ETELAWYAN Telegram 5269
ወዳጆቼ ይነጋል 🥰

👉ለአንዳንዶቻችን መሽቶብናል፣

👉 ለአንዳንዶቻችን ጀንበር አዘቅዝቃብናለች፣

👉ለአንዳንዶቻችን በር ተዘግቶብናል፣

👉 ለአንዳንዶቻችን ተስፋ መቁረጥ ጓዙን ጠቅልሎ እኛ ጋር ከትሞብናል፤

👉 ለአንዳንዶቻችን በፀሐይ ጨልሞብን መሸሸጊያ አጥተናል ።

👉 ምናልባት የስራ ማመልከቻችሁ ተቀባይነት አጥቶ ይሆናል፣

👉ምናልባት ፕሮሰሳችሁ አላለቀላችሁ ኢምባሲ ተቀባይነት አታችሁ ይሆናል፣

👉 ምናልባት የጠየቃችሁት ይቅርታ ተቀባይነት እጥቶ ይሆናል ግን ወዳጆቼ አንዳች ልባችሁ አይሸበር አምላካችሁ አባታችሁ ፈጣሪያችሁ እግዚአብሄር ተቀብሏችኃል 🥰

ደግሞ እግዚአብሄር የተቀበለውን ማንም አይጥለውም ሰዎች ቢቀበሏችሁ ባሉበት ቦታ ነው እግዚአብሄር ግን ሲቀበላችሁ በሰማይና በምድር ነው በኢትዮጵያ ተቀባይነት ብታገኙ የኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ የሚፅፍላችሁ እስከ ድንበሩ ነው ።

እግዚአብሄር ግን ድንበር የለውም በሰማይና በምድር ነው። በእውነት እግዚአብሄር ተንከባክቦ አንከብክቦ በትከሻው አሰማርቶ ነው የያዘን።

 የዓለም ውበቷ ይሄ ነው 😢

      የእግዚአብሔር ቃል ግን "ማታም ሆነ ፤ ጠዋትም ሆነ" (ዘፍ 1፥13) ሰው ከጠላህ ጠላህ፣ ከጨከነ ጨከነ፣ ጥርሱን ከነከሰብህ ነከሰ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ይራራልሃል። ጨለማውን በዛው አያስቀረውም ያነጋዋል ጠዋትን ያመጣልሃል። የሚጨልመው ላንተ ሊመስልህ ይችላል ለደከማቸው ማረፊያ ነው ላንተ ደግሞ የንጋት መምጫ ዋዜማ ነው። እግዚአብሔር ለአንተ ጨለማ ቀን የለውም  የሚነጋ ፣የሚያብብ ፣ የሚደምቅ፣ የሚያምር፣ የሚስብ ቀን ይወጣልሀል።

    ሁሌም አስታውስ ወደ ጎን 360 ዲግሪ ብትዟዟር ካንተ በቀር የምታየው የሚረዳህ ላይኖር ይችላል፤ ቀና ስትል ግን የሰማይ ደጅ ላንተ ክፍት ነው። አባትህና የርሱ የሆነው ሁሉ ያንተ ነው።

አይዞህ ጨልሞ አይቀርም ይነጋል። እግዚአብሄርን አላልፍም ብሎ የሚገዳደር የትኛውም ሀይል የለም። አሳላፊው ስላለ ያልፋል። አልነጋም ብሎ ስታክ አርጎ የሚቀር የጨለማ ለሊትና የልብ ክረምት የለም።
በጨለመብህ ጊዜም ቢሆን ጭለማ ውስጥ ጌታ ሊያሳይህ የፈለገውን ነገር ለማየት ሞክር።

    ፀሐይዋ ወደመኝታዋ ስትሄድ ጥላዋን ትልክልናለች ጨለማው ሲደምቅ የሚያምሩ ከዋክብትን እናያለን። በጨለሙብን ነገሮች ውስጥም እንባችን የጋረዳቸው ከዋክብቶች ይኖራሉ እነሱን እያየህ ለሊቱ መንጋት ይሆንልሀል።

አይዞህ ጨልሞ አይቀርም ይነጋል
ዛሬ ባንተ ላይ የሆነው ካንተ በፊት ብዙ ሚልየን ሰዎች ላይ ደርሷል። አንተ መጀመሪያ አይደለህም መጨረሻ ግን ልትሆን ትችላለህ። ምንም ይሁን ምን ቢመሽም ይነጋል።

    ┄┉┉✽»🌹🌹»✽┉┉┄
             
#ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ

የአብስራ ተስፋዬ))

  📩Coment- Telegram ላይ
@Yeabm

Join and share
💚💛❤️
@Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️
@Etelawyan 💚💛❤️
💚💛❤️
@Etelawyan 💚💛❤️
 
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

tgoop.com/etelawyan/5269
Create:
Last Update:

BY ኢትኤላውያን🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5269

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

How to Create a Private or Public Channel on Telegram? Read now Select: Settings – Manage Channel – Administrators – Add administrator. From your list of subscribers, select the correct user. A new window will appear on the screen. Check the rights you’re willing to give to your administrator. Content is editable within two days of publishing Concise
from us

Telegram ኢትኤላውያን🇪🇹
FROM American