ነው።

ወክልኤ መኃትው እለ ቅድመ እግዚአብሔር
(በእግዚአብሔር ፊት ያሉ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የሚሆኑ ሁለቱ መብራቶች) መባላቸው
☞ በትምህርታቸው የሰውን ልቡና ብሩህ ያደርጋሉና

ነገረ ዘይት/ ወይራ ዛፍ (About Olive Tree)

ከዕለተ ሠሉስ ዕፀው መካከል ዕፀ ዘይት (የወይራ ዛፍ) አንዱ ነው! ቅባት የሚሰጥ ለመብልነት ለመብራትም የሚውል የወይራ ወገን ነው::
* በሕገ ልቡና በሰብአ ትካት ለጥፋት ውኃ መወገድ በሰላም አብሣሪዋ ርግብ የመጣ ምልክት ይኼ ወይራ ነው! "ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ።" 【ዘፍ ፰፥፲፩】

* በሕገ ኦሪት ከምድረ ርስት ከነአን ገጸ በረከት አንዱ ይኼ ወይራ ነው! "ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፥..." 【ዘዳ. ፰፥፰ በቤተ መቅደሱ ያሉ ሁለቱ ኪሩቤል የተቀረጸው : የመቅደሱ መግቢያ መቃን እና የቅድስተ ቅዱሳኑ ደጃፍ አምድ የተሰራው ከዚሁ ከወይራ ነው! 【፩ ነገሥ. ፮፥፳፫-፴፬】

* በሕገ ወንጌል በመዋዕለ ሥጋዌው ሌሊት ሌሊቱን ጌታችን የመረጣት የጸሎት ሥፍራ ምጽአቱን ያስተማረባትና ዕርገቱን የፈጸመባት ደብር የወይራ ዛፍ የበዛባትን ሥፍራ "ደብረ ዘይትን" ነው! 【ሉቃ. ፳፩፥፴፯】 ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፥ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር።

በነገረ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ምሳሌነቱ

የወይራ ዛፍ የቤተ እግዚአብሔር መብራት ምንጭ ነው! የፈጣሪን ገጸ ምህረት ተወካፌ ጸሎትነት ያሳያል "አንተም መብራቱን ሁል ጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው።" 【ዘጸ· ፳፯፥፳】
የወይራ ዛፍ ክር የሚነድበት ዘይት መገኛ ነው! ለእግራችን መብራት ለመንገዳችን ብርሃን የሆነ ህጉን ለሚያስተምሩ ምግባር ለሚያሰሩ አበው ምሳሌ ነው! "ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።" 【መዝ. ፻፲፰፥፻፭】
የወይራ ዛፍ በቤተ እግዚአብሔር ያማረ የተወደደ እንደሆነ እንዲሁ በሥላሴ ፊት ባለሟልነት በምዕመናን ዘንድ መወደድ በአጋንንት ዘንድ መፈራት ያላቸውን አበውን የመስላል! "ለእስራኤልም እንደ ጠል እሆነዋለሁ... ውበቱም እንደ ወይራ ይሆናል" 【ሆሴ. ፻፬፥፮】
የወይራ ዛፍ ብዙ ፍሬ እንዲያፈራ ባለ ብዙ ጸጋና ክብር የሆኑትን አበውን ይመስላል! " ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።" 【መዝ. ፻፳፯፥፫】
የወይራ ዛፍ ቀን ከአእዋፍ ሌሊት ከአራዊት በአጥር በቅጥር ተጠብቆ እንዲኖር በረድኤቱ በቤቱ ጥላ ተጠብቀው የሚኖሩ አበውን ይመስላል! "እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤" 【መዝ· ፶፩፥፰】

ለዚህ ነው የኢያሴንዩና የቶና ልጅ ኤልያስን ባለራእዩ ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፈ ቀለምሲስ «ዕፀ ዘይት ወመኃትው በቅድመ እግዚአብሔር » እያለ የሚጠራው። እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው። ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል። እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው። በረከታቸው በሁላችን ይደር !

