tgoop.com/etelawyan/5276
Last Update:
ከጓደኞቻቹ ጋር ላቀያይማቹ ነው 🤫ትዝ ይላቿል ያ 38 አመት ሙሉ ወደ መጠመቂያው ውሃ የሚወስደው ሰው አጥቶ በመጨረሻ ኢየሱስ የፈወሰው ሰው ? (ዮሐንስ ወንጌል 5 ላይ)....
እሺ ያስ ሰዎች የቤት ጣራ ቀደው ኢየሱስ ጋር ያደረሱት ሽባው ሰው ? ( ማርቆስ 2 ላይ ).. በነገራችን ላይ እዚህ ጋር ሁለቱም ሰዎች ሽባዎች ናቸው ፣ ሁለቱም መራመድ አይችሉም ፣ ሁለቱም የሰው ድጋፍ ይፈልጋሉ ነገር ግን በመካከላቸው አንድ ልዩነት ነበረ 😊 የምን ልዩነት ካላቹኝ "የጓደኛ ልዩነት " ይሄን ክፍል በደንብ አንብባቹት ከሆነ ያ 38 አመት ሙሉ ሽባ የነበረው ሰው ጓደኞቹም እንደርሱ ሽባዎች ነበሩ ለዛም ነው ለ 38 አመታት ሙሉ ማንም የሚረዳው ጠፍቶ በሌሎች ሰዎች ሲቀደም የነበረው ነገር ግን እዚኛው ሽባ ሰው ጋር ስንመጣ ጓደኞች መራመድ የሚችሉ ፍፁም ጤነኞች ነበሩ 👌 እንደውም በጣም የሚገርመው እነኚ ጓደኞቹ ሽባውን ጓደኛቸውን ፈጣሪ ፊት ለማቅረብ ብለው ጣራ እስከመቅደድ ድረስ ደርሰው ነበር 🙆 ...
ወደ እናንተ ልመለስ እና እናንተጋስ ያሉት ጓደኞች እንዴት ናቸው ይራመዳሉ ወይስ ሽባዎች ናቸው ? እናንተንስ የመቀየር አቅም አላቸው ወይስ እነርሱ ራሱ ሰው ያስፈልጋቸዋል ?
እስኪ መልሱልኝ እውር እውርን መምራት ይችላል🤚 ? አይችልም አይደል 🤗 ስለዚህ የሆነ ጉዳይ ላይ ማየት የሚከብዳቹ ከሆነ በዛ ጉዳይ ላይ በደንብ ማየት የሚችሉ ሰዎችን ጓደኞቻቹ አድርጉ ካለዚያ እናንተን ሊቀይሩ በማይችሉ ሰዎች ምክንያት ብቻ ብዙ ነገሮችን ታጣላቹ።
እስቲ #Share💯Share
🤗አቅፎ እና ደግፎ ሰላም ያሳደረን አምላካችን ቀናችንን ባርኮ ቀድሶ ሰላም ያውለን ሰናይ ቀን🙏
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan3 •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5276