tgoop.com/etelawyan/5263
Last Update:
#ይቅር__በለኝ🙏
#ከኃጢያታችን የበለጠ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝነው ይቅር አይለንም ብለን ማሰባችን ነው። በደል የሌለበት አምላክ ከእኛ ከትቢያዎቹ ጋር ራሱን አቻ አድርጎ "ኑና እንዋቀስ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዛቶ ትጠራለች" ብሎ የምሕርት ጥሪ እያቀረበ ይቅር አይለኝም ሰንል ሲሰማን ያዝናል። (ኢሳ,፩፥፲፰)
አንተ በክፉ ሥራህ ራስህን ብትጠላውም እንኳን #እግዚአብሔር ግን አይጠላህም፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው #እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር አንተ #ለራስህ ካለህ ፍቅር ይበልጣል» እንደ ይሁዳ ብትክደው ፣ ወዳጅህን ብትሸጥ፣ ንጹሕ ደም በግፍ ብታፈስስ፣ ሙዳየ ምጽዋቱን ብትዘርፍ፣ እንደ ይሁዳ በአምላክነቱም ጨርሶ ባታምን እንኳን ፈጣሪ የሚጠብቀው የምትሞትበትን ሳይሆን #የምትጸጸትበትንና የምትመለስበትን ቀን ብቻ ነው። በወንጌሉ «እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት» እንደሚል #እግዚአብሔር ከእርሱ እጅግ በጣም ርቀህ እያለህ እንኳን እያየ ያዝንልሃል እንጅ አያዝንብህም። (ሉቃ. ፲፭፥፳)
#_ሰናይ__ቀን🙏
🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️
🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ @yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥• 💚
💛 •✥• @Etelawyan3 •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5263