tgoop.com/etelawyan/5267
Last Update:
ወዳጆቼ 🥰 ማፍቀርም ሆነ መፈቀር የማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ባህሪ ነው
🌹ፍቅር መስዋትነት ነው ላፈቀሩት ሰው ደስታ ፣ሰላም ፣ምቾት፣እረፍት ሲሉ የራስን ደስታ አቶ ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ የሚከፈለውን ዋጋ ነው።
🌹የእውነት ያፈቀረ ሰው ለኔለኔ ከሚል ስሜት የፀዳ ፥ ለኔ ከማለት ይልቅ ለወደደው ሰው ራሱን ሳይሰስት መስጠት ነው ለኔ።
👉ፍቅር የማንነት... የዘር... ወይንም የገንዘብ ጥያቄ አይደለም.......የህሊና የነብስ እና ራስን አሳልፎ የመስጠት 😍ጥያቄ እንጂ.....💖
ፍቅር እኔ....እኔ...ለኔ....ለኔ ከሚል የራስ ወዳድነት ቀንበር የፀዳ ነው፡፡
❣እውነተኛ ፍ...ቅ...ር በእድሜ የማይለካ...በችግሮች የማይገታ በማግኘት ያልተጀመረ በማጣትም የማይቀየር የሰብአዊነት ጥምረት ነው::❤
👉 ከባዱ ነገር ፍቅር መጀመር ሳይሆን በፍቅር መቆየት ነው::
👉ስለ ፍቅር ቢያወሩ የሚያምርባቸው ፍቅርን በፊልም የተማሩት ሳይሆን በፍቅር የኖሩት ናቸው ፡፡😘
👉ፍቅር ማለት😘 እወድሻለው እወድሀለው ከመባባል በላይ በተግባር የሚፈተን....በመተማመን የሚፀና...በመደማመጥ 😍የሚሆን...በመከባበር❤ የሚሰምር ...የህይወት ማጣፈጫ ቅመም የሆነ የፈጣሪ የፀጋ ስጦታ ነው፡፡ ማፍቀር መፈቀርም መታደል ነው፡፡ሁለቱንም ማግኘት ደግሞ መመረጥም መባረክም ነው፡፡😍
ፈጣሪ "ፍቅርን" ያብዛልን!!!😜አምላካችን የሚያከብረን የሚያምነን አጠፋህ ብቻ ሳይሆን አጥፍቻለሁንም የሚያውቅ ፈጣሪው ይቅር ሲል ይቅር እንደሚለው አውቆ ይቅርታን በልቡ ያተመ እዉነተኛ አፍቃሪ ይስጠን ❤️😘
┄┉┉✽»✨🌹✿🌹✨»✽┉┉┄
#ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
Join and share
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5267