tgoop.com/etelawyan/5265
Last Update:
ምን አይነት ፍቅር ነው 🙆
መግደላዊት ማርያም ትባላለች ፈጣሪዋን በጣም ከመውደዷ የተነሳ " በቃ ጌታሽ እኮ ሞቷል " ተብላ እንኳን ሽቶ ልቀባው ነው በሚል ሰበብ የሞተ ስጋውን ለማየት ለሊቱ እስኪነጋላት አጠብቅም ፤ ባይገርማቹ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርቶች ኢየሱስ በህይወት እያለ " አንተ ጌታችን ነህ " ብለውት ነበር ነገር ግን ኃላ ላይ እንደ ሰው ሲሞት ሀሳብ ቀይረው ሁሉም ወደ ኋላ ተመለሱ ይቺ ድንቅ ሴት ግን በህይወት እያለ በራሷ ላይ ብቸኛ ጌታ ያረገችውን ኢየሱስን ሞቶም እንኳን ልትቀይረው አልፈለገችም፤ ምን አይነት ፍቅር ነው 😭 ምን አይነት መረዳት ቢኖራት ነው ኢየሱስ ሞቶም እንኳን ለእርሱ ያላት ፍቅር አልቀዘቅዝ ያለው እናንተዬ ለካስ ፈጣሪ እንዲም ይወደዳል....ትዝ ካላቹ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የገለጠው ለዚች ድንቅ ሴት ነበር 🔥
የተወደዳቹ እህቶቼ ትናንት ላይ ይህቺን ልባም ሴት 😍 የነካት ይሄ ታላቅ ፍቅር ዛሬ ላይ ሁላችንንም ይንካን የእርሷን የልብ ማስተዋል ለእኛም ያድለን 🔥🔥
🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️
🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ @yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥• 💚
💛 •✥• @Etelawyan3 •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5265