tgoop.com/etelawyan/5268
Last Update:
አረ ወገን እያስተዋልን 🤔
ሰው እንዴት እግዚአብሄር ይስጥልኝ ሲባል ....አይ ምንም ችግር የለም እንዴት ይባላል 🙊
👉ይህ ቋንቋ ለርዕስ አይመች ለምንም አይመች ።
👉 አሁን ይሄ ምን ይባላል በወላዲቷ ?
ባህል፣ እምነት ምንም አይገልፀውም እንደው ከንቱ ልማድ ካልሆነ በቀር
ሰዎች እግዚአብሄር ይስጥህ(ሽ) ሲሉን ሁልጊዜ መልሳችን ችግር የለውም የሚል ነው እስቲ ማን ይሙት 🙈 አሁን እኛ ችግር የለብንም ?
👉ያውም ተቆጥሮ ተሰፍሮ የማያልቅ ነዋ .....በችግር ያደግን ፣በችግር የተመረቅን፣ በችግር ወላፈን ተጠብሰን የኖርን የምንኖር አይደለንም ? እንዲህ ማለት በኛ አይምርም 🙅♂ ኑሮ ናላችንን አዙሮት ፣በበሽታ ጠውልገን፣ ሌቱ ጠሮብን፣ ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖብን እግዜር ይስጥህ ስንባል ችግር የለም እንላለን ⁉️
አሜን🙏 ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ማንን ገደለ 🤔 እንደው የአምላክ እናት የአስራት ሀገር የብዙ ቅዱሳን መካናት መገኛ በቅዱሱ መፅሐፋችን ኢትዩጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተሰኘች ደግሞ ኢትዩጵያ ሲባል ምድሪቷና ዛፎቹ ጋራ ሸንተረሩ ሳይሆን ህዝቦቿን መሆኑን አትዘንጉ እንኳን እኛ ብዙ የተባለልን ቀርተን
👉 ፈረንጆች እንኳ የእግዚአብሄር ስም ላልተጠራበት ምስጋና ቴንኪው ሲባሉ ዩ አር ዌልካም ነው የሚሉት እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለን የተሰኘንስ እግዚአብሄር ይስጥልን ስንባል ችግር የለም ማለታችን ያሳፍራል ከዕርሱ ከቸር አምላካችን በላይ ማን አለ ማን ይስጠን 🤔
🌹 ወዳጆቼ በዛ በሰፊው እጁ እየሰፈረ የሚያኖረን መልካም አባት እርሱ ነው ።
ከኛ አንደበት ይሄ ቃል ሲገኝ ያስነውራል ።
ቅድስናችን በአንደበታችን ጭምር ነውና የምንናገረው ቃል ሁሉ የተቀመመና ማስተዋል ያለበት እንጂ ከንቱ ንግግር መናገር የለብንም ለማለት ነው ወዳጆቼ ።
ከዚህ በኃላ መልሳችን አሜን 🙏 ብቻ ነው ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወዳጆቼ 🙏
┄┉┉✽»✨🌹✿🌹✨»✽┉┉┄
#ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
Join and share
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️
💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5268