tgoop.com/etelawyan/5258
Last Update:
አይዞሽ
አንቺ ከመኖሪያሽ ተነስተሽ ወደ አንድ ከተማ በመኪና ስትጓዢ ለዓይን ያማረሽን ለምላስ የጣመሽን ምግብ ቋጥረሽ ትጓዣለሽ። እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ወጥተው የሲና ምድረ በዳን ሲያልፉ የቋጠሩት ምሳና እራት አልነበረም። በማያርሱበት በማይዘሩበት በማያጭዱበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ጎራ ብለው የሚበሉበት ሬስቶራንት በሌለበት፣ የታሸገ ምግብ የሚገዙበት ሱፐርማርኬት ባልኖረበት ምድረ በዳ ላይ እግዚአብሔር መናና ድርጭት እየመገበ መራቸው። ከመሀላቸው አንዳች የተራበ አልነበረም። እግዚአብሔር መሪ የሆነበት ህይወትና ጉዞ በጉድለት ሳይሆን በበረከትና በጠል የተመላ ነው። ወዳጄ አምላክሽ እስራኤልን በምድረ በዳ የመገበ፣ እውር አሞራን የሚቀልብ፣ ድንጋይ የተጫነውን ትል የማይረሳ፣ ትንሿን ትንኝ ሳይዘነጋ የሚመግባት ጌታ ነው። አንቺንማ ሞቶልሽ እንዴት ይረሳሻል ርቦሽ እንዴት ይጨክንብሻል በፍፁም!
ምድረ በዳ በሆነ የህይወት ቀጠና ብታልፊ፣ ዘርተሽ የማታጭጂበት ሰርተሽ የማታተርፊበት፣ ቀድተሽ የማትጎነጪበት ሁኔታ ላይ ብትሆኚ እንኳ በሚያስፈልግሽ ሁሉ መለኮታዊ እጁን ይገልጥልሻል።
ምድረ በዳ ነው ብሎ ሰው ሲጨነቅ በምድረ በዳ አንቺን ለመርዳት የማይከለክለው ጌታ የበረከቱን ጠል ያዘንምልሻል። በሲና ምድር እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሰዎች ለጉብኝት አልፈዋል፣ ሀገር አቋርጠው ሄደዋል ያቋርጡ እንጂ መና አልበሉም ከአለት ውኃ አልጠጡም የጠጡት በእግዚአብሔር ያመኑት እስራኤላውያን ብቻ ናቸው። አንቺ ግን ሰው በሚራብበት ዘመን ትጠግቢያለሽ፣ ሰው በሚጠማው ዘመን ትረኪያለሽ፣ በሚሞትበት ዘመን በህይወት ትኖሪያለሽ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያዘጋጃል! "እናት ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ታበላለች እግዚአብሔር ግን ከሞትም ቀስቅሶ ይመግብሻል።" በአንዳች አትጨነቂ እግዚአብሔር ያዘጋጃል።
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
መልዕክት፣አስተያየት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ
በ @Yeabm
🕊//ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር //🇪🇹
@Etelawyan 🇪🇹
@Etelawyan3 🇪🇹
@Etelawyan 🇪🇹
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5258