tgoop.com/etelawyan/5282
Last Update:
#የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር ከምግብ፣ ከውሃ ከመጠለያ፣ ከሁሉም መሰረታዊ ፍላጎቶች በፊት በህይወት እንዲቆይ ፍቅር ያስፈልገዋል።
🌹ፍቅር ከሌለው ባይሞትም ገዳይ ነው፤ ባንቀብረውም ሙት ነው።
🌹በህይወት ቢመላለስም ሬሳ ነው።
🌹ፍቅር ህይወትን በትክክለኛ የመንገድ አቅጣጫ የሚተልም የስብእና ገበሬ ነው።
✝የክርስቶስን ፍቅር ከመተረክ ባለፈ በህይወታችን እንግለጠው።
✝የሚጠጡት ውሃ በሰጣቸው በምትኩ በሰፍነግ ሆምጣጤ እንደሰጡት
🌹በሰጣችኋቸው እምነት ፈንታ ክህደትን የለገሷችሁ፤
🌹በሰጣችኋቸው ፍቅር ምላሽ ጥላቻን ያሳጨዷችሁን፤
🌹ስትስሟቸው የነከሷችሁን፤
🌹ክርስቶስን በበርባን እንደለወጡት በሌላ ሰው የለወጧችሁን ሁሉ እንደ ክርስቶስ ግሩም በሆነ ፍቅር ልባችሁን ከፍታችሁ በይቅርታ ተቀበሏቸው።
❤️ አልቀበልም ብላችሁ የገፋችሁትን ይቅርታ ዛሬ ተቀበሉ።
❤️አልሰጥም ያላችሁትን ይቅርታ ዛሬ ለግሱ።
❤️ፀፀትና በደል ባጎበጠው ህሊና መኖር ይብቃችሁ በይቅርታ ቀና በሉ ።
✝ፍቅርም እንደዚህ ነውና እንደዚህ አድርጉ ይላል ቃሉም ።
🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌
✍የአብስራ ተስፋዬ))
📩Coment- Telegram ላይ @Yeabm
💚 •✥• @Etelawyan •✥•💚
💛 •✥• @Etelawyan •✥•💛
❤️ •✥• @Etelawyan •✥•❤
BY ኢትኤላውያን🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/etelawyan/5282