tgoop.com/dmtse_tewaedo/9819
Last Update:
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርቱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቀረበ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ በዝርዝር በማጣራት የመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደያቀርብ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ባለፉት ዐሥራ አምስት ቀናት ሲያከናውናቸው የሰነበተውን የማጣራት ሥራዎች በማስመልከት ያዘጋጀውን ሪፖርት ዛሬ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል።
አጣሪ ኮሚቴው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአካል ተገኝቶ ማጣራት እንዳይችል የተከለከለ መሆኑን በመጥቀስ መረጃውን ለማሰባሰብ ይቻል ዘንድ ተበዳዮች በስልክ፣በቴሌግራምና በዋትስ አፕ እንዲሁም በአካል በመቅረብ በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ፣በድምጽና በቪዲዮ በተቀረጸ ማስረጃ ጭምር መረጃዎችን ማሰባሰቡን፣መተንተኑን፣ማደራጀቱንና ጥቅም ላይ ማዋሉን ገልጿል።
በሪፖርቱም ከመልካም አስተዳደርና ከብልሹ አሠራር ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በማስረጃ ተደግፈው የቀረቡ ሲሆን በማጣራት ሥራው የተረጋገጡ ጉድለቶችንና ጥፋቶችን መሰረት በማድረግም በጊዜያዊነትና በቋሚነት ችግሮቹን ለመፍታትና የካህናትና የአገልጋዮችን ቅሬታ ዘላቂነት ሊፈቱ ይችላሉ ተብለው የቀረቡ በሰባት ነጥቦች የተተነተኑ የመፍትሔ ሐሳቦችና በዘጠኝ ነጥቦች የተተነተኑ ችግሮቹንና የመፍትሔ ሐሳቦችን አቅርቧል።
የጥናት ሰነዱ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
#ድምፀ_ተዋህዶ
@dmtse_tewaedo
@dmtse_tewaedo