tgoop.com/etelawyan/5264
Last Update:
እግዚአብሔር ዝም ሲል 😢
አስተውላቹ ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ሲል ተናጋሪ ይበዛል ኢዮብ ትዝ ይላቿል ምንም በማያውቀው ጉዳይ ምክንያት ያለው ንብረት ሁሉ አንድ በአንድ ሲጠፋበት፣ የገዛ ሚስቱ እንኳን ስትክደው ፣ ሰውነቱም በገል ብረት ሲቆሳስል እግዚአብሔር ግን በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ዝም ሲለው ነበር ፤ ነገር ግን ኃላ ላይ እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ የነበረውን ሀሳብ ሲጨርስ በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ እንደ ገና እንዳሰበው ቅዱሱ መጽሐፍ 📖 ይነግረናል ።
ወዳጆቼ አስቸውሉ የእግዚአብሔር ድምጽ በጣም አስፈልጓቹ ድምጹን ግን ሳትሰሙት ስትቀሩ እግዚአብሔር በህይወታቹ ላይ እናንተ ሳታውቁ የሆነ ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሆነ አስቡ፤ አንዳንዴ ደግሞ በእግዚአብሔር ዝም ውስጥ እናንተ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ልታልፉ ትችላላቹ ነገር ግን ከብዙ ዝምታዎች በኋላ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስትሰሙ የቀድሞ ዝምታው ለምን እንደነበር ይገባቿል።
ዝምታው ውስጥ ክብር አለ 🔥
🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️
🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ @yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥• 💚
💛 •✥• @Etelawyan3 •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5264