tgoop.com/etelawyan/5233
Last Update:
ልባሟ እህቴ 😍 ሆይ
☞አንቺ ግን እህቴ የውበት መዋቢያሽን ከእግዚአብሔር ግዢ፤ ኩል በሆነው ደሙ🩸 ተዋቢ፤ መስታወት 🪞 በሆነው ቃሉ 📖 ራስሽን ተመልከቺ 👀፤ አረማመድሽ በቄንጠኛ 💃 መሆኑ ቀርቶ እንደቃሉ 🧖♀ ይሁን።
☞በሰው ሜካፕ የተሰሩ አርባ ሺህ ብር ይከፍሉ ይሆናል አንቺ ግን እግዚአብሔር ካስዋበሽ ዋጋሽ ተመን አልባ ነው። ለአንድ ጊዜ ሳይሆን ለሁልጊዜ ውብ ትሆኛለሽ። ሰው እንደሚያስውብሽ አምነሽ ፊትሽን እንደሰጠሽው እግዚአብሔር እንዲኩልሽ ልብሽን ስጪው።
እህቴ እስኪ በደንብ አስተውይ 🤔
☞ዶክተር ራጅ አንስቶ፣ አፍሽን ክፈቺ ምላስሽን አውጪ ብሎ፣ አልትራሳውንድ አገላብጦ፣ ሆድሽን ቀዶ ያይኻል። እህቶቼ x-ray የማያነበውን፣ ሆድሽን ቀዶ እንኳ ማየት የማይቻለውን ከትላንት እስከ ፍፃሜ ያለሽን ማንነትሽን እግዚአብሔር ያውቀዋል። በቃሉ ይመረምርሻል፤ በፍቅሩ ያክምሻል።
☞ እህቴ ማንም በማያውቅሽ የስደት አገር ላይ ልትሆኝ ትችያለች የልብሽን የሚያውቅ ቋንቋሽን የሚሰማልሽ አጥተሽ ይሆናል። አይዞሽ ‼️ የሚያውቅሽ ዘንበል ብሎ የሚሰማሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው። ያንቺ ነገር ግድ ይለዋል በተረሳሽበት ዘመን ያስታውስሻል፤ ባዘንሽበት ወራት ያስደስትሻል ።
ከትምህርቱ መሀል የተወሰደ ነው አድምጡት በደንብ ታተርፉበታላችሁ 🙏
ለማንኛውም ጥያቄ ሃሳብ እና አስተያየት 📥 @yeabm
🙌መልካም ምሽት ቸር ቆዩልኝ🙌
በፍቅር 🥰 የምታምሩበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበረቁበት ሰናይ 😁 ምሽት ይሁንላችሁ
✍ የአብስራ ተስፋዬ @yeabm
Join and share
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5233