🍁 [ኦ ኤልያስ] ; ብፁዓን ፡ እለ ፡ ያአምሩከ ፤ ወእለ ፡ ስርግዋን ፡ በፍቅርከ ፤ ወንሕነሂ ፡ ሕይወተ ፡ ነሐዩ ፡ (በእንቲአከ) ።

🍁 [ኤልያስ ሆይ] ; የሚያውቁህና በፍቅርህ ያጌጡ ሰዎች ብፁዓን ናቸው፣ እኛም ስለአንተ በሕይወት እንኖራለን።

🍁 [Oh Elijah] ; Blessed are they that saw thee, and slept in love; for we shall surely live.
【ሲራ ፵፰፥፲፩, Sirach 48:11】

መጽሐፍ እጅግ ማግነናችንን ከአምላክ ማስተካከላችን እንዳልሆነ ሲነግረን እንዲህ ይላል ⇨ አኮ ዘናስተአርዮ ምስለ ፈጣሪሁ አላ ናስተማስሎ በኵሉ ግብር ምስለ አምላኩ። ⇨ ከፈጣሪው ጋር የምናስተካክለው አይደለም በሥራዎቹ ሁሉ ከአምላኩ ጋር እናመሳስለዋለን እንጂ ⇨ We do not equate Him with the Creator, but we view him as an example of God in all his works.
አልያስ ፍጥረቱ እንደኛው መሆኑን “ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥” 【ያዕ፭፥፲፯】 ነገር ግን ከመጠን ይልቅ ማክበራችን ታዘንና ተለምነን መሆኑን ልብ ይሏል “ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን። ”【፩ኛ ተሰ ፭፥፲፪】

አንድ #ማስተካከያ በማመልከት መልእክታችንን እንቋጫለን።

ኤልያስ የተወለደው በምን ቀን ነው?
መጽሐፈ ስንክሳራችን ታኅሳስ ፩ ቀን "የተገለጠበት ቀን” የሚለውን ይዘው ናቡቴ ባረፈበት ቀን ተወልዷል የሚሉ መምህራንና አድባራት ጭምር ይታያሉ፤ መገለጡ በጾመ ነቢያት በነቢይነቱ በ’ነ አክአብ ፊት ፣ በሐሳውያን ነቢያትና በካህናተ ጣኦት ዘንድ፣ በእስራኤላውያን መካከል… መሆኑን ለመግለጥ እንጂ መወለዱን የሚገልጥ እንዳልሆነ መጽሐፍ ያብራራል።
ታዲያ ልደቱ መቼ ነው ያሉ እንደሆነ «መልኩ» በዚሕ መልክ አስቀምጦታል

"…ኤልያስ እምከ ካልዕተ ሣራ ጠባብ
ልደትከ አመ እሥራ ወአመ ሰኑዩ ለአብ
እንዘ ኩለንታከ በእሳት ግልቡብ …"

ከዚህ ውሥጥ «ልደትከ አመ እሥራ ወአመ ሰኑዩ ለአብ»
አብ የተባለው ወርኅ የቱ ነው ብለን የአይሁድን ዜና መዝገብ ብንፈትሽ ታሪክ ጸሐፊው ዮሴፍ (Flavius Josephus ⇝Yoseph Ben Mattithyahu) እንዲህ በማለት የወሩን ቁጥር ጭምር ያመለክትልናል
"ወርኃ ኃምስ ወውእቱ ወርኅ ወርኃ አብ ⇨ አምስተኛው ወር እርሱም አብ የሚባለው ወር ነው"【መጽሐፈ ዮሴፍ ኮርዮን ፶፫፥፭】

ይህ በዕብራውያኑ አብ የተባለው ለሚያዝያ ፭ኛው ወር በእኛ ደግሞ ወርኃ ነሐሴ ነው፤ ስለዚህ የኤልያስ ልደቱ "አመ እሥራ ወአመ ሰኑዩ ለአብ" ባለው መነሻ ነሐሴ ፳፬ ይውላል ማለት ነው።

“እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።”【ሚል ፬፥፭ 】

#የቅዱስ_ኤልያስ_በረከቱን
#አምላካችን_ለሁላችን_ይላክልን 🙏

✍️ ከቴዎድሮስ በለጠ ታኅሳስ ፩/፳፻፲፮ ዓ.ም. ( Edited & Яερ๑šтεd ƒr๑๓ ጥር ግዝረት ፳፻፲፭ ከእንጦጦ ርእሰ አድባራት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አልያስ ወኤልሳዕ)

መጋቤ ሐዲስ Tewodros Belete Mengistu
የታላቁ ነቢይ የቅዱስ ኤልያስ ረድኤተ አይለይዎ
በእውነት ቃለ ሕይወት ያሰማልን 🙏🏾🙏🏾🙏🏾

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
እንዲህ ወብ አድርገው ሥለውታል

@deacongetabalewamare
መ ቅ ደ ሲ ቱ ን ፡ በ መ ቅ ደ ስ ፡ አ ስ ቀ መ ጧ ት

#ታኅሣስ_3_ቀን እመቤታችን መንፈሳዊ ጉዞ የጀመረችበት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ የታየበት ለካህናቱና ለሕዝቡ ያስረዳበት ዕለት ናት ይህም እንዲት ነው ቢሉ

ሐና ከነገደ ይሁዳ የተወለደ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው አግብታ ስትኖር እንደ አያቶቿ መካን ሆነች በዚህ እያዘኑ ሳለ ሐና ቤተ እግዚአብሔር እጅ ነሥታ ስትመለስ ርግቦች ከዛፍ ሥር ልጆቻቸው ጋራ ሲጫወቱ አየች ።

« አቤቱ ፈጣሪዬ ሁሉን ሁለት ሁለት አድርገህ ፈጥረህዋል ለመሆኑ ባሪያህ እኔን ምን ብለህ ፈጥረሃታል ? ደንጊያ ብለህ ፈጥረሃታል ? ለእንስሳቱ ለአዕዋፉ ያልነሣህውን ዘር ለእኔ ለምን ነሣህኝ » ብላ ምርር ብላ አለቀሰች ከዚህም በውኋላ ሐናና ኢያቄም ሱባዔ ያዙ ስእለትም እንዲህ ብለው ተሳሉ።

« አቤቱ አምላካችን ሆይ ስድባችንን ብታርቅልን ልጅም ብትሰጠን ወንድ ልጅ ከሆነ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ያብላን ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መብራት አብሪ መሥዋዕት አቅራቢ እንዲሆን ለአንተ እንሰጣለን ።

ሴት ብንወልድ ውኃ ቀድታ እንጨት ሰብራ እንጀራ ጋግራ ትርዳን ትጡረን አንልም መሶበ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ እንድትኖር ለአንተ እንሰጣለን ብለው ብፅዐት ገቡ ። » የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸሩ አምላክ ልመናቸውን ሰምቶ ከስቶታ ሁሉ በላይ የሆነች ስጦታ እመቤታችንን ሰጣቸው ።

እመቤታችን የስእለት ልጅ ናትና ሶስት ዓመት ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋት ሄዱ ፡፡

ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም መጥቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ ባለ ጊዜ ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ ፡፡

ዘካርያስ ለርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሣ መልአኩ ወደላይ ራቀበት የርሱ ተወራጅ ስምዖንም እንኪያስ ለኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ ራቀበት ፡፡

ካህናቱና ሕዝቡም በሙሉ ተራ በተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ ሐና ትተሻት እልፍ በይ አሏት ትታት እልፍ አለች ፡፡

ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት ፡፡

© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
Daweit Tesfay
ታኅሳስ 3 20 17 ዓ.ም

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /

📞 +251923075264

@deacongetabalewamare
መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ፤ ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ፤ በረምሃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ።


ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ
www.tgoop.com/deacongetabalewamare
#በታኅሳስ_ወር_በ6ኛው_ቀን የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያኗ ቅዳሴ ቤቷ በአርማንያ ሀገር ፣ በኪልቂያ ፣ በሶርያ ፣ በአንጾኪያና በግብጽ አውራጃዎች ሁሉ ሆኗል።

« ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ » እንዳለ እግዚአብሔር አምላክ ለእናታችን ቅድስት አርሴማ ስለ አምላኳ ስትል ከብዙ ጽናትና ተጋድሎ በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ኪዳን ገባላት

« በእኔ ስም አምነሽ የዚህን ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ ፤ በዓልሽን ያከበረ ፤ ዝክርሽን የዘከረ ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ ፤ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ » ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል ፡፡

በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ በገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው ፡፡

የሰማዕቷ : ቅድስት : አርሴማ : ረድኤት : ከሁላችን : ጋር : ይሁን : የቅድስት : አርሴማ : ቃልኪዳኗ : ሀገራችንን : ኢትዮጵያን : ከክፉ : ይሰውርል ።

© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ ✍🏽 Daweit Tesfay
ታኅሳስ 6 20 17 ዓ.ም

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
እንደሳሉት
📞 +251913684351

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
የሰማዕቷ : ቅድስት : አርሴማ : ረድኤት : ከሁላችን : ጋር : ይሁን : የቅድስት : አርሴማ : ቃልኪዳኗ : ሀገራችንን : ኢትዮጵያን : ከክፉ : ይሰውርል ።


ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
📞 +251913684351
🍂 ጻድቁ አባታችን #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
ታህሳስ 9 በዓለ ልደታቸው

አባታቸው መልዓከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም
ይባላሉ፡፡የተወለደበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር
ዳውንት ይባላል፡፡

ጻድቁ አባታችን በዚያች ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈራ
ስሙ መልዓከ ምክሩ የሚባል ደግ ሰው ባለቤቱም ወለተ
ማርያም ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው
በእግዚአብሔር ህግ ጸንተው የሚኖሩ መልካም ስራን
በመስራት እንደ ዘካርያስና ኤልሳጴጥ እውነተኞች ነበሩ፡፡

ሁለት ደጋጎች ልጆችም አሏቸው የተባረከ መልካም ፍሬን
የሚያፈራ በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔርን
የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ
እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር፡፡

🍂 ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ጆሮውን ወደ
ልመናቸው አዘነበለ እንዳለ መዝ 33፤29 እግዚአብሔር
አምላክ በዓይነ ምህረት ተመለከታቸው ልመናቸውንም
ሰምቶ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ቀን
ተጸንሶ #ታህሳስ_9 ቀን ተወለደ፡፡በተወለደ እለትም ተነስቶ
በእግሩ ቆሞ 3 ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ ጣዕም ባለው አንደበቱ
ተናገረ፡፡ 9 ጊዜም ህጻናትን ለሚያናግሩ ገዥ ለሚሆኑ
ለአጋይዝተ አለም ስላሴና ለእመቤታችን ለመስቀሉም
ሰገደ፡፡እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ብዙ ሰዎች ከህጻኑ
አንደበት የስላሴን ምስጋና ሰምተው ፈጽመው አደነቁ
ዳግመኛም በዚህ ህጻን ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ
አድሮበታል ብለው እየተጨዋወቱ ወደ ሀገራቸው ገቡ፡፡

አባቱና እናቱም መጀመሪያ ስለመወለዱ ዳግመኛም
የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ምስጋና በማቅረቡ ደስ
አላቸውና እግዚአብሔር ይህን ህፃን ሰጠን እኛ በአብ
በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስዕል ፊትና ለፍጥረት ሁሉ
ለምትራራ ከሁሉ በላይ በሆነች አምላክን በወለደች
በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ቁመን እንደለመንን
ልመናችንን ሰምታ የተመረጠ ልጅ ሰጠችን ብለው
አመሰገኑ፡፡የመንጻት ወራት በተፈጸመ ጊዜ በ40 ቀን
አባትና እናቱ በጸራ ወርቅና ብር ንጉስ ይኩኖ አምላክ ወደ
አሰራው እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ወስደው አዳም
በ40 ቀኑ ወደ ገነት እንደገባ በቤተክርስቲያን ስርዓት
ተጠመቀ፡፡

አዳም በአርባ ሄዋን በሰማንያ ቀን ወደ ገነት
እንደገቡ ኩፋሌ 4፤9 ካህናትም መንፈስ ቅዱስ
እንዳናገራቸው ስሙን እስትንፋሰ ክርስቶስ ብለው ሰየሙት ስጋ ወደሙን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ የስሙም ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቀው አደገ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቦናውን ብሩህ አድርጎለት በ5 ዓመቱ የቅዱሳን መጽሐፍትን፣ ቃላትን ፣ብሉያትንና
፣ሐዲሳትንም፣ድርሳናትንም አወቀ፡፡ ከመምህር ኪራኮስ
የመፅሐፍትን ትምህርት ከነትርጓሜው በ7 ዓመቱ ጨረሰ፡፡

🍂 በማስተዋል ሲመለከት አባቱንና እናቱን ዘመዶቹን የተወ ቃሌን ይጠብቃል መንግስተ ሰማያትን ይወርሳል ይህን ያላደረገ ሊያገለግለኝ አይችልም የሚለውን አገኘ ማቴ
10፡37 ይህንንም ቃል በልቦናው ይዞ የምነናውን ስርዓት
ይጠብቅ ነበር፡፡ 7 ጊዜ በመዓልት 7 ጊዜ በሌሊት
በየዕለቱ 150 መዝሙረ ዳዊትን ሲያደርስ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊቱን በትምህርተ መስቀል አማትቦ
ጸሎት በጀመረ ጊዜ እጆቹን ሲዘረጋ ወጥመዳቸውን
ያጠመዱ አጋንንት በነፋስ ፊት እንዳለ ጢስ ተነው ይጠፋሉ

እየተሯሯጡም ፈጥነው ይሸሻሉ፡፡ ከዚህ በኃላ ስሙ
ማርቆስ ከሚባል ጳጳስ ድቁናን ተቀበለ፡፡ ልጄ
ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ
ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ እንዳለ ሲራክ 2፤1 ይህንን
አለም ናቀ፡፡ ልዩ ክብር የሚሆን የምንኩስናን ልብስ
ይቀበል ዘንድ በተወለደ በ 14 ዓመቱ ወደ ደብረ ሐይቅ
ገዳም ሄደ ከባህር ዳር ቆሞ የሙሴን ጸሎት ወደ
እግዚአብሔር ጸለየ ያለመርከብ ባህሩን ተሻግሮ ወደ
ቤተክርስቲያን ገባ፡፡የኢየሱስ ሞዐ ልጅ የሚሆን አበምኔቱ
በመነኮሳት መጽሐፍ እንደተፃፈ 3 ዓመት ፈተነው፡፡ በኃይቅገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት ያገለግል ነበር፡፡ከአባ ህንጻ ደብረ ድባ ከሚባል ቦታ የቅስና ስልጣን ተቀበለ፡፡

🍂 አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ለማስተማር ወደ
አባቶቹ ሀገር ወደ አባቱ መቃብር በገባ ጊዜ እዚያው ደርሶ
ቤተክርስቲያን ሰራ እለቱን ስንዴ ዘርቶ፣ወይን
ተክሎ፣ጽድንም ወይራን ግራርን ተክሎ በአንዲት ቀን
ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እለቱን አድርሷል፤ስንዴውን
ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሷል፡፡
ከእለታት በአንድ ቀን አባታችን በጸሎት ላይ ሳለ መልአኩ
ቅዱስ ሚካኤል ከብሩህ ደመና ጋር ወደ እርሱ መጥቶ
በደመና ጭኖ ከፈጣሪው ዘንድ አደረሰው፡፡ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቅዱሳኖቹ እንዲባረክ
ካደረገ በኃላ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘው ወደ
ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ አድርሰህ አሳየው
አለው፡፡መላዕኩም እንደታዘዘው አደረገ፡፡መልሶም ወደ
ኢትዮጵያ ምድር ደብረ ዛብሒል ወደ ምትባል ቦታ
አደረሰው፡፡ ከዚያም ደርሶ ድንቅ ታምራትን አደረገ ውሃም
ከአለት ላይ እያመነጨ ህሙማንን ፈወሳቸው፡፡

በባህር ውስጥ ጠልቆ ዘወትር በሄደበት ሀገር ሀሉ
ሲጸልይየሚያርፍበትን ቦታና ስጋዬ የሚቀበርበትን ቦታ ግለጽልኝብሎ በጸለየጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተልኮ መጥቶ የአባትህ አባት ከሸዋ ሀገር መጥቶ ታቦተ እግዚአብሔር አብን ወደ አስተከለበት ወደ አባ ሙሴ ደብር ወደ አባትህና እናትህ ቦታ ዳውንት ምትባል ሀገር ሂድ ብሎ የእረፍት ቦታውን ነገረው፡፡ከዚያም ወደ ብዙ ገዳማት በመሄድ ቡራኬን ተቀበለ፡፡ ከአራት ዓመት በኃላ አረጋውያን መነኮሳትንተሰናበታቸው መርቀውት ተለያዩ፡፡

🍂 የኢትዮጵያን ገዳማትተዘዋውሮ እየጎበኘ ጎዣም ደረሰ ፤በዚያ እያስተማረ፣ እያጠመቀ የታመሙትን
እየፈወሰ፣የእውራንን አይን እያበራና ሙታንን እያስነሳ በዚያ ተቀመጠ፡፡ በባህር ውስጥም ገብቶ 9 ዓመት ለኢትዮጵያ ጸለየ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኃላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ይህችን ሀገር እና የኢትዮጵያን ህዝቦች ምሬልሃለሁ ከዚህች ባህር
ውጣ አለው፡፡ አባታችንም ከባህር ውስጥ ወጥቶ ተንበርክኮ ለጌታችን ሰገደ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማረፊያህ ቦታ ምስራቅ ወደ ምትሆን ወደ ዳውንት ሂድ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ አባታችንም በአስራሰባት ዓመቱ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄድበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ደረሰች፡፡ አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ጸለየ አለቀሰ በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ አላት ጸሐይም ወደ ኃላ ተመልሳ በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቃል ቆመች ደብረ አሰጋጅ እንደገባ ጸሐይም አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ
እገባ ዘንድ ፍታኝ አለችው እግዚአብሔር ይፍታሽ ባላት
ጊዜ ገባች፡፡

🍂 እድሜው ሰላሳ ሦስት በሆነ ጊዜ ወደ ደብረ ድባው
አበምኔት መጥቶ ሚያዝያ ዘጠኝ ቀን ምንኩስናን ተቀበለ፡፡በዚያ ደንጋይ ፈልፍሎ ዋሻ አዘጋጀ፡፡ ሉቃስ የሳላት ከግብፅ የመጣች የድንግል ማርያምን ስዕል አስገብቶ የዋሻውን በር ዘጋ፡፡ ያለ ደቀመዝሙሩ ልብሰ ክርስቶስ
በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር አይገናኝም፡፡በዚህ ድንቅ ድንቅ
ታምራትን እያደረገ ሁለት መቶ አርባ ሺ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣ፡፡

ያባታችን የረፍት ጊዜ በደረሰ ሰዓት ጌታችን ለአባታችን
ቃልኪዳን መታሰቢያህን ያደረገ ዝክርህን የዘከሩ
የገድልህን መጽሐፍ የጻፉ ያጻፉ ቤተ ክርስቲያንህን የሠሩ
ያሠሩ የሠሩትን ኃጢአት ይቅር እላቸዋለሁ።

ወዳጄ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ገድልህን የጻፈውን ያጻፈውን
ያነበበውን የተረጎመውን ጽፎም በቤቱ ያስቀመጠውን ሰው የተለያዩ በሽታ የሚያመጡ ሰውን የሚፈትኑ ርኩሳን
አጋንንት አይቀርቡትም ተላላፊ በሽታ ወይም ተስቦ
ተቅማጥ ርኃብ ቸነፈር የውኃ መታጣት የልብስ መራቆት
መዥገር አይደርሱበትም ሌጌዎን የተባለ ክፉ ጋኔንም
ፈጽሞ አይቀርብም። ፋኑኤልና ሩፋኤል እስከ ዘለዓለሙ
ይጠብቁታል ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ
የሰማይ መላእክት በተድላ በደስታ ወደ ሰማይ ያሳርጉታል።
እንዲሁም ጌታችን በርካታ ቃልኪዳኖች ላባታችን
ተሰቷቸዋል ገድላቸውን ገዝተን እናንብበው በቤታችን
እናስቀምጠው ።

አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
በሚያዚያ 9 ቀን አርፉ ::

የአባታች የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
ረድኤት እና በረከት አይለየን 🙏🏽



ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሣት ሥዕላት ሠዓሊ /

📞 +251923075264

@deacongetabalewamare
2025/02/06 04:00:41
Back to Top
HTML Embed Code